Thursday, 11 February 2021

ሳይንትን በግጥም

 //አማራ ሳይንት//

----------✿----------

ገርት የብልህ አገር የምሁር መነሻ

ቆተት የምርት ሀገር የጤፍ መናገሻ

የበልግ ምድር ወዠድ የበያይት ጉርሻ

ቀጨዉ የማር ሀገር የጥበብ ድል መንሻ

የደንቆሮ ጫካ ያለባቸዉ ዋሻ

የብርቅየ እንስሳት ምሽግ መናገሻ

ሰንበት ብሎ ያየዉ ያንችን መዳረሻ ፡፡

የነ ጋሻዉ ቀዬ ድኩላባር ማሩ

ፍታ ማሪያም ሰማኝ ያቀይ ዋሻ በሩ

ዉል አለኝ አገሬ አምሃራ ሳይንት ቀየዉና አድባሩ

ያን የወንድ ብቅል አያሌዉ ዘገዬን አትማ ያነሳች

ዶቃ ላይ ፍላቴን አጥና ያሳደገች

ታላቁን መንግስቴን አሽታ የፈተገች

ሠላም ነች ዎይ ሳይንት እንደምን አደረች

መመሸጊያዉ ጎደል መዳረሻዉ ልመስክ መናገሻዉ ቄታ

ጓሜዳና ዋሮ `መለስሳንቃ እዋ ሁሉም በየተርታ

ቀኝ አዝማች ደጅ አዝማች ራስ ወይ ብላታ

ለመሪ ይታጫል አጅባር ስር ፋሬታ ።

የጓሜዳ ችግኝ የበሽሎስር ነብሮች

ጭቆናን የጠሉ ለነፃነት ሟቾች

ለመለስሳንቃዉ ነፍጥ እንቁ ምስክሮች

አንበሳ ሲያንስ ነዉ ለሳይንት ወንዶች !

አሰፋ ከቤጃ በወግሎ ተሸግሮ የተክልየን ገዳም

ምስካቤን ተሳልሞ ቀርነ መርያም የድራል አዛኟን ለምኖ

ገላግለዉ አሰፋ ተሾመና ይርዳዉ ሲሰምር ህልማቸዉ

የይልፍኝን ቅቤ መጠጣት ሲያምራቸዉ

የታደሰ ሙክት ላት ሲጋብዛቸዉ

ይከትማሉ ከንቤ አሁን ምን ከዳቸዉ

አዳራሽ ከልፍኝ ነዉ ቤቱ ያጎታቸዉ

ጎጃም ላይ ጉልት አላት ቤጌምደር ርስት

ኑና ሰላም በሏት ያወቀን እናት

አይነጥፍ ለቅቤ የይልፍኟ ጓዳ ጧትም ሆነ ማታ

ለገላግለዉ ወንድም ለተሾመ ደስታ

እሱን ዝም ብየ ሌላ ምን ላነሳ

ሀይ ልበለዉ እንጅ ያን የዘቃ ጭቁኝ

ያባይ ዳር አንበሳ ያስኔ ታላቅ ወንድም ወንድ ይርዳዉ አፈሳ

ካሳና ተሾመ የሽፈሬ ልጆች ወንድማማቾቹ

ምሀል ሳይንት ደንሳ ተቀብሮ እትብታቸዉ

መለስ ሳንቃ አጅባር ስር ቢቋጭም ህልማቸዉ

ወንድ የወንድ ብቅል ነበረ ዝናቸዉ

ለምን ዝም ይባላል በክብር ይዘከር ይወሳ ስማቸዉ

የበሮዉ ምካኤል ነዉ ምስክራቸዉ

ደግሳ ሸኝታዉ ባቲ ድል ወንበራ

ዘምቶ ነበር ግራኝ ሽ ጥፋት አቅዶ ሽ ጭፍራ እየመራ

መለሰችዉ እንጅ አናጥፋ አሳፍራ

ያንች የናት እንቁ ያትሮንሷ እማወራ

አማላጅ ለምድር ስጋ ዋቢ ለሰማይ ነፍስ

መንገዱ ምቹ ነዉ ድልድዩ ያጤዳስ

ለሁሉ ተያዥ ናት እመይ ቀድስት አትሮንስ

መች ይረሳል ቅኔዉ ያድንግል ዉበቷ

የሳይንት ወጓ ባህሉ ትዉፊቷ

ያሽር ብትኑ ዝርዝር መቀነቷ

ያባየ ብልኮ የማየ እጥፍ ኩታ

የረኞቹ ፉሊጥ የነሚጡ ድርቼ

የጎረምሳዉ ፉጨት የቆንጆዎቹ እስክስታ

የእነ አባ ምርቃት የድናቦች ሆታ

ዉል ይላል ባይኔ ላይ ሰጥቶኝ ለትዝታ

ያገሬ ናፍቆቱ ህልሜ ላይፈታ

የባቸታዉ መስቀል የእንቡሃዉ ጊወርጊስ

የወርዛዉ ምካኤል የወዠድ ዮሀንስ

የፈረስ ባር አቦ የቆተቱ ጨርቆስ

እምነት ፅላያቸዉ ድዉያን ሲፈዉስ

አድስ አምባ ደብር አለጎና ማሪያም

የዳዳዉ ተክልዬ ማህሌት ቅዳሴ

ተድባ ማርያም አርፋ እፎይ ስትል ነፍሴ

በጭቅማዉ አቦ በፈዋሹ ፀበል

ጉድፌ ተጠርጎ ቀልቤ ይላል ወለል

ያሂዎ ነጭ ጤፍ ያሪግባ ስንዴ ምርት

የዋሮ ሽንብራ የድንቻ ቦለቄ

ያትሮንስ ማሽላ የገዳባስ ድንች

የጭላጋ ቅቤ የኮረጃ አስታ ማር

የእዋ ኮረፌ ያንባ ፈሪት ጠላ

ዉል ይለዋል ልቤ በሀሳብ ሲብላላ

የማየ እጅ ርቆኝ መንፈሴ ሲቁላላ

አነጀቴ ሲገረፍ በነፍቆት አለንጋ

ቀኑስ እንደት መሽቶ ሌቱስ እንደት ይንጋ

ለእንደኔ አይነቱ ሀጅ ርቆ ለሄደ ካገሩ ለወጣ

እንኳን ያባት ቀዬ እንኳን የናት ኳዳ

ጉድት ተራራዉም የቀበሮ ሜዳ

ይናፍቃል ዉርጩ ድንጋይ ኮረኮንቹ

የበረሀዉ ፍየል የደጋዉ በጎቹ

የዱር አዕዋፉ ከቤት እንስሶቹ

ግልገል እና ጥጃዉ በሬና ላሞቹ !!

No comments: