ጭቅማ (አምሐራ ሳይንት)
መንደሩ ዙሪያውን በገደል እና በገዳማት የተከበበ ሲሆን የአየር ንብረቱ ደግሞ ሞቃታማ ነው። ወደ መንደሩ ቁልቁል መውረጃ ሁለት የተፈጥሮ በሮች ብቻ አሉት። መልከአምድራዊ አቀማመጡ ደግሞ የተለያየ ቅርፅ አለው። ጭቅማ የአጅባር ከተማ ውበት ነው።
ጭቅማ ሁለት የአባይ ገባር ወንዞች ያሉት ሲሆን ስማቸውም ጭላጋ እና ደንደዋ ይባላሉ።
መንደሩ በስተምእራብ በኩል አባ ሩፋኤል እና እምነ ጽዮን ገዳም፣በስተ ደቡብ ፅጌሬዳ ባህታ ለማርያም እና ቤጃ ማርያም፣ በስተ ደቡብ ምእራብ የጉሬዛ ጊዮርጊስና አስት ዮሃንስ ሲያዋስነው በስተ ሰሜን ደግሞ ጋንጭ ማርያምና ሙዛ(ዋሻ) ስላሴ ያዋስኑታል።
ነገር ግን እስካሁን ቦታውን ለማስተዋወቅ የሞከረ አንድም አካል ባለመኖሩ ቦታው ለሙዚቃ ክሊፕ እናፊልም ቀረፃ የሚመረጥ ቦታ ሳይሆን ቀርቷል።
በአጠቃላይ ጭቅማ አፋፍ ብቅ ብትሉ አትሮንሰ ማርያምን አልፎ እስከ ጎጃም ድረስ መጎብኘት ይቻላል።
No comments:
Post a Comment