Thursday, 18 February 2021

የታቦር ተራራ (አምሓራ ሳይንት)

 ታሪክን ተሸክሞ ጠያቂ ያጣ ተራራ    ታቦር - አምሓራ ሳይንት



መገኛ (Astronomical position): 

  • ኬክሮስ (Latitude)= 10°55'60" North
  • ኬንትሮስ( Longitude)=  38° 58' East

ጆግራፊያዊ ስም:  የታቦር ተራራ

ከፍታ: ከባህር ጠለል በላይ 4247 ሜትር

መገኛ (Geographical location): አማራ ክልል፤ በደቡብ ወሎ ዞን፤ በአምሓራ ሳይንት ወረዳ ከአጅባር ከተማ በስተምስራቅ አቅጣጫ በኩል  30ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

👉ታሪካዊ ሁነት እና የታቦር ስያሜ

 (በአለቃ ወ/ሃና ተክለ ሃይማኖት 1958 ዓ.ም የግዕዝ መጽሃፍ)

💢ከቅድመ ልደት ክርስቶስ 982 ዓ.ዓ

የእስራኤሉ ንጉስ ሰለሞን እና የኢትዮጲያይቱ ንግስት ሳባ


የታቦር ተራራ ስም የወጣለት የዛሬ ሶስት ሺህ አመት ነበር።  በመጽሃፍ ቅዱስ ታሪክ የምናውቃቸው የእስራኤሉ ንጉስ ሰለሞን እና የኢትዮጲያይቱ ንግስት ሳባ ልጅ ከሆነው ቀዳማዊ ሚኒሊክ ጋር ወደ ኢትዮጲያ ከመጡት የእስራኤል የበኩር ልጆች ጋር የተያዘ ታሪክ አለው ታቦር ተራራ፡፡ 

ንግስ ሳባ በጠቢብነቱ በስፋት የሚነገርለት የእስራኤል ንጉስ ሰለሞን ለመጎብኘት ወደ እስራኤል ሂዳ ቆይታ ባደረገችባቸው ጊዚያት ከንጉሱ ወንድ ልጅ ፀንሳ ነበር፡፡  ወደ ሀገሯ ስትመለስ የጠቢቡን ሰለሞን ልጅ ቀዳማዊ ሚኒሊክ ወለደች፡፡ ይህ ልጅ አድጎ ለአቅመ አዳም ሲደርስ አባቱን እንዲጎበኝ ወደ እስራኤል ትልከዋለች፡፡ ልጁ ወደ እስራኤል ሂዶ ከአባቱ ጋር ከተገናኘ በኃላ የተለያዩ የአስተዳደራዊና ወታደራዊ ጥበቦችን ከአባቱ ሲማር ቆየ፡፡

ቀዳማዊ ሚኒሊክ ወደ ሃገሩ ኢትዮጲያ ሲመለስ ንጉስ ሰለሞን የእስራኤልን የበኩር ልጆች በሙሉ ከልጁ ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ አደረገ፡፡ የእስራኤል የበኩር ልጆችም ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ጋር ወደ ኢትዩጲያ የገቡት የካህናት ዘሮች /ሌዋውያን / ወደ ኢትዮጵያ በሚሄዱበት ወቅት ብቻቸውን አልነበሩም፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ጽላት /ጽላተ ሙሴ/ እና የጽላቱ ጠባቂ ሀላፊዎች የሆኑትን የካህናት ዘሮች እና ሌሎች ነገደ እስራኤላዊያን ወደ ኢትዮጲያ ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ጋር አብረው መጡ። 

ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመጡት አስራ ሁለት ሺህ ነገደ እስራኤል መካከል ሁለት ሺህ አምስት መቶ እስራኤላውያን በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ መሪነት አምሃራ ሣይንት ገብተው ተድባበ ፅዮንን የዛሬዋ ተድባበ  ማርያምን የመሰረቱት ሌዋውያን የተድባበ ፅዮንን ስም ካወጡ በኋላ የአማራ ሣይንትን ምድር በሃገራቸው በኢየሩሳሌም አምሳል ሰይመውት ነበር። ከነዚህ  ቦታዎች መካከል የኢትዮጵያን ታሪክ ይዞ ጠያቂ ያጠው አንዱ የታቦር ተራራ ነው። የእስራኤላዊያን ዘር የሆኑት ካህናትም ወደ አምሃራ ሳይንት ገብተው የጽላቱን ቤተ መቅደስ በከፍተኛ ተራራ ላይ ሰርተው የአምልኮ ስርዓታቸውን እያከናወኑ ይኖሩ ነበር፡፡ ይህም ለ12ቱ ነገደ እስራኤላውያን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በየስማቸው የተለያዩ አካባቢዎችን ሲሰይሙ ይህንን ተራራ የታቦር ተራራ ‹‹ደብረ-ታቦር›› ብለው እንደጠሩትም መዛግብት ይናገራሉ፡፡ 

💢12ኛው ክ/ ዘመን :

በአስራ ሁለተኛው ከፍለ ዘመን የነገሰው ኢትዮጵያዊ ንጉስ አፄ ይኩኖ አምላክ በታቦር ተራራ  ከትሞበታል። አፄ ይኩኖ አምላክ የነገሰው ሐይቅ እስጢፋኖስ ሲሆን  ቤተ መንግስቱ ግን ያለው አምሃራ ሣይንት ታቦር ተራራ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። (ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ)

💢14ኛው ክ/ ዘመን:

የታቦር ተራራ በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ዮሐንስ ገብላዊ የሚባል አምሃራ ሣይንት ላይ የነበረ ሊቅ ቅኔ ደርሶበታል። ይህ ተራራ እነ አፄ ብዕደ ማርያም ቅኔ የተማሩበት ቦታ ነው ። የጎጃሙ ተዋነይ የዋድላው ልብሰ ወርቅ ቅኔ የተማሩበት የፈላስፎች መንደር የነገስታት ከተማ እንደነበር ያስረዳሉ።

👉ተፈጥሮአዊ ገጽታው ጠቀሜታው (Naturalness)

የታቦር ተራራ በደጋማው  የአምሓራ ሳይንት  ክፍል የሚገኝ ነው።  ይህ ተራራ ከፍተኛ የውሃ ጋን ከመሆኑ የተነሳ  የአባይ ወንዝ ትልቁ ገባር የበሽሎ ወንዝ መነሻ ነው። የተራራው ቅርጽ የጓሳው ውበት ልብን ያማልላል። 

የታቦር ታራራ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ በላይ ዙሪያዉን በጥርብ ገደል የታጠረ ነዉ፡፡ በመሆኑም ወደ ተራራዉ መግባት የሚቻለዉ በ2 ተፈጥሯዊ በሮች ብቻ ሲሆን ይህም ተራራዉ ራሱን የቻለ ተፈጥሯዊ እስትራቴጅካዊ  ውበትን አላብሶት ይታያል። 

በዚህ ተራራ ግርግጌ አካባቢ በሰፊዉ የሚበቅል ተፈጥሮዊ ሳር ጓሳ በብዛት ይገኛል።  ጓሳ በአይነቱ ረዘም ብሎ ከርደድ ያለ እና ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለዉ የሳር አይነት ነዉ፡፡ አስታና ጅብራ ሌላዉ በታቦር ተራራ አካባቢ የሚበቅሉ ተፈጥሮአዊ እፅዋቶች ናቸው ፡፡ 

በቀዝቃዛዉ እና በነፋሻማዉ  በታቦር ተራራ  የወፎቹ ድምፅ ህብረ ዝማሬ ፣ የቀበሮ ደፈጣና የአይጦች ሩጫ የማደን እና የመታደን እልህ አስጨራሽ የሞት ሽረት ፍትጊያ ፣ የጥንቸል ፈጣን ሩጫ ማየቱ ቀልብን ሰርቆ ልብንን ያማልላል።

ታቦር ተራራ እና አካባቢው በተፈጥሮዊ ይዘቱ የሰው ልጅን (የጎብኝዎችን) ቀልብ ሊስቡ የሚችሉ ማራኪ ገጽታዎች ያሉት ሲሆን ከተፈጥሮዊ መስህብነቱ በተጨማሪ አካባቢው ፖለቲካዊ፣ ኃይማኖታዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ እምቅ የቱሪዝም ፖቴንሻል ሃብቶችን የያዘ ነው፡፡ የዱር እንሰሳትና ዕፅዋትን ባሉበት ሁኔታና በተፈጥሮዊ አኗኗራቸዉ ለሚደረግ  ሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምር ለማካሄድ ይረዳል፡፡  በዚህ ረገድ ለሚደረጉ ምርምሮች የመስክ ላቦራቶር ሊሆን ይችላል፡፡


ENGLISH VERSION

The Lost of seekers for  Historical mountain that carries history - Mount Tabour


Mount Tabor - Amhara Saint

Astronomical position:

  • Latitude = 10 ° 55'60 "North
  • Longitude = 38 ° 58 'East
Geographical name: Mount Tabor

Height: 4247 meters above sea level

Geographical location: Amhara Region; South Wollo Zone; It is located 30 km east of Ajbar town in Amhara Saint Woreda.

👉Historical event and Tabor designation

(Geez book by Aleka W / Hanna Tekle Haymanot 1958)

💢 Before birth of Jesus Christ: 982 B.C.

Mount Tabor was named three thousand years ago. The story of Mount Tabor is the story of King Solomon of Israel and Menelik I, the son of the Ethiopian Queen of Sheba, whom we know from biblical history.

King Sheba became pregnant with King Solomon's son during a visit to Israel, where he was widely known for his wisdom. When she returned to her homeland, she gave birth to the son of the wise Solomon. When the boy reaches the age of puberty, she sends him to visit his father in Israel. After visiting his father in Israel, the son learned various administrative and military skills from his father.

When Menelik I returned to Ethiopia, King Solomon sent all the firstborn of Israel to Ethiopia with his son. The firstborn sons of Israel, who came to Ethiopia with Menelik I, were not alone when they left for Ethiopia. Menelik I came to Ethiopia with the descendants of the priests and other tribes who were in charge of the tablets that God had given to Moses.

Out of the 12,000 tribes of Israel who came to Ethiopia with Menelik I, 2,500 Israelis, under the leadership of High Priest Azariah, entered Amhara Saint and founded Zion. One of these places is Mount Tabor, which has a long history in Ethiopia. The priests, who were of Israel descent, also went to Amhara Saint and built the Temple of the Tablets on a high mountain and performed their rites. Records show that they named Mount Tabor "Debre Tabor" in memory of the 12 tribes of Israel.

💢 12th century:

Emperor Yikuno, an Ethiopian king who ruled in the twelfth century, was buried on Mount Tabor. According to historians, the lake was ruled by Emperor Stephen, but the palace was located on Mount St. Tabor in Amhara. (Professor Abba Wolde Tinsae Abate)

💢 14th century:

Mount Tabor was discovered in the fourteenth century by a poet named John Geblawi, an Amhara Saint. This mountain is the place where the emperors learned poetry. According to Gojjam actor Wadla's gold dress, the village of the philosophers was a royal city.

Nature and Naturalness

Mount Tabor is located in the upper part of the Amhara Saint. This mountain is so large that it is the source of the Nile, the largest tributary of the Nile. The shape of the mountain captivates the heart.

Mount Tabor is so high that it is surrounded by cliffs. Thus, access to the mountain is possible only through 2 natural gates, which are considered to be the most strategic natural beauty of the mountain.

There is an abundance of natural grass that grows on the slopes of this mountain. Gussa is a long-stemmed and multi-faceted herb. Astana Jibra is another natural plant that grows near Mount Tabor.

On the cold and windy mountain of Tabor, the sound of birds chirping, foxes and rats running, hunting and hunting, the sight of rabbits, and the sight of rabbits rushing to the heart.

Mount Tabor and its surroundings are fascinating in nature, and in addition to its natural attractions, the area also has political, religious, historical and cultural potential for tourism potential. Helps to conduct scientific research on the condition of wildlife and plants and their natural habitat. It could be a field laboratory for research.

ለተጨማሪ ቤተሰብ ይሁኑ

የጦማር ድረገጽ: 
አምሓራ ሳይንት የማህበራዊ ሚዲያ መረብ
https://amharasayint.blogspot.com/

የፌስቡክ ገጽ: 
Amhara Sayint Social Media Network ASSMN 

 https://m.facebook.com/amhasayint

No comments: