Wednesday, 1 September 2021

ሀብታም ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?


የስኬት ንድፍ (Success Blueprint) 

ሀብታም ለመሆን የሀብታሞችን ባህሪ መላበስና የድሆችን አመለካከት ደግሞ ማስወገድ ያስፈልጋል። በዚህ ፖስት ብዙ ሰዎችን በድህነት ቀፍደው የሚያስቀሩ ስድስት የድህነት ባህሪያትን እንመለከታለን፤ ምክንያቱም የስኬት አንዱ መሰረት የውድቀት መንስኤዎችን ለይቶ ማወቅ ነው። እነዚህ ስድስት ባህሪያት የሚተገብራቸውን ሰው ሀብታም፣ የማይተገብራቸውንም ደግሞ ድሃ የሚያደርጉ ናቸው፣ ስለሆነም እነዚህ 6 ልማዶች ሀብታም እንዲትሆን ይረዱሃል ማለት ነው። የውድቀት መንስኤዎችን ለይተን ስናውቅ እግረ መንገዳችንን የስኬት መሰረቶችንም እንማራለን።

እኛ የሰው ልጆች በርካታ ልማዶችና ባህሪዎች ያሉን የልማድ ፍጥረታት ነን። እናም አብዛኞቻችን በድህነትና በተለያዩ እዳዎች ውስጥ እንገኛለን። ምን አይነት ልማዶች ናቸው እንድንደኸይና ከዚያም አልፎ እዳ ውስጥ እንዲንገባ ያደረጉን? ገና ስላልተከፈሉ እዳዎች፣ ስለ ክሬዲት ካርድ ክፍያ፣ ስለ ብድር፣ ስለ ቤት ኪራይ ክፍያ፣ ስለ ኤሌክትሪክና የውሃ አገልግሎት ክፍያ ወዘተ የመጨነቅ አዙሪት ውስጥ የገባነው እንዴት ነው? ይህ ሁሉ የልማዳችንና የድህነታችን ውጤት ነው። ልማዳችን ቢስተካከል አንደኸይም ነበር፣ ቢኖር ስለብድር አንጨነቅም ነበር። ቶማስ ሲ ኮርሊ በዚሁ ዙሪያ ያደረገውን ምርምር እናነባለን።

የዛሬ አመት ሆነህ የምትገኘው በየቀኑ የምታደርጋቸውን ልማዶች ስብስብ ውጤት ነው። አንተ የልማድህ ውጤት ነህ። አንብብ፣ ማንበብ የስኬትህን ምስጢር የምታገኝበት ምክንያት ሊሆን ይችላል...

ኮርሊ ሚሊየነር የሆኑ ሰዎችን ለአምስት ዓመታት ሲያጠና የቆየ የፋይናንስ እቅድ አውጪ እና ደራሲ ነው። ሆኖም ስለ እብታሞቹ የኢንቨስትመንት ስልት ለማወቅ ፍላጎት አልነበረውም። ነገር ግን እንዴት እንደሚኖሩ፣ የሚከታተሏቸው የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ምን እንደሆኑ፣ አዘውትረው ምን እንደሚመገቡና ምን እንደሚያነቡ የበለጠ ለማወቅ ፍላጎት ነበረው። እነዚያ ልማዶች ሀብትን በመገንባት ረገድ ትክክለኛ አክሲዮኖችን መርጦ ኢንቨስት የማድረግን ያህል ጠቃሚ እንደሆኑ አውቋል። 

ኮርሊ በዓመት ቢያንስ 160,000 ዶላር ያልተጣራ ገቢ የሚያገኙና 3.2 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት ያላቸው 233 ሰዎችን ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር። እናም 177 የሚሆኑት አብዛኞቹ ሰዎች በራሳቸው ጥረት ታግለው ሚሊየነሮች የሆኑ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ሀብትን ለማካበት አስፈላጊ የሆኑ ልማዶች እንዳሏቸው ግልጽ ነው፤ ነገር ግን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎችስ ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ ነበራቸውን?

ኮርሊ በጠቅላላ አመታዊ ገቢ 35,000 ዶላር ወይም ከዚያ በታች የሚያገኙ እና 5,000 ዶላር ወይም ከዚያ በታች የሆነ liquid asset (በቀላሉ ወደ ጥሬ ብር ሊቀየር የሚችል ንብረት) ያላቸው 128 አሜሪካውያንንም ቃለ መጠይቅ አድርጓል።

እናም ጥናቱ ሀብታም ሰዎች፣ የአበልፃጊ ልማዶች ባለቤት መሆናቸውን ያሳያል። ከነሱም መካከል ሁልጊዜ ያነባሉ፣ አስተማሪ ንግግሮችን ያዳምጣሉ፣ በየቀኑ ከአንድ ሰአት በላይ ቴሌቪዥን አይመለከቱም፣ የሚመገቡትን የካሎሪ መጠን ይቆጣጠራሉ፣ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፣ እንዲሁም ጥርሳቸውን ሁልጊዜ ይቦርሻሉ። 

የአፍን ጠረን መጠበቅና የባንክ አካውንትን ማሳደግ ምን ያገናኘዋል ታዲያ ልትለኝ ትችላለህ። ጥርስን መቦረሽ ስነስርዓት መያዝን ወይም የስነምግባር መመሪያን ማክበርን ያመለክታል። እንደዛ አይነት የመርህ አክባሪነት ባህሪ ከሌለህ፣ ኮርሌ "የድህነት ልማዶች ወይም “poverty habits” የሚለው ልማድ አለብህ ማለት ነው። 

ቀጥለው ሰዎችን “ለብልፅግና ወይም ለድህነት የሚዳርጉ ተመሳሳይ ልማዶች / ባህሪያት ተዘርዝረዋል። እነዚህን ልማዶች የተገበረ ሰው ስኬታማ ይሆናል። ያልተገበረ ደግሞ በድህነት ውስጥ ይኖራል። በነዚህ 6 ልማዶች ዙሪያ ሀብታሞችና ድሆች ምን አይነት እርምጃ እንደሚወስዱ እያነፃፀርን እናያለን። 

1. የመዳረሻ ግብ አስቀምጥና ግብህን ለማሳካት በእቅድ ተመራ (Set a goal and plan how you will achieve it)

ሀብታሞች ግብ ይነድፋሉ። ብዙ ስኬታማ ሰዎች በእያንዳንዷ ቀን፣ ሳምንት፣ ወር እና አመት ምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ግባቸውን በግልጽ አስቀጠው ነው የሚንቀሳቀሱት። ስለዚህ ህልማቸው ግልፅ ስለሚሆን የዛሬ 20 አመት የት መድረስና ምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ቢጠየቁ ያለችግር መናገር ይችላሉ። 

በአንጻሩ ድሆች ደግሞ ምንም ግብና እቅድ ሳያወጡ ነው የሚኖሩት። ግብ ያወጣን ቢመስላቸውም በትክክል አያወጡትም። ኮርሊ “ጥናት ካደረኩባቸው ድሆች 95 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የህይወት እቅድ አልነበራቸውም። የሚንቀሳቀሱትም ያለምንም ፕላን ነው። የረጅምና ያጭር ጊዜ ግብ የሚባል ነገር እነሱ ጋ አይታወቁም። ያለምንም ግብ የምንኖር ሰዎች፣ ያለ ዓላማ በምድር ላይ ስንገዋለል እንኖራለን።” ሲል ጽፏል። እቅድ ለማውጣት ሀብታም መሆን አይጠበቅብህም፣ ሀብታም ለመሆን ከፈለክ ግን እቅድ ማውጣት የግድ ይልሃል።

እቅድ የማውጣት ጥቅሞች

እቅድ ማውጣት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 

እቅድ ማውጣት ማለት ምን ማድረግ እና እንዴት ማድረግ እንዳለብን ቀድመን ማሰብ ነው። አስበንና አቅደን የሰራነው ነገር ደግሞ ብዙውን ጊዜ ውጤታማ ያደርገናል። 

እቅድ ማውጣት አንድ አቅጣጫ ይዞ ለመጓዝ ያስችላል። እቅድ ሳናወጣ በምንቀሳቀስበት ጊዜ አቅጣጫችን ይዘበራረቃል፣ ተግባራችንም የተሰላና ሀይል ያለው አይሆንም። በእቅድ ስንቀሳቀስና አንድን ነገር በእቅድ ስንሰራው ጥሩ አድርገን የመስራት እድል ይኖረናል። Planning allows you to move in one direction. When we do not plan, our direction will be distorted, and our actions will not be calculated and powerful. When we plan and do something in advance, we have the opportunity to do well.

አንድ ሰው ስራ ሲጀምር ያልጠበቃቸው ለውጦች እና መሰናክሎች ወደፊት ሊያጋጥሙት ይችላሉ። እናም እቅድ ማውጣት ለእነዚህ ችግሮች ቀድሞ እንዲዘጋጅና እነሱን ለመቋቋም ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ያስችለዋል። 

የእያንዳንዱ ግለሰብና ተቋም የስራ አፈጻጸም ሊለካ የሚችለው በእቅድ ነው።

አስቀድሞ እቅድ ማቀድ አስተሳሰባችንና ድርጊታችን ግልጽ እንዲሆን ያደርጋል። ስራውን ያለምንም ግራ መጋባት፣ በተቃና ሁኔታ ለማከናወን ያስችላል። (Planning ahead clarifies our thoughts and actions. It allows you to get the job done smoothly and successfully.) እቅድ የማጣት አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት በጣም ብዙ ነው። 

2. ገንዘብህን አታባክን  (Don’t overspend) 

የሚያገኙትን ገንዘብ እየቆጠቡ ኢንቬስት ማድረግ ሀብት ለመገንባት ቀላሉ እና አስተማማኙ መንገድ ነው። ይህ ሂደት ልክ አንድ ችግኝ ተክሎ ወደ ዛፍነት ሲያድግ እንደመመልከት ነው። ታዲያ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ችግር የሆነው የሚተከለውን ችግኝ ማግኘት አለመቻል ነው።

ገንዘባችንን ከልክ በላይ የምናወጣበት ብዙ ምክንያቶች አሉ። ምናልባት፣ ገንዘብ የምናወጣበትን ዋነኛው ልማዳችን የትኛው እንደሆነ ለይተን ላናውቀው እንችላለን፤ ሆኖም ራሳችንን በአንክሮ ከፈተሽነው ሁል ጊዜ ገንዘብ ባገኘን ቁጥር ብዙም ጥቅም የማይሰጡ ውድ ውድ እቃዎችን እየገዛን ይሆናል፣ ከፍተኛ የሆነ የመጠጥ፣ የሲጋራና የጫት ሱስ ሊኖርብን ይችላል ወይም በሌላ በማንኛውም ጎጂ ምክንያት ብዙ ገንዘብ ልናወጣ እንችላለን። 

ብዙውን ጊዜ ገንዘብ ከመጠን በላይ የሚያወጡ ሰዎች መድሃኒቶች ላይ ጥገኛ የሆነ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ናቸው። በደበራቸውና በጨነቃቸው ጊዜ ሁሉ፣ ወይም ከሰው ጋር በተጋጩ ቁጥር ከዛ ስሜት ለጊዜውም ቢሆን ለመገላገል፣ የፈጀውን ያህል ገንዘብ አውጥተው የሚያነቃቋቸውን ነገሮች ይወስዳሉ። 

ብዙዎች ጓደኞቻቸውን ለመማረክ ወይም በይሉኝታ ተይዘው በየ ምግብ ቤቱ ላገኙት ሁሉ በመጋበዝ፣ መጓጓዣ ላይ ላገኙት ሁሉ ሂሳብ በመክፈል፣ ተበድረው ለማይመልሱ ሁሉ ገንዘብ በማበደርና እቃ በማዋስ፣ ወይም ለታይታ ውድ ውድ ልብሶችን እየለበሱ በመውጣት፣ ውድ የቤት ዕቃዎችን በመሰብሰብና ውድ መኪናዎችን በማሽከርከር ብዙ ገንዘብ ያጠፋሉ። ውሎ አድሮም የባንክ ሒሳባቸው ከጠበቁት በላይ ሲያሽቆለቁል ያስተውላሉ። 

“በየሳምንቱ ገንዘብ ቆጥብ፣ የመጠኑ ጉዳይ አያሳስብህ፣ አነሰ ብለህም አትናቀው፣ ብቻ ዝም ብለህ ያገኘኸውን ቆጥብ።” 

እ.ኤ.አ. በ 2018 የፌደራል ሪዘርቭ ሪፖርት ባደረገው መሠረት ከ 10ሩ ሰዎች ውስጥ 4ቱ ለአደጋ ጊዜ የሚፈለገው ገንዘብ ይቅርና የ400 ዶላር ወጪን እንኳን መሸፈን እንደማይችሉ አረጋግጧል።  ስለዚህ እዳዎን ከፍለው ለመጨረስም ሆነ ለመቆጠብ በቂ ገንዘብ ከሌልዎት፣ አንደኛ የሚያገኟትን ትንሽ ገንዘብ በጥንቃቄ ይጠቀሙ፣ ይህ ባህሪ ብዙ ገንዘብ በሚያገኙበትም ወቅት ቆጥበው የመጠቀም ልማድን እንዲያዳብሩ ይረዳዎታል። ሁለተኛ ተጨማሪ ገንዘብ የሚያገኙባቸውን የስራ አማራጮች ይፍጠሩ። ይህ ደግሞ ወደ ቀጣዩ የሀብታም ሰዎች ባህሪ ይወስደወታል። 

3. ተጨማሪ የገቢ ምንጮችን ይፍጠሩ

የአሜሪካ የህዝብ ቆጠራ ቢሮ በ2019 ይፋ ባደረገው መሰረት፣ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የገቢ ምንጭ ያላቸው ሴቶች 8.8% የሚሆኑት ሲሆኑ ከወንዶች ደግሞ 8% የሚሆኑት ብቻ ናቸው። ኮርሊ ደግሞ 65 በመቶ የሚሆኑት ሀብታም ሰዎች የመጀመሪያውን 1 ሚሊዮን ዶላር ከማግኘታቸው በፊት ቢያንስ ሶስት የተለያዩ የገቢ ምንጮችን እንዳቋቋሙ አረጋግጧል። 

ኮርሊ “ድሆች አንድ የገቢ ምንጭ ብቻ ያላቸው ሲሆን ሁሉንም እንቁላላቸውን ባንድ ቅርጫት ያስቀመጡ ናቸው።” ይላቸዋል።

ስለዚህ፣ ዕዳ ውስጥ ካለህ ወይም በቂ የገቢ ምንጭ ከሌለህ፣ ቲቪ መመልከትህን አቁም፣ ከሰዎች ጋር በየካፌውና በየቦታው እየተሰበሰብክ የምታጠፋሁን ጊዜ ቀንስ፣ ከዚያ ይልቅ ብዙ አንብብ፣ ብዙ ትምህርቶችን አድምጥ፣ እቅድ አውጣ፣ አዎንታዊ አመለካከት አዳብር፣ ሙያ ተማር፣ ክህሎትህን አዳብር፣ እና ተጨማሪ የገቢ ምንጮችን ፍጠር።

ሰዎች በየ በአላቱና በየ ፓርቲው ሲጨፍሩና ሲደሰቱ አንተ ስራህ ላይ አተኩር። በርትተህ ከሰራህና ከተማርክ፣ በእርግጠኝነት ይሳካልሃል። ጓደኞችህ በስተ እርጅና ሲንከራተቱ አንተ የተደላደለ ህይወት ትኖራለህ። 

ብቻህን መሆንን እና ራስህን መቻልን ተማር፤ ይህ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚካኑት ክህሎት ነው። 

ተጨማሪ የገቢ ምንጮችን እንዴት መፍጠር እችላለሁ? How to create additional income streams? 

ከመደበኛ ስራህ በተጨማሪ በትርፍ ጊዜዎ የሚሰሩ ስራዎችን በመስራት ተጨማሪ ገቢን መፍጠር ትችላለህ። ሆኖም እነዚህ ስራዎች ጊዜ፣ ፅናት፣ ተጨማሪ ሙያዎችን መማርንና በርትቶ መስራትን ይጠይቃሉ። በትርፍ ጊዜ ሊሰሩና ተጨማሪ ገቢን ሊያስገኙ የሚችሉ የተወሰኑ ስራዎችን ቀጥለን እንመለከታለን። 

በመጀምሪያ ሰዎች ሊያስቡት የሚገባው ነገር ገንዘብ ለማግኘት የሰዎችን ችግር መፍታት ያስፈልጋል። ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር ስናቀርብና ችግራቸውን ስንፈታ ብቻ ነው ገንዘብ ልናገኝ የምንችለው። ካልሰረቅን በስተቀር፣ ለሰዎች አንድ ቫሊው ሳናስገኝ፣ ዝም ብለን ገንዘብ ልናገኝ አንችልም።



No comments: