ቤተ አምሐራ ሳይንት
አማርኛ ቋንቋን ወልዴሽ ያሳዴግሽ፣
የአምሃራ ኩራት ሰገነት የሆንሽ፣
የጀግኖች መፍለቂያ የወሎ እመቤት ፡፣
እንዴት ነሽ ሀገሬ አምሃራ ሳይንት።
ሆርሞ ጭላጋ ታቦር አምባፈሪት፣
እንደት ነሽ ሀገሬ ቄታ መሀል ሳይንት።
ምን ነበር የሰራሽ አገራችን በፊት፣
ታሪክሽ ይነገር ይውጣ በህዝብሽ ፊት።
ያለፈውን ትተሽ አሁንም ስትኮሪ፣
ተነሺ አገራችን ታሪክሽን ንገሪ።
የመቃና ዉቅር ዕዋና አምባፈሪት፣
እንዴት ናት ተዲባበ የጥንቷ አዲባራት።
ዕዋ መጀን ብለው አበው ሲመርቁ፣
መረዳዳት እንጅ ክፋት የማያውቁ።
ዝናሩ ትራሱ ምንሽሩ ጌጡ፣
አምሃራ ሳይንት የወሎየ ፈርጡ።
ዲሂት ዋርካ ጉል ሜዳ እንደምን ነው ዋሮ፣
ያ ያትክልቱ ቦታ የተክልየ ጓሮ።
ተክልየ ፀበሉ ተባርኮ በጃቸው፣
ይፈወሱበታል ዛሬ ልጆቻቼው።
አገሬን ሳልዞራት እኔ አልመለስም፣
ዋካ ሚካኤልን ወፍ አምጭ ማርያም።
ጨፈርፈሬ ማርያም ያለች በሽሎ ዳር፣
ሰው ተፈቃሪ ደግየ ገራገር።
በጥርብ ገደል ላይ በተዓምር የቆመ፣
ዋካ ሚካኤል ነው ሁሉን ያስደመመ።
ልዝለቅ ሸንጎ ደፈር ከትልቁ ሚዳ፣
የዮሀንስ ደብር እንዴት ነው ሳሌዳ።
አልሄዲም በግምት ሳላቅ አገሩን፣
የሳታቡይ ገብሬእል እያዬሁ በሩን።
እስኪ ልወዝወዘው እኔም ትንሽ ላዝግም፣
ጉሬዛ ጊወርጊስ ታቦታቱን ልስም።
ተድባበ ማርያም ማዶ አለች አሉ ደብር፤
ኢየሩሳሌም ነች የታሪክ ምስክር።
ያፄ የኩኖ አምላክ የያኔው ቤተ መንግስት፤
ያማርኛ ቅኔ የተዘረፈበት፤
ታቦር ተራራ ነው ወሎ አማራ ሳይንት።
የጤፍ የማሽላ የፍራፍሬ አገር፤
እንደምን ይረሳል የጭቅማ ነገር፤
አያልቅም ታሪኳ ቢነገር ቢዘከር።
እስኪ አሸንጋ ልዝለቅ ልየው አገሩን፣
አጅባር ከተማዋን ነሆር ሜዳውን፣
መቸም እግረኛ ነኝ ልሄድ ልገስግስ፣
ከሜዳዉ ሚካኤል ለንግሱ ብደርስ።
የዷጡ ሚካኤል አንተ ጠብቀኝ፣
እበርህ ለቆምኩኝ ሰው በክፉ አየኝ።
ፆለቴን ነግሬ ለዷጡ ሚካኤል፣
መድረሻየ ሆነ ሰንጓጓእሩፋኤል።
የጎበዞች አገር የነመሪ ጌታ የነቀሳዉስቱ፣
የነመህምር አገር የነሊቃውንቱ፣
የዋሰልገኝ ማርያም እንዴት ናት ደብሪቱ።
ድሮ የምትባል የመገሻ አድባር፣
እንደት ናት አገሬ እንደት ናት አጅባር።
እኔስ አይደክመኝም ልዙር ልገስግስ፣
ታሪክ ታለው አገር ጭቅማ ቂርቆስ።
ልሻገረው ማዶ አባ ሩፋኤል፣
አዲሱ ደብራችን እንደት ነው ገብርኤል።
ቦታው የቅዱሳን የጥንት የመነኩሴ፣
ትጠብቀናለህ ያዉሻሹ ስላሴ።
ጉዞየን ልቀጥል መቸ ያልቃል እና፣
የጎበዞች መንደር ማጎር ከሽመና።
እስኪ ልዝለቅ እና እናቴን ልያት፣
አትሮንሰ ማርያምን ታልሳለማት።
እምቧጮ ተጠርቦ በር አይገጠም፣
ይሄው ዛሬ መጣሁ ከአትሮንሰ ማርያም።
መንገደን ልቀጥል ጉዞ አይደለም ወይ፣
ማይስ የእግዜር ድልድይ አህዮ ዴባይ።
እንደት ነው ባቼታ አሰፍ ዘመር ሷና፣
ባንድ እንተባበር አገራችን ትቅና።
ገብርኤልን ለመሳም ድንቻ ሳልደርስ፣
ገባሁ ክርስትና ሰጠቃ ቄርቆስ።
ወቂት ኪዳነ ምህረት እነጎራዳ በር፣
የመነኩሴወቹ የድንግላን አገር።
ይህንን ብናገር ሀቅ አይደለም ወይ፣
ምርት እሚታፈሰው አህዮ ደባይ።
እንደት ናት ቀንጠፊት ዘንጎድ ለምለሚቱ፣
ሁሉ የሚስማማው ለሰው ለእንስሳቱ።
እንደምነው ቆተት ደራው መጥቅ አፋፍ፣
የንብ ውሃ ጊወርጊስ ሁሉም ሲሰለፍ፣
ዘቃን ለመመልከት ወረዲኩኝ አፉፍ።
ልመለሰው ዳዳ ተክልየን ልያቸው፣
ዘንዶውን ያጠፋ ቅዱስ አባት ናቸው።
ልለፍ ወዴ ሳይንት ለንጎጡ ስላሴ፣
የሚፈጠርበት ጳጳስ ከመነኩሴ።
ልሻገር ግራሪያ ልበለው ፈልሰስ፣
ታሪካዊ ቦታ አለ አሉ አጤዳሳ።
እስኪ ልውረድ እና ልጎትን ልያት፣
ከቀደሙት ደብር አንዷም እሷ ናት።
አገሬን ሳልዞራት እኔ አልመለስ ፣
ፈረስ መጋለቢያው የወርዛ እየሱስ።
እኔስ ተመልሼ ልሻገር ነው ማይስ፣
ታሪኩ አልተወራም እስካሁን ድረስ።
የነብላታ አገር የነደጅ አዝማቾች፣
ወንዙ ማን ይባላል ከደብሩ በታች።
እኔም እሄዳለሁ ከማንም አላንስም፣
ያገርቱን አቡነ አቢብ ጥንታዊውን ልስም።
እስኪ ልዝለቅ ዲማ ልየው አገሩን፣
የፍታለ ማርያም የዋይ ገብርኤልን።
ልመለሰው ቤጃ አያዋጣኝም፣
ቅዲሲቲቷ ደብር ማርያምን ሳልስም።
ከባርሔ ማርያያም ከጓሳው ስር ሆኘ፤
ልቤ ታች ጓሜዳ ሸፍቶ ተገኘ።
በጀግኖቹ ቦታ እስኪ ልገስግስ፣
ልሻገረው ማዶ ዶቃ ጊወርጊስ።
ልመለሰው ዴንሳ አድሱ ወረዳ ፣
በይ ሀገሬ ልሚ ባንድ እንረዳዳ።
እስኪ አድስ አምባ ላይ አለች አሉ ደብር፣
የተማሪዎቹ የነመምህር የነመሪ ጌታ የነሊቃውንቱ፣
እንደምን ነው ዋሮ ያለቃወቹ አገር የነቀሳውስቱ፣
የሚካኤል ደብር የነመኳንቱ፣
የማርያሟ ደብር ታየች የጎሊቱ።
ያሰብኩበት ሳልደርስ እኔ መች ደክሜ፣
ወዠዲ ዮሀንስን በቁም ተሳልሜ፣
አስቀድሳለሁኝ ቀርነ ማርያም ቆሜ።
ልመለሰው ደራው አቦየ ገዳም፣
ትጠብቀኛለች ታች ደንሳ ማርያም።
የታች ደንሳ ማርያም እምየ እመቤቴ፣
ጉዞየን ሳልጨርስ አይደክምም ጉልበቴ።
እስኪ ልሰናበት ልሂድ ወርቅ ማውጫ፣
እንደምናት ወይለት የፍቅር መቋጫ፡።
እዋ አምባ ፈሪት ስር የተወለደው፣
ብላታ ገባ አሉ ወይለት ከሜዳው።
እንደት ነው አቡነ አቢብ አፅሙ ያረፈበት ታላቁ ደብር፣
የናለቃ አበበ የነመምህር።
በሉ እንግድህ ሰዋች ልዝለቀው ቀይ ዋሻ፣
አገራችን ትልማ እስከመጨረሻ።
እስኪ ልግባ እጫካው ከደንቆሮ ዋሻ፣
ብንሄደው ብንዞረው የለውም መድረሻ።
በይ አማራ ሳይንት ተነሽ ከመኝታሽ፣
እንዴፅጌረዳ ይጣፍጥልን ሺታሽ።
እስኪ እምየ ተነሽ አንችም ተመከሪ፣
ያለፈውን ታሪክ ለልጆችሽ አውሪ።
በራስ መንገሻ ጦር ጣሊያንን ስተወሪ፣
እንደት ነበር ያኔ ታሪክሽን ንገሪ።
ከበረሀ ቆላው ደጋውን ጨርሸ፣
ትዝ አለኝ አንድ አገር መጣሁ አስታውሸ፣
አጓማሪያም መጥሪያ ዲናባ ቂስማርያም ጓሜዳ ዴርሼ።
መለሳንቃ በሩ ደብረ ጊወርጊስ፣
ታሪኩ እማይጠፋ እስካሁን ድረስ።
ቅድስቲቷ ደብር ዋሰልገኝ ማርያም፣
ከእንግዲህ ቢቀረኝ እኔ አልታማም።
ከበሺሎ ተነስቶ ዴንቆሮ ድረስ፣
አምሃራ ሳይንት ሁሌም ትወደስ።
አለጎና ማርያም ዘቃ ጊወርጊስ፣
ሾጤ ማርያም ቆተት ምስካቤ ዲረስ፣
ከለጋቦ ይዞ በጌምድር ድረስ።
አገራችን ትደግ ተባብረን እንስራ፣
ጥለን እናልፋለን የታሪክ አሻራ።
ወይ አማራ ሳይንት ዋ ከንበል ታድርገኝ፣
ምን ሀገር ቢሰፋ እንዳማራ አይገኝ።
ወለል ያለው ፊቷ ልክ እንዴ አሽንጋ መስክ፤
የሳይንት ልጅ ናት የምታውቅ የሰው ልክ።
ወይ ትንሽ በርበሬ ወይ ትንሽ ሽንኩርት፤
በምን አመካኝቶ ይገባል ሳይንት።
አምሃራ ሳይንት ጋራ ሸንተረሩ፤
አጃኢብ ያሠኛል መልከዓ-ምድሩ።
የሁሉ መታያ የሁሉ መነሻ፤
አምሃራ ሳይንት የአገር ማስታዎሻ።
from Abba Gergory Amharansis page
No comments:
Post a Comment