Labels
- #አዘጋጅ (1)
- ፩. ታሪክና ህብረተሰብ (11)
- ፪. የህይወት ክህሎት (7)
- ፫. ነጻ ሃሳብ (6)
- ፬. ቤተ-አምልኮ (22)
- ፭. ኪነ-ጥበብ (9)
- ፮. ውብ ሀገር (8)
- ፯. አገራዊ ጉዳዮች (2)
- ፰. ሳይንስና ቴክኖሎጅ (ሳይቴክ) (13)
- ፱. ንግድና ኢኮኖሚ (9)
- ለቤተ-መፅሃፍትዎ (5)
- ስራ-Vacancy (1)
- የጉዞ ማስታወሻ (1)
Saturday, 19 February 2022
Sunday, 28 February 2021
አድዋ በኪነ ጥበብ ሰዎች
የአድዋ ድል የጥቁር ህዝቦችና የመላው አፍሪካ ኩራት ነው። ከዛሬ 125 ዓመታት በፊት ፋሺስቱ የኢጣሊያ ጦር ባህር ተሻግሮ፣ ድንበር ጥሶ በመጣ ጊዜ ጀግኖቹ ኢትዮጵያውያን ለወሬ በማይመች መልኩ ውርደትን አከናንበው ሸኝተውታል። ባልዘመነ የጦር መሳሪያ ጠላትን ለመመከት አድዋ የዘመተው የኢትዮጵያ ጦር ታላቅ ነኝ ያለችውን ኢጣሊያን ያንበረከከው አቻ በሚባል የውጊያ ስልቱ አይደለም። የዛኔ በውስጡ ከሰነቀው አይበገሬነት በቀር በቂ የሚባል ትጥቅን አልያዘም።
ያለአንዳች መጫሚያ በባዶ እግሩ ተጉዞ በሶሎዳ ተራሮች ዙሪያ ሲተም እዚህ ግባ ከማይባል ኋላ ቀር መሳሪያውና ከጦርና ጋሻው በቀር ጠንካራ መከላከያ አልነበረውም። አባቶቻችን ትናንት በከፈሉልን መስዋዕትነት ዛሬ ላይ ቆመን የምንመሰክረውን አኩሪ ታሪክ ጽፈውልናል። በእነ እምዬ ምኒልክ ደምቆ የታተመው ጀግንነትም ከሀገራችን አልፎ ለጥቁር አፍሪካ ህዝብ የነጻነት ምልክት ሊሆን በቅቷል።
መላው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ቀንበር በወደቀበት ዘመን ኢትዮጵያ «እምቢኝ» ስትል ታላቅ የተጋድሎ ዋጋ መክፈሏን ዓለም ያውቀዋል። ይህ መሆኑ ደግሞ ዛሬ እንደሌሎች ሀገራት የነጻነት ቀኗን ሳይሆን የድል በአሏን ለማክበር ግንባር ቀደም አድርጓታል። ይህን ተጋድሎ የውጭ ሀገራት ጸሀፍት ሳይቀሩ በበርካታ ታሪካዊ ድርሳናቸው ሲከትቡት ኖረዋል።
ከሁሉም በላይ ግን በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች እየተዋዛ ሲቀርብ የቆየው የኪነ-ጥበብ አውድ ግዙፉን ታሪክ ይበልጥ አጉልቶ ለማሳየት ታላቅ አቅምን መፍጠር ችሏል።
አድዋ በሎሬት ጸጋዬ ብዕር ዋ! አድዋ
ከኪነጥበብ ማሳያዎች አንዱን ስናነሳ ደግሞ በዋናነት የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን የስንኝ ቋጠሮ እናስታውሳለን። ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን አድዋን ባነሳበት ስንኙ የጦርነት ውሎውንና የተገኘውን አኩሪ ድል ለማሳየት ሞክሯል። የአድዋ ጦርነት የኋላ ታሪክ የእያንዳንዱ ኢትዮጵዊ አኩሪ ድል የሁሉ አፍሪካዊ ደማቅ ታሪክ ነው። ይህንን ሀቅ
Thursday, 11 February 2021
ሳይንትን በግጥም
//አማራ ሳይንት//
----------✿----------
ገርት የብልህ አገር የምሁር መነሻ
ቆተት የምርት ሀገር የጤፍ መናገሻ
የበልግ ምድር ወዠድ የበያይት ጉርሻ
ቀጨዉ የማር ሀገር የጥበብ ድል መንሻ
የደንቆሮ ጫካ ያለባቸዉ ዋሻ
የብርቅየ እንስሳት ምሽግ መናገሻ
ሰንበት ብሎ ያየዉ ያንችን መዳረሻ ፡፡
Sunday, 7 February 2021
ጀግና
አትንኩኝ የሚለው የሰራ አካላቱ
ክንዱ እሳት ነበልባል ቁርጥ ያለ አሞቱ
አየናና ሜታ ወግሎ ነው እድገቱ
ደግነት ጀግንነት ደሞ ምን ቸግሮት
አምሓራ ሳይንቴው ስበር አስተምሮት
ካልነኩት አይነካም ጅንን ያለ ነው
ከነኩት አይለቅም ልክ ነብር ነው።
ፎጣ ለባሾቹ
ያገር ባለ አደራ ፎጣ ለባሾቹ
ከነኳቸው ነብር እንደ አንበሳ ቁጡ
ለአገራቸው ታማኝ ኩሩና ቅንጡ
የነጻነት አባት ነፍጠኛ ነው ፈርጡ !!
በነገራችን ላይ በእያንዳንዱ ፎጣ ስር እሳት የሚተፋ ነፍጥ እና ንፍጣሙን የሚያናፍጥ ወኔ አለ !!
ትዝታ ወ-ልጅነት
ኤቢ የማርያም ልጅ
ውሀ ቅጂ ብላ ብሰደኝ እናቴ
ወለሹን ቀዳሁት አወይ ልጅነቴ
አወይ ልጅነቴ ነፍስ አለማወቄ
ሲመጣ መሽኮርመም ሲሄድ መናፈቄ።
እያልን እያንጎራጎርን ነበር ድሮ ከወንዝ ውሀ የምንቀዳው
ወሎ ቤተ አምሐራ
ባህሌን እወደዋለሁ እኮራበታለሁ
Friday, 5 February 2021
የሰርግ ስነ ስርዓታችንና አማራ ሳይንት
ጥር ወር በአብዛኛው የሀገራችን ክፍሎች የሰርግ ወቅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በገጠሩ የህብርተሰብ ክፍል ዘንድም ይህ ወር አድስ ቤተሰብ የሚመሰረትበት ወቅት ነው በአምሃራ ሳይንት ወረዳ ም በሰርግ ወቅት በሽማግሌዎች የሚመረቁ ምርቃቶችና ከሚዜሙ ዜማዎች መካከል በጥቂቱ ፡፡
ይህ ጋብቻ ስሩ ጠለቅ ጫፉ ዘለቅ ያለ ይሁን ፣ልጅቱንና ልጁን ያልምድልን፣ጋብቻውን የአብርሀምና የሳራ ጋብቻ ያድርግልን፣ ልጅ ወሎዶ ለመሳም፣እህል ዘርቶ ለመቃም ያብቃችሁ፣ ለእማ ለአባ ለመባል ያብቃችሁ፣ ለደጀ ሰላሙ ለስጋ ወደሙ ያብቃችሁ፣ እነዚህ የተጋቡ ልጆቻችሁ፣ለዘመድ ለወገን የሚተረፉ ያድርጋቸው፣ በቦታው ደግማችሁ ደግማችሁ ዳሩበት፣ ከውሀ ጢስ ከጢስ ቀልብ ይቀጥናልና ከዚህ እርግማን ይጠብቃችሁ፣ በወንድ ልጅ ተበከሩ በማለት በዕድሜ ባለጸጎች ይመረቃል ፣፡
Wednesday, 3 February 2021
ቤተ አምሐራ ሳይንት
ቤተ አምሐራ ሳይንት
አማርኛ ቋንቋን ወልዴሽ ያሳዴግሽ፣
የአምሃራ ኩራት ሰገነት የሆንሽ፣
የጀግኖች መፍለቂያ የወሎ እመቤት ፡፣
እንዴት ነሽ ሀገሬ አምሃራ ሳይንት።
ሆርሞ ጭላጋ ታቦር አምባፈሪት፣
እንደት ነሽ ሀገሬ ቄታ መሀል ሳይንት።
ምን ነበር የሰራሽ አገራችን በፊት፣
ላች ዝም አንልም
BY: Desalew Zelalem
ለማን አቤት እንበል ማንስ ይሠማናል
ጩህታችን በዝቷል
ድምጻችን ተቀብሯል
ከወረዳ አስከዞን በኛ ይሳለቃል
ሳይንትን ሴሏቸው ልባቸው በትቤት
ጆሯቸው በክህደት ሙሉ ይደፈናል
ለማን እንጩህልሽ አንች ውደ ሃገሪ
የታሪክ መዘክር መሠረቴ ክብሪ
የሙህር መፍለቄያ የነገስታት ሃገር
እየጠባሽ አድጎ ታሪኩ እስኬቀየር
ላች እሜጮህ ጠፋ ስላች እሜናገር
።።።።ላች ዝም አንልም።።።።።



