Tuesday, 21 December 2021

ከላሊበላ ሰማይ ስር

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን እና ሀገር ጐብኚዎች ወደ ቅዱስ ላሊበላ መናገሻ ከተማ  11ዱ ፍልፍል አብያተ-ክርስቲያናት ወደሚገኙበት ሮሃ ከተማ ይጓዛሉ። ምክንያታቸው ደግሞ ታሪክና  ጥበብን ለማወቅ እንዲሁም በረከትን ለማግኘት።  በዚህ የጉዞ ማስታዎሻ ስለ ቅዱሱ ንጉስ( Holly king) ቅዱስ ላሊበላ እና ስራዎቹ ከላሊበላ ሰማይ ስር ስላሉት ነገሮች እናወሳለን።

Monday, 6 December 2021

ሰብአ ሰገል

የሰብአ ሰገል ምንነት፥ ታሪክ፥ ኮከቡ፥ ጉዟቸው፥ በስተመጨረሻው መሰወራቸው

አባታችን አዳም በዕለተ አርብ በነግህ ከተፈጠረ በኋላ እናታችን ሔዋን በሳምንቱ አርብ በዘመናችን አነጋገር 3 ሰዓት ላይ ከግራ ጎኑ ተፈጠረች። በገነትም 7 ዓመት ከ3 ወር ከ 17 ዕለታት ካሳለፉ በኋላ ሕግን ተላልፈው እፀ በለስን በመብላታቸው ከገነት ተባረሩ። በዚህ ግዜ አምላካችን እግዚአብሔር ለአዳም የተስፋ ቃል ሰጠው፤ እርሱም ከልጅ ልጅህ ተወልጀ ከ5 ቀን ከመንፈቅ በኋላ አድንሃለሁ የሚል ቃል ነበረ። ይህ የተስፋ ቃልና ከመላእክት ለአዳም የተሰጡትን ስጦታዎች አዳምና የልጅ ልጆቹ ሲቀባበሉት ቆይቶ ከካሕኑ መልከጼዴቅ እጅ ላይ ደረሰ። ከመልከጼዴቅ አንዳንዶቹ ለአብርሃም ተሰጠ ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ለኢት-ኤል ተሰጠ ይላሉ። 

Thursday, 4 November 2021

ኤክሳይዝ ታክስ ምንድነው?

ኤክሳይዝ ታክስ የቅንጦት እቃዎች ሆነው ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሰረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ፣ እንዲሁም የሕብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱና ማህበራዊ ችግር የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል የተጣለ ታክስ ነው፡፡

Friday, 1 October 2021

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በበረራ

ለመካከለኛው ምስራቅ እና ለገበያዎች ቅርብ የሆነችው በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ እንደ መዝለል ነጥብ ስትሆን የኢትዮጵያ ሥፍራ ስልታዊ የበላይነትዋን ይሰጣታል ፡፡ ከኤርትራ ፣ ከሶማሊያ ፣ ከኬንያ ፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከሱዳን ድንበር ጋር የተገናኘ ድንበር ተሻጋሪ አገራት የተገነቡ ሲሆኑ ፣ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የጎረቤትዋን ጅቡቲ ዋና ወደብ ሲጠቀሙ ቆይተዋል ፡፡ ሆኖም በቅርቡ ከኤርትራ ጋር ሰላም በመፍጠር ኢትዮጵያ ለአለም አቀፉ ንግድ የአሳባንና ማሳሳ ወደብ የኤርትራን ወደቦች መድረሷን ለመቀጠል ተዘጋጅታለች ፡፡

ስለ ለውጥ ያለኝ አተያይ

መለወጥና ስኬታማ መሆን የምትችለው በማድረግ ብቻ  ነው።  ስለዚህ የምትጓጓለት አንድ ሐሳብ ካለህ አሁኑኑ ጀምረው። ምክንያቱም የምትማርበት ብቸኛው መንገድ ይሄ ነው። 

You only learn by doing, so if you have an idea you crave to explore, start now—that’s the only way to learn. 


በአንድ አመት ውስጥ የምትሆነው በእያንዳንዷ ቀናት የምታደርጋቸው ልማዶችን ውጤት ነው። (አንተ የልማድህ ውጤት ነህ። እንደሚባለው።)

Who you’ll become in a year’s time is a summation of your daily habits and what you do everyday, today. 


እድገት የሚመጣው በሙከራ ነው። ነገሮችን በአዲስ መንገድ ማድረግና መሞከር ስታቆም፣ ማደግህንም ታቆማለህ። 

Growth is a function of experimentation; when you stop testing new ways of doing things, you stop growing. 


ታላቅ የሚያስብለው ውጤቱ ሳይሆን ሂደቱ ነው። እንድሁም፣ በማንኛውም ዘርፍ ላይ ውጤታማ ለመሆን ፅናትና ወጥነት ያስፈልጋል። 

Greatness is in the process, not the result—to be great at anything, you must be consistent.


ብዙ የለውጥ በሮች በዙርያህ አሉ። ደስተኛ ካልሆንክ፣ አዳዲስ በሮችን ለመክፈት ሞክር። 

The doors to change are all around you; if you’re unhappy, try opening a new door in your life. 


የፈጠራ ችሎታህ ውጤታማ የሚሆነው ቀላል ሲሆን ነው። ነገሮችን አታወሳስባቸው። 

Creativity wins when it’s simple—don’t complicate things. 


ለማመስገን ሁሌም ምክንያት አለህ! 

You can always find a reason to be grateful.


Wednesday, 1 September 2021

ሀብታም ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?


የስኬት ንድፍ (Success Blueprint) 

ሀብታም ለመሆን የሀብታሞችን ባህሪ መላበስና የድሆችን አመለካከት ደግሞ ማስወገድ ያስፈልጋል። በዚህ ፖስት ብዙ ሰዎችን በድህነት ቀፍደው የሚያስቀሩ ስድስት የድህነት ባህሪያትን እንመለከታለን፤ ምክንያቱም የስኬት አንዱ መሰረት የውድቀት መንስኤዎችን ለይቶ ማወቅ ነው። እነዚህ ስድስት ባህሪያት የሚተገብራቸውን ሰው ሀብታም፣ የማይተገብራቸውንም ደግሞ ድሃ የሚያደርጉ ናቸው፣ ስለሆነም እነዚህ 6 ልማዶች ሀብታም እንዲትሆን ይረዱሃል ማለት ነው። የውድቀት መንስኤዎችን ለይተን ስናውቅ እግረ መንገዳችንን የስኬት መሰረቶችንም እንማራለን።

Tuesday, 18 May 2021

ታሪክን መማርና ማወቅ መጀመሪያ የድንቁርና ዕውር ዓይን ይከፈታል

 ታሪክን መማርና ማወቅ መጀመሪያ የድንቁርና ዕውር ዓይን ይከፈታል ሰነፎችንም በምክሩና በትምህርቱ ከድንቁርና ወደ ጥበብ ይመልሳል።

 ታሪክ ሦስቱን ዘመናት/ትውልድ (ኃላፊውን፣ ነባራዊውንና መጻዒውን) የሚያስተሳስር ድንቅ ድልድይ ነው፡፡ 

ታሪክ አንድን ጉዳይ ከሥር መሠረቱ ጀምረን እንድናውቀው ስለሚያግዘን የአንድን ክሰተት እውነታነት በስሜት ያይደለ አሳማኝ በሆነና ቅቡልነት ባለው መልኩ (logically) እንድንሞግተው፣ አልያም እንድንቀበለውም ያግዘናል፡፡ እናም ታሪክን በአግባቡ የሚያጠና ትውልድ በቂ መረጃ ያለው (well informed)፣ በራሱ የሚተማመን (self-confident) እና ትክክለኛውን ውሳኔ መስጠት የሚችል (decision maker) ይሆናል፡፡  

Saturday, 6 March 2021

አምሓራ ሳይንት አስት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን



 ኑ የበረከት ስራ እንስራ

ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ፣ ወልደ ነጎድጓድ፣ ፍቁረ እግዚእ፣ ነባቤ መለኮት(ታኦሎጎስ)፣ ቁጽረ ገጽ በመባል የሚታወቀው ወንጌላዊው ቅዱስ ዩሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣት የመጨረሻው ሽማግሌ ሐዋርያ እሱ ነበር፡፡ 

ቅዱስ ዩሐንስ የተወለደው በገሊላ አውራጀ በቤተ ሳይዳ ነው፣ አባቱ ዘብዴዎስ ይባላል፡፡ ቅዱስ ዩሐንስ ገና በወጣትነቱ ዘመን ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮ የጌታውን እግር ተከትሎ አድጓል፡፡ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የጌታ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ከነበሩት ደቀ መዛሙርት አንዱ ነው፡፡

Tuesday, 2 March 2021

ከአድዋ ምን ተማርን? ምን አተረፍን? ምንስ እንስራ?


 


በአፄ ምኒልክና በተቀሩት ጀግና የጦር መሪዎቻቸው  የሚመራው የኢትዮጵያ ወታደር በወራሪው ጣሊያን ላይ ድል ከተቀዳጀ ይኸው 125 ዓመት ሆነው። ከረጅም ዓመታት ጀምሮ የአድዋ በዓል በየአመቱ ይከበራል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንን ታላቅ የድል በዓል ያከብራል። አገሩን ከሚወደውና አዲስ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት ከሚፈልገው ጀምሮና፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከውጭ ኃይሎች ጋር በማበር ዛሬ አገራችን የምናየው ውድቀት ውስጥ እንድትወድቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለማበርከት ከበቃው ድረስ፣ ሁሉም በየፊናው ይህንን በዓል ያከብራል።

Sunday, 28 February 2021

አድዋ በኪነ ጥበብ ሰዎች

የአድዋ ድል የጥቁር ህዝቦችና የመላው አፍሪካ ኩራት ነው። ከዛሬ 125 ዓመታት በፊት ፋሺስቱ የኢጣሊያ ጦር ባህር ተሻግሮ፣ ድንበር ጥሶ በመጣ ጊዜ ጀግኖቹ ኢትዮጵያውያን ለወሬ በማይመች መልኩ ውርደትን አከናንበው ሸኝተውታል። ባልዘመነ የጦር መሳሪያ ጠላትን ለመመከት አድዋ የዘመተው የኢትዮጵያ ጦር ታላቅ ነኝ ያለችውን ኢጣሊያን ያንበረከከው አቻ በሚባል የውጊያ ስልቱ አይደለም። የዛኔ በውስጡ ከሰነቀው አይበገሬነት በቀር በቂ የሚባል ትጥቅን አልያዘም።

ያለአንዳች መጫሚያ በባዶ እግሩ ተጉዞ በሶሎዳ ተራሮች ዙሪያ ሲተም እዚህ ግባ ከማይባል ኋላ ቀር መሳሪያውና ከጦርና ጋሻው በቀር ጠንካራ መከላከያ አልነበረውም። አባቶቻችን ትናንት በከፈሉልን መስዋዕትነት ዛሬ ላይ ቆመን የምንመሰክረውን አኩሪ ታሪክ ጽፈውልናል። በእነ እምዬ ምኒልክ ደምቆ የታተመው ጀግንነትም ከሀገራችን አልፎ ለጥቁር አፍሪካ ህዝብ የነጻነት ምልክት ሊሆን በቅቷል።

መላው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ቀንበር በወደቀበት ዘመን ኢትዮጵያ «እምቢኝ» ስትል ታላቅ የተጋድሎ ዋጋ መክፈሏን ዓለም ያውቀዋል። ይህ መሆኑ ደግሞ ዛሬ እንደሌሎች ሀገራት የነጻነት ቀኗን ሳይሆን የድል በአሏን ለማክበር ግንባር ቀደም አድርጓታል። ይህን ተጋድሎ የውጭ ሀገራት ጸሀፍት ሳይቀሩ በበርካታ ታሪካዊ ድርሳናቸው ሲከትቡት ኖረዋል።

ከሁሉም በላይ ግን በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች እየተዋዛ ሲቀርብ የቆየው የኪነ-ጥበብ አውድ ግዙፉን ታሪክ ይበልጥ አጉልቶ ለማሳየት ታላቅ አቅምን መፍጠር ችሏል። 

አድዋ በሎሬት ጸጋዬ ብዕር ዋ! አድዋ


ከኪነጥበብ ማሳያዎች አንዱን ስናነሳ ደግሞ በዋናነት የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን የስንኝ ቋጠሮ እናስታውሳለን። ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን አድዋን ባነሳበት ስንኙ የጦርነት ውሎውንና የተገኘውን አኩሪ ድል ለማሳየት ሞክሯል። የአድዋ ጦርነት የኋላ ታሪክ የእያንዳንዱ ኢትዮጵዊ አኩሪ ድል የሁሉ አፍሪካዊ ደማቅ ታሪክ ነው። ይህንን ሀቅ

Saturday, 27 February 2021

ግስበት (gravity)

 











ግስፈት Gravity

ግስበት(gravity) ማናቸውም ግዝፈት (ክብደት) ያላቸው ቁስ ነገሮች እርስ በርሳቸው እንዲሳሳቡ ግድ የሚላቸው የተፈጥሮ ጉልበት ነው። በዕለት ተለት ኑሯችን ክብደት ያላቸው ነገሮች በአየር ከመንሳፈፍ ይልቅ ከመሬት ጋር እንዲላተሙ የሚያደረጋቸው፣ በሌላ አነጋገር ለነገሮች ክብደት

Friday, 26 February 2021

Tedbabe Mariam Negist (The Queen of the Monasteries)

 

Tedbabe Mariam Negist (The Queen of the Monasteries)







Tedbabe Mariam, one of the ancient monasteries of the Ethiopian Orthodox Tewahido church, is found 600 km north of Addis Ababa in south Wollo Diocese west of Dessie Town in Amhara Sayint Woreda. The distance from Addis Ababa to Dessie Town is 400 km and from Dessie to Tedbabe Mariam 200 Km, covering a total of 600 km.

Wednesday, 24 February 2021

የከተማ እድገት መሰረት፤ የኢኮኖሚ ደም-ስር፤ አንገብጋቢው ጉዳያችን የሁልግዜም ጥያቄያችን መንገድ መንገድ መንገድ

"መንገድ ካሰቡበት የሚያደርስ" የሚለው ብሂል ለአማራ ሳይንት አይሰራም።  የንግድ ልውውጦቹ የተሳለጡ እንዲሆኑለት፤ አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ በጊዜ እንዲያደርስና ተጠቃሚ እንዲሆን፤ የከተማዋ ነዋሪዎች የሚፈልጉትን ሸቀጥም ሆነ ምርት በጊዜ እንዲያገኙ፣ ወረዳዋ የቱሪዝም

ሃብቷ እንዲተዋወቅና የገቢ ምንጭ እንዲሆናት፤ የህክምና፣ የመብራት፣ የትምህርትና የመሳሰሉ አገልግሎቶች ወረዳዋ  እንዲዘምኑላት፤ በጥቅሉ የወረዳዋ ኗሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እንዲሻሻል፤  የወረዳዋ ልማትና እድገቷ እውን እንዲሆን  የዘመናዊ መንገድ  ልማት (የአስፋልት መንገድ)  ህዝቡ አብዝቶ የሚጮህለት ግን እስካሁን  ሰሚ ያጣ ጥያቄያችን ነው።

Sunday, 21 February 2021

ነነዌ

👉Neway Kassahu's View  (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

ነነዌ

ወቅቱ በቤተክርስቲያናችንን አስተምህሮ በቀናት አነስተኛ የሆነችው ጾም፤ ጾመ ነነዌን የምንጾምበት ወቅት ነው፡፡ ቀኑ እንጂ ተግባሩና ትምህርቱ ግን ሰፊ ነው። ነነዌን ብዙ ጊዜ ከምንሰማውና ካስተማርነው በላይ ትልቅ ምስጢራዊና ታሪካዊ ከተማ ናት፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያና ነነዌን የምናነጻጽርበት ብዙ ገጽታ አለን፡፡

ነነዌ የአሦራውን ጥንታዊ ከተማ ስትሆን በላዕላይ መስጴጦምያ በአሁኑ አጠራር በሰሜናዊ ኢራቅ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ ከተማዋን ሶርያ ቱርክ ኢራን ያዋስኗታል፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 1800 ዓ.ዓ በኩሽ ልጅ ናምሩድ የተቆረቆረች ከተማ እንደሆነች መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ዘፍ. 10፣ 11

በወቅቱ በአሦራውያን ግዛት ትልቋ የዓለም ከተማ ስትሆን በወቅቱ ታላቅ የሃይማኖት መዲና እንዲሁም የአሶራውያን አማልክት (ኬሽታር) ማማለኪ ስፍራ ተገንብቶባትም ነበር፡፡ ከተማዋ በተደጋጋሚ መሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ሲገጥማት የማምለኪያ ስፍራው ቢወድምም ከተማዋ እንደገና በ2260 ዓ.ዓ አካዲን በተባለው ንጉስ በድጋሚ ታንጻለች፡፡

ነነዌ በመጀመሪያ ስሟ የተጠቀሰው በዘፍጥረት 10፡11 ላይ ሲሆን የአሦር ግዛት ዋና ከተማ ነበረች፡፡ በንጉሡ ሕዝቅያስ ዘመን የይሁዳ ነቢይ የነበረው ኢሳይያስ የኖረባት፤ ሰናክሬም በ705 - 681 ዓዓ የገዛት፤ በኋላም በሁለት ልጆቹ አድራማሌቅና ሶርሶር በተባሉ ልጆቹ የተገደለባት ከተማ ናት፡፡ ኢሳ 37፡37-38

ነነዌ በአሁኑ አጠራር በሰሜናዊ ኢራቅ ከተማ ሞሱል (Mosul) በሚባል ስም ትጠራለች፡፡ በወቅቱ መቶ ሃያ ሺኽ ሰው ያኽል ይኖርባት የነበረ ሲሆን ከተማዋን ትንንሾቹን መንደሮች ጨምሮ ዞሮ ለመጨረስ ሶስት ቀን ይፈጃል።

ነነዌ በበደል ምክንያት እግዚብሔር ተቆጥቶ ሊያጠፋት ይኽንንም እንዲውቁ ዮናስን እንዲያስተምር አዘዘው፡፡ ሕዝቧ ሩህሩህ ስለነበር ከንጉሡ እስከ ሕዝቡ ሕጻናት እንስሳት ሳይቀሩ የእግዚአብሔርን ፊት ፈለጉ፣ ንሰሐ ገቡ እግዚአብሔርም ራራላቸው ይቅርም አላቸው፡፡ ነቢዩ ዮናስና ናሆም የነበረውን ታሪክ ጽፈው አቆዩልን፡፡ ነቢዩ ዮናስና ነቢዩ ዳንኤል መቃብር በዚያ የነበረ ሲሆን በአክራሪው እስልምና ISIS ሰራዊት ፈራርሷል፡፡

Saturday, 20 February 2021

ነፃ የመጽሃፍት ድረገፆችን (Websites) ይጎብኙ

 


የአምሓራ ሳይንት የማህበራዊ ሚዲያ መረብ  ተከታታዮች ኢትዮጵያውያን ጠቃሚና ነፃ  የሆኑ የመጽሃፍት ድረገፆችን  (Websites) እንጠቁማችሁ።

  • www.bookboon.com
  • http://ebookee.org
  • http://sharebookfree.com
  • http://m.freebooks.com
  • www.obooko.com
  • www.manybooks.net
  • www.epubbud.com
  • www.bookyards.com
  • www.getfreeebooks.com
  • freecomputerbooks.com
  • www.essays.se
  • www.sparknotes.com
  • www.pink.monkey.com


በቀጣይ በሌሎች ጠቃሚ ድረገጾች እስክንመለስ በfacebook ለወዳጅ ዘመዶችዎ ያጋሩ።

Thursday, 18 February 2021

የታቦር ተራራ (አምሓራ ሳይንት)

 ታሪክን ተሸክሞ ጠያቂ ያጣ ተራራ    ታቦር - አምሓራ ሳይንት



መገኛ (Astronomical position): 

  • ኬክሮስ (Latitude)= 10°55'60" North
  • ኬንትሮስ( Longitude)=  38° 58' East

ጆግራፊያዊ ስም:  የታቦር ተራራ

ከፍታ: ከባህር ጠለል በላይ 4247 ሜትር

መገኛ (Geographical location): አማራ ክልል፤ በደቡብ ወሎ ዞን፤ በአምሓራ ሳይንት ወረዳ ከአጅባር ከተማ በስተምስራቅ አቅጣጫ በኩል  30ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

👉ታሪካዊ ሁነት እና የታቦር ስያሜ

 (በአለቃ ወ/ሃና ተክለ ሃይማኖት 1958 ዓ.ም የግዕዝ መጽሃፍ)

💢ከቅድመ ልደት ክርስቶስ 982 ዓ.ዓ

የእስራኤሉ ንጉስ ሰለሞን እና የኢትዮጲያይቱ ንግስት ሳባ

Tuesday, 16 February 2021

ሳይንስን ለመማር እና ለማስተማር የሚጠቅሙ 5 የነፃ ድህረገፆች



1- Scitable

https://www.nature.com/scitable

ዝንባሌዎ ስለ ጅኔቲክስ እና ስለሮቦት ሳይንስ ማወቅ ከሆነ እንግዲያውስ ሳይቴብል ለርሶ የተከፈተ ድህረገፅ ነው፡፡ ይህ ድህረገፅ በማበብ ብቻ በግልዎ መማር የሚችሉበት ሲሆን ልክ እንደ ት/ቤት በጋራም ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በኦንላይን ክፍል ውስጥ መማር ይችላሉ፡፡ ይህ ድህረገፅ በዓለም ላይ የሳይንስ ነክ ፅሁፎችን በማሳተም በሚታወቀው በ Nature Publishing Group ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በሌሎች ትልልቅ የሳንስ ኩባኒያዎች ስለሚደገፍ ት/ቱን በነፃ ነው የሚያስተምረው፡፡

በዚህ የኦንላይን ት/ቤት ውስጥ በ 4 ብቁ ፕሮፌሰሮች የተዋቀረ ሲሆን ተማሪዎች ለሚጠይቁት ማንኛውም ጥያቄ ከ 48 ሰዓት ባነሰ የጊዜ ገደብ ውስጥ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

2- iTunes U

https://www.open.edu/itunes/

ይህ ድህረገፅ ከ 600 በላይ በሆኑ ዩኒቨርስቲዎች የሚደገፍ ሲሆን ዓለም ላይ አሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎችን ማለትም የስታንፎርድ፣ የያሌ እና የኤም አይቲን ዩኒቨርሲቲዎችን የማስተማሪያ መፅኃፎችና ሌክቸር ኖቶች ሰብስቦ ይዟል፡፡ ይህ ድህረገፅ በተለይ ለመምህራን ትልቅ እፎይታን ያመጠጣ ሲሆን የማስተማሪያ መፅሀፎች፣ ቪዲዮዎችን እና ፈተናዎችን አካቶ ይዟል፡፡

ድህረገፁ ሰፋ ያለ ይዘት ያለው ሲሆን በውስጡ የግብርና፣ አስትሮኖሚ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ጂኦሎጂ ፣ ኬሚስትሪ እና የመሳሰሉ ሳይንሶችን በጥልቀት ይተነትናል፡፡

Monday, 15 February 2021

እለታዊ የገበያ ዋጋ መረጃ www.aaminfo.gov.et አዲሱ ድረ-ገጽ

ለህብረተሰቡ እለታዊ የገበያ ዋጋ መረጃ የሚሰጥ አዲስ ድህረ-ገፅ ይፋ ሆነ

www.aaminfo.gov.et

---------------------------------------

የካቲት 05/2013 - የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት በከተማዋ ያሉ የገበያ ማዕከላትን በማስተሳሰር በተለይ ሸማቹ ማህበረሰብ ቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልክና የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም መረጃዎችን በማግኘት ግብይት ማግኘት ያስችላል ብለዋል።

በተጨማሪም የምርት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማወቅ፣ በምርቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪን ለመለየት እና ሸማቹ ህብረተሰብ በየትኛው የገበያ ስፍራ በምን አይነት ምርት በምን ዋጋ እንደሚሸጥ ካለበት ሆኖ ለማወቅ እንደማያስችል ኃላፊው ገልጸዋል።

Sunday, 14 February 2021

የስራ ማስታወቂያ ድረ-ገጾች


ይህ አምድ ሁሉም የስራ ማስታወቂያዎች የበይነ መረብ ስብስብ ሲሆን የተቀመጠው ሊንክ በመጫን ወቅታዊ ስራዎችን የሚያገኙበት ድረ-ገጽ ነው።


This column is an online collection of all job vacancy and it is a website where you can find the latest jobs by clicking the link.

Ethio jobs:
Link👉 https://ethiopage.com/

Reporter jobs:
Link 👉 https://www.ethiopianreporterjobs.com/

EZEGA website
Link👉 https://www.ezega.com/

ese work
Link 👉 https://www.esework.com/

AMN job Vacancy - ayerbayer
Link 👉 https://ayerbayer.com/

Addis jobs
Link 👉 https://addisjobs.net/

ET CAREERS
Link 👉 https://etcareers.com/

job web ETHIOPIA
Link 👉 https://jobwebethiopia.com/

Ethiopia Work. com
Link 👉 https://www.ethiopiawork.com/

Geez Jobs
Link 👉 https://www.geezjobs.com/

የጥቁር ገበያ


      ጥቁር ገበያ ምክንያት እና ጉዳት

የጥቁር ገቢያ (Black market)፤- ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ አንድን እቃ ወይም አገልግሎት መግዛትም ሆነ መሸጥ ክልክል በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ገዝቶ ወይም ሸጦ መገኘት ነው።


ለምሳሌ፤- የመሳሪያ ሽያጭ፤ የውጪ ምንዛሬ ሽያጭ፤ አደንዛዥ እጽ ሽያጭ፤ የሰው እና የሰው አካል ሽያጭ፤ እንሰሳት እና የእንሰሳት አካላት፤ ወዘተ መግዛት ወይም መሸጥ ማለት ነው።

ኦንላይን ትምህርት የሚሰጡ ምርጥ ዌብሳይቶች

 ኦንላይን ትምህርት የሚሰጡ ምርጥ ዌብሳይቶች


👉እድሜያችን 9 ይሁን 95 ኢንተርኔት ተዝቆ የማያልቅ ስፍር ቁጥር የሌለው እድሎችን ይሰጠናል፡፡ ከተጠቀምንበት።

ትምህርትን በተመለከተ ኢንተርኔት ለተማሪዎች በጣም ብዙ የመማር እድሎችን ይዟል፡፡ከታሪክ እስከ ኮምፒውተር ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች ላይ  ኦንላይን ትምህርት የሚሰጡ ዌብሳይቶች አብዛኛዎቹ ነፃ ናቸው፡፡

የተፈጥሮ ውብት (ጭቅማ)

 ጭቅማ (አምሐራ ሳይንት)



መንደሩ ዙሪያውን በገደል እና በገዳማት የተከበበ ሲሆን የአየር ንብረቱ ደግሞ ሞቃታማ ነው። ወደ መንደሩ ቁልቁል መውረጃ ሁለት የተፈጥሮ በሮች ብቻ አሉት። መልከአምድራዊ አቀማመጡ ደግሞ የተለያየ ቅርፅ አለው። ጭቅማ የአጅባር ከተማ ውበት ነው።

Friday, 12 February 2021

Minilik II crowing of black king











Look to Africa for the crowing of a black king. He shall be the redeemer.

                                                    Marcus Garvey

Adwa, a pre-eminent symbol of Pan-Africanism that thwarted the campaign of the Kingdom of Italy to expand its colonial empire in the Horn of Africa is an Ethiopian victory that ran against the current of colonialism.

125 years ago, traditional warriors, farmers, pastoralists and women defeated a well-armed Italian army at the battle of Adwa. The outcome of this battle ensured Ethiopia’s independence, making it the only African country never to be colonized.

SDና HD ሪሲቨር

SDና HD ሪሲቨር ልዩነት ምንድን ነው?

✅ በሁለቱ መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት

Standard Definition (የመደበኛ ጥራት) (ኤስዲ) ወይም High Definition (ከፍተኛ ጥራት (ኤች ዲ))  ያላቸውን  የቴሌቪዥን ስርጭቶችን  ለማሳየት መቻላቸው ነው ፡፡ 

✅ የኤስዲ(SD) ሪሲቨር  ሣጥን መደበኛ ጥራት(Standard Definition) የቴሌቪዥን ቻናል ስርጭቶችን ብቻ ማሳየት ይችላል።

✅ ኤችዲ(HD) ሪሲቨር High Definition (ከፍተኛ ጥራት) ደግሞ ሁለቱንም መደበኛ ጥራት እና ከፍተኛ ጥራት ቻናሎችን ያሳያል ፡፡ 

✅ ኤችዲ ሪሲቨር እንደ HDTV ማሳያ እንዲጠቀሙባቸው ከኮምፒዩተር ማሳያዎች(ሞኒተር) ጋር ማያያዝም ይቻላል ፡፡

◄◄◄◄◄◄🔹🔹🔹▻▻▻▻▻▻▻▻

Thursday, 11 February 2021

ሳይንትን በግጥም

 //አማራ ሳይንት//

----------✿----------

ገርት የብልህ አገር የምሁር መነሻ

ቆተት የምርት ሀገር የጤፍ መናገሻ

የበልግ ምድር ወዠድ የበያይት ጉርሻ

ቀጨዉ የማር ሀገር የጥበብ ድል መንሻ

የደንቆሮ ጫካ ያለባቸዉ ዋሻ

የብርቅየ እንስሳት ምሽግ መናገሻ

ሰንበት ብሎ ያየዉ ያንችን መዳረሻ ፡፡

Wednesday, 10 February 2021

Important scie-tech Acronyms

አስፈላጊው gmail account ለስራና ለመረጃ



የሳይቴክ አምዳችን ከትንሹ ከgmail ይጀምራል

  የራሳችንን የ gmail account ወይም የ Google account የምንከፈትበት መንገድ በስልካችን......


gmail account ማለት ምን ማለት ጥቅሙስ ምንድነው  ?

 🌱 gmail በቀጥታ ስራ ለማመልከት መረጃችንን cv ለመላክ የሚጠቅም የመልዕክት መላኪያ መቀበያ ነው።

Tuesday, 9 February 2021

የኢኮኖሚ ዋልታችን ግብርናችን! መልስ ለሗላቀር ግብርናችን ለአማሓራ ሳይንታችን



ለአርሶ አደሩ

****

ለአማራ ሳይንት የህብረተሰቡ ዋነኛ የኢኮኖሚያችን ዋልታ ግብርና እንደሆነ ይታወቃል። ሆኖም ወረዳዋ ራሷን በምግብ እንዳትችል እና  ግዜው የሚጠይቀውን የግብርና ልማት እንዳትከተል፣  የግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂ እንዳታገኝ ሲነፈጋት የኖረች ወረዳ ናት። አምሓራ ሳይንት የግብርናና የገጠር ልማት ስራዋ ለዘመናት ተረስቶ ከመሬት የተሻለ የግብርና የልማት ግብዓትን እንዳታገኝ   የወረዳዋ አርሶ አደሮች ከተመጽዋችነት የማያላቅቅ  ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የግብርና ዘይቤ ውስጥ እንድትሆን የተፈረደባት ወረዳ ናት። 

Sunday, 7 February 2021

Land of origin



 ETHIOPIA-ኢትዮጵያ "Land of origin"✈️🌍🇪🇹

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


🇪🇹 Ethiopia’s unique mix of fascinating history, deep-rooted identity, incredible natural wonders and rare wildlife makes its one of the most intriguing places on Earth.


🇪🇹 The country is home to landscapes as diverse as deserts, volcanoes and highlands, architecture ranging from rock-hewn churches to medieval-style castles, and wildlife that includes rare species such as the gelada baboon, the walia ibex and the Ethiopian wolf.

ክብረ አምሓራ የማንነታችን ዐምድ


 

ጀግና

 አትንኩኝ የሚለው የሰራ አካላቱ

ክንዱ እሳት ነበልባል ቁርጥ ያለ አሞቱ

አየናና ሜታ ወግሎ ነው እድገቱ

ደግነት ጀግንነት ደሞ ምን ቸግሮት

አምሓራ ሳይንቴው ስበር አስተምሮት

ካልነኩት አይነካም ጅንን ያለ ነው

ከነኩት አይለቅም ልክ ነብር ነው።



ፎጣ ለባሾቹ



ያገር ባለ አደራ ፎጣ ለባሾቹ

ከነኳቸው ነብር እንደ አንበሳ ቁጡ

ለአገራቸው ታማኝ ኩሩና ቅንጡ

የነጻነት አባት ነፍጠኛ ነው ፈርጡ !!


 በነገራችን ላይ በእያንዳንዱ  ፎጣ ስር እሳት የሚተፋ ነፍጥ እና ንፍጣሙን የሚያናፍጥ ወኔ አለ !!

ትዝታ ወ-ልጅነት

ኤቢ የማርያም ልጅ







ውሀ ቅጂ ብላ ብሰደኝ እናቴ

ወለሹን ቀዳሁት አወይ ልጅነቴ

አወይ ልጅነቴ ነፍስ አለማወቄ

ሲመጣ መሽኮርመም ሲሄድ መናፈቄ።


እያልን እያንጎራጎርን ነበር ድሮ ከወንዝ ውሀ የምንቀዳው

ወሎ ቤተ አምሐራ

ባህሌን እወደዋለሁ እኮራበታለሁ

ኑ አምሓራ ሳይንት እንሂድ

      

                       ****

(የተረሱ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ መስህብ ፍለጋ)

Photo credit: Amhara sayint press


ምስጢር፣ እውቀት፣ እውነት፣ ውበት፣ እምነት፣ ታሪክ፣ ጀግንነት፣ ተፈጥሮ ሁሉም በአንድ ላይ ተሰድረውና ተደምረው የሚገኙባትን ቦታ ፍለጋ እንሄዳለን ፡፡ አምሓራ ሳይንት

Saturday, 6 February 2021

ያላለቀው ልማታችን

 


ከአምሐራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ ወደ ርዕስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም እየተሰራ ያለው መንገድ ስራ 90 በመቶ የሚሆነው የአፈር ጠረጋና ምንጣሮ ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ ስራ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዑመር እንደገለጹት ከአጅባር ተድባበ ማርያም 30ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ ስራ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በመሰራት ላይ እንደሆነ ገልጸው አስካሁን በተሰራው ስራ 23 ነጥብ 17 ኪ.ሜትር የሚሆነው መንገድ የአፈር ጠረጋና የምንጣሮ ሥራ ተሰርቶለታል ፡፡

ኢኮኖሚያችን እድሜው የእለት ነው!

 



እኛ ሀገር የለት የለቱን ሰርቶ የሚኖረው በርካታ ህዝብ ነው! ምክንያቱም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ መደበኛ ባልሆነው (Informal economic sector) ላይ ነው ኢኮኖሚካሊ ህይወቱ የተመሰረተው! ስለዚህ የትኛውም አይነት ብጥብጥ ከአንድ ቀን በላይ ከቆየ በልቶ የማደርን ህልውና ነው የሚያሳጣው።

Friday, 5 February 2021

የሰርግ ስነ ስርዓታችንና አማራ ሳይንት

 

ጥር ወር በአብዛኛው የሀገራችን ክፍሎች የሰርግ ወቅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በገጠሩ የህብርተሰብ ክፍል ዘንድም ይህ ወር አድስ ቤተሰብ የሚመሰረትበት ወቅት ነው በአምሃራ ሳይንት ወረዳ ም በሰርግ ወቅት በሽማግሌዎች የሚመረቁ ምርቃቶችና ከሚዜሙ ዜማዎች መካከል በጥቂቱ ፡፡

ይህ ጋብቻ ስሩ ጠለቅ ጫፉ ዘለቅ ያለ ይሁን ፣ልጅቱንና ልጁን ያልምድልን፣ጋብቻውን የአብርሀምና የሳራ ጋብቻ ያድርግልን፣ ልጅ ወሎዶ ለመሳም፣እህል ዘርቶ ለመቃም ያብቃችሁ፣ ለእማ ለአባ ለመባል ያብቃችሁ፣ ለደጀ ሰላሙ ለስጋ ወደሙ ያብቃችሁ፣ እነዚህ የተጋቡ ልጆቻችሁ፣ለዘመድ ለወገን የሚተረፉ ያድርጋቸው፣ በቦታው ደግማችሁ ደግማችሁ ዳሩበት፣ ከውሀ ጢስ ከጢስ ቀልብ ይቀጥናልና ከዚህ እርግማን ይጠብቃችሁ፣ በወንድ ልጅ ተበከሩ በማለት በዕድሜ ባለጸጎች ይመረቃል ፣፡

Thursday, 4 February 2021

🌴🌴አሸንዳ🌴🌴

 ETHIOPIA-ኢትዮጵያ "Land of origin"✈️🌍🇪🇹

                  

🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊

                   #Ashenda

🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉


🇪🇹 #Ashenda is a unique #Ethiopian_traditional_festival_©️ which takes place in August to mark the ending of fasting called filseta. 

             🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

ለአማራ ሳይንት እንጮሃለን እንጠይቃለን መልስ ሳይሆን ተግባር እንሻለን!


 

Wednesday, 3 February 2021

🌻እንቁጣጣሽ🌻

 ETHIOPIA-ኢትዮጵያ "Land of origin"✈️🌍🇪🇹

Socio-cultural, Historical and Geographical view


     🌻ENKUTATASH?🌻

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

#Enkutatash is the name for the Ethiopian New Year, and means “gift of jewels” in the Amharic language. The story goes back almost 3,000 years to the #Queen_of_Sheba of ancient Ethiopia and Yemen who was returning from a trip to visit King Solomon of Israel in Jerusalem, as mentioned in the Bible in I Kings 10 and II Chronicles 9. She had gifted Solomon with 120 talents of gold (4.5 tons) as well as a large amount of unique spices and jewels. When the Queen returned to Ethiopia her chiefs welcomed her with #enku or #jewels to replenish her treasury.

ተድባበ ማርያም ወሎ አምሐራ ሳይንት

በይርጋለም ታደሰ

-ከክርስቶስ ልደት በፊት 982ዓ.ዓ 2990 ዓመት እድሜ አስቆጥራለች፡፡

-ከአክሱም ጺዮን ገዳም ቀጥሎ ጥንታዊ የሚባለው የተድባበ ማርያም ገዳም በኢትዮጵያ መስዋተ ኦሪት ከተሰዋባቸው 4 ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አንደኛዋ!

-ቅዱስ ሉቃስ እንደሳላት የሚነገርላት ጸደንያ የቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል መገኛ!

ቤተ አምሐራ ሳይንት

 

ቤተ አምሐራ ሳይንት


አማርኛ ቋንቋን ወልዴሽ ያሳዴግሽ፣

የአምሃራ ኩራት ሰገነት የሆንሽ፣

የጀግኖች መፍለቂያ የወሎ እመቤት ፡፣

እንዴት ነሽ ሀገሬ አምሃራ ሳይንት።

ሆርሞ ጭላጋ ታቦር አምባፈሪት፣

እንደት ነሽ ሀገሬ ቄታ መሀል ሳይንት።

ምን ነበር የሰራሽ አገራችን በፊት፣

በጠያቂ እጦት ስትሰቃይ የኖረች አምሓራ ሳይንት

 

አምሓራ ሳይንት ለብዙ ዓመታት “ወንዝ የሚሻግራት” መሪ አጥታ ቆይታለች።  የአመራር ድክመቶች ሁሉ ምንጭ የመሪ ጉድለቶች ብቻ የሆነ አድርገን መውሰድ ይቀለናል። እኛ ተከታዮች ወይም ተመሪዎች (followers) ከመሪ ያላነሰ ተጠያቂነት አለብን። መሪዎቻችን ለአመራር ስኬት ብቸኛ ተወዳሽ መሆን እንደሌለባቸው ሁሉ ለአመራር ጉድለት ብቸኛ ተጠያቂ መሆን የለባቸውም። የመሪው ጉድለት መኖሩ ብናረጋግጥ እንኳን መሪው ብቸኛ ተጠያቂ ላይሆን ይችላል። ለአምሓራ ሳይንት ኋላቀር እድገት መሪና ተመሪውም ናቸው።  

መጥምቀ መለኮት ሳሌዳ ዮሀንስ

                

መጥምቀ መለኮት ሳሌዳ ዮሃንስ ቤተክርስቲያን አምሓራ ሳይንት


በደቡብ ወሎ ዞን በአምሐራ ሳይንት ወረዳ በ04 ቀበሌ ልዩ ስሙ ሳሌዳ በሚባል አካባቢ ከዞኑ ርአሰ ከተማ ደሴ 185 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንድሁም ከወረዳው ከተማ አጅባር በምስራቅ አቅጣጫ 5 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ጥንታዊ ደብር ነው፡፡

ላች ዝም አንልም

BY: Desalew Zelalem


ለማን አቤት እንበል ማንስ ይሠማናል

ጩህታችን በዝቷል

ድምጻችን ተቀብሯል

ከወረዳ አስከዞን በኛ ይሳለቃል

ሳይንትን ሴሏቸው ልባቸው በትቤት

ጆሯቸው በክህደት ሙሉ ይደፈናል

ለማን እንጩህልሽ አንች ውደ ሃገሪ

የታሪክ መዘክር መሠረቴ ክብሪ

የሙህር መፍለቄያ የነገስታት ሃገር

እየጠባሽ አድጎ ታሪኩ እስኬቀየር

ላች እሜጮህ ጠፋ ስላች እሜናገር

።።።።ላች ዝም አንልም።።።።።

        

Tuesday, 2 February 2021

ዋና አዘጋጅ


አንዱዓለም አስናቀ 
 ዋና አዘጋጅ

አንድን ንባብ ስናነብ ያንን ያነበብነውን ነገር ለሌሎች ማካፈል   እንዳለብን ይሰማኛል። እንደዚህ ስናደርግ በአንድ ጎኑ ራሳችንን እያስተማርን የእውቀት መጠናችንን በብዙ እጥፍ እየጨመርን እና ለሌሎች የማካፈል ማሕበራዊ ግዴታችንን እየተወጣን ነው፡፡ የዚህ ተግባር እና ውጤቱ ደግሞ የውስጥ እርካታና ደስተኛነት ነው፡፡

ስለሆነም ይህ የጡመራ ድረ ገጽ  (Web-Blog) በአዘጋጁ የግል ጥረት የተሰራ (ዲዛይን) የተደረገ ሲሆን ዋና አላማውም ጸሃፊው ከተለያዩ መጽሃፍት፣ ድረገጾች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች በተለያየ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያገኛቸውን መረጃዎች፣ እውቀቶችና ክህሎቶችን በአንድ ድረ ገጽ  በማሰባሰብ  ታሪካዊ፣ ተፈጥሮአዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጅን መሰረት ያደረጉ ጉዳዮች  በአንድ ላይ ለማስቀመጥ ታስቦ የተሰራ የጡመራ ገጽ ነው። 

እናንተም የጦማራች ቤተሰብ በመሆን  ገጻችንን  ውድድ( follow) የተሳሳትነውን እርም እያደረጋችሁ የሚሻሻል እና የሚበረታታ ነገር ካላችሁ ሀሳብ እና ጥቆማችሁን ከጦማራችን  የአስተያየት መስጫ ሰሌዳ (Feed back box) ላይ አስተያየታችሁን    ይላኩልን። እናመሰግናለን!!!


አንዱዓለም አስናቀ 
(የ'የሽወርቅ ልጅ)

 

ይከተሉን

የጦማር ድረገጽ: 
የአንዱዓለም እይታዎች
https://andualemasnake.blogspot.com/

የፌስቡክ ገጽ: 
Andualem Asnake (የ'የሽወርቅ ልጅ)
 https://www.facebook.com/andualem.asnake.33 

Sunday, 31 January 2021

አምሓራ ሳይንትን ፍለጋ

  



🔴 ስያሜ

᪥᪥᪥᳀᪥᪥᪥

አምሐራ የሚለው ስያሜ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሲሆን  ታሪካዊነቱን አስቀጥሎ  አምሓራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ ተብሎ ተሰይሟል ፡፡  

Saturday, 30 January 2021

አምሓራ ሳይንት የሚለው ስም

 የአምሐራ ሕዝብ የዘር ሀረግ ፣ የተድባበ ጽዮን አመሰራረት እና አምሐራ ሳይንት

======= ======= =======

ዘመናት ተነባብረው ሰማ ሰማያት የሚደርስ የእድሜ ክምር ቢሰሩ ታሪክ የበለጠ ያደምቁት እንደሆነ እንጅ አያደበዝዚትም፡፡ታሪክም የክንዋኔ ወቅቱን እያሰላ እና እየቀመረ ልደትና ህልፈትን በየተራ እየመዘገበና እያፈራረቀ በገቢረ ተቃርኖ አንዱ የሌላውን ሁነት እያጎላ የሚሔድ በመሆኑ በሂደት የሚገጥመው ውጥንቅጥ ባህሪ ለውበቱ ተጨማሪ ድምቀት ይሰጠዋል፡፡

Friday, 1 January 2021

Borena-Sayint National Park


Borena-Sayint National Park (formerly known as denkoro Chaka state reserve) is found in the central Amhara development corridor of Ethiopia, which is about 600km from Addis Ababa through Debre Birhan, 300km from Bahirdar through Merto Lemariam and 200km south west of Dessie. Borena-Saynt NationalPark is sharing a boundary with Borena, Mehal Saynt, and Saynt woredas.Most part of the park is found in Borena wereda. It is bordered by Nine kebeles in the side of Borenawereda namely, Miskabie, Fati-Janeberu, Abu-Aderie, Jelisa-Jibanos, Anferfra, Chero-Cherkos, Chiro-Kadis, Dega-Dibi, and Hawey-Betaso. It also shares a common boundary with three Kebeles(namely Kotet, Wejed, and Samayie) from Mehal Sayntwereda and one kebele (namely Beja-Chilaga)in the side of Saynt wereda.