Showing posts with label ፱. ንግድና ኢኮኖሚ. Show all posts
Showing posts with label ፱. ንግድና ኢኮኖሚ. Show all posts

Thursday, 4 November 2021

ኤክሳይዝ ታክስ ምንድነው?

ኤክሳይዝ ታክስ የቅንጦት እቃዎች ሆነው ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሰረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ፣ እንዲሁም የሕብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱና ማህበራዊ ችግር የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል የተጣለ ታክስ ነው፡፡

Friday, 1 October 2021

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በበረራ

ለመካከለኛው ምስራቅ እና ለገበያዎች ቅርብ የሆነችው በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ እንደ መዝለል ነጥብ ስትሆን የኢትዮጵያ ሥፍራ ስልታዊ የበላይነትዋን ይሰጣታል ፡፡ ከኤርትራ ፣ ከሶማሊያ ፣ ከኬንያ ፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከሱዳን ድንበር ጋር የተገናኘ ድንበር ተሻጋሪ አገራት የተገነቡ ሲሆኑ ፣ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የጎረቤትዋን ጅቡቲ ዋና ወደብ ሲጠቀሙ ቆይተዋል ፡፡ ሆኖም በቅርቡ ከኤርትራ ጋር ሰላም በመፍጠር ኢትዮጵያ ለአለም አቀፉ ንግድ የአሳባንና ማሳሳ ወደብ የኤርትራን ወደቦች መድረሷን ለመቀጠል ተዘጋጅታለች ፡፡

Monday, 15 February 2021

እለታዊ የገበያ ዋጋ መረጃ www.aaminfo.gov.et አዲሱ ድረ-ገጽ

ለህብረተሰቡ እለታዊ የገበያ ዋጋ መረጃ የሚሰጥ አዲስ ድህረ-ገፅ ይፋ ሆነ

www.aaminfo.gov.et

---------------------------------------

የካቲት 05/2013 - የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት በከተማዋ ያሉ የገበያ ማዕከላትን በማስተሳሰር በተለይ ሸማቹ ማህበረሰብ ቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልክና የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም መረጃዎችን በማግኘት ግብይት ማግኘት ያስችላል ብለዋል።

በተጨማሪም የምርት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማወቅ፣ በምርቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪን ለመለየት እና ሸማቹ ህብረተሰብ በየትኛው የገበያ ስፍራ በምን አይነት ምርት በምን ዋጋ እንደሚሸጥ ካለበት ሆኖ ለማወቅ እንደማያስችል ኃላፊው ገልጸዋል።

Sunday, 14 February 2021

የጥቁር ገበያ


      ጥቁር ገበያ ምክንያት እና ጉዳት

የጥቁር ገቢያ (Black market)፤- ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ አንድን እቃ ወይም አገልግሎት መግዛትም ሆነ መሸጥ ክልክል በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ገዝቶ ወይም ሸጦ መገኘት ነው።


ለምሳሌ፤- የመሳሪያ ሽያጭ፤ የውጪ ምንዛሬ ሽያጭ፤ አደንዛዥ እጽ ሽያጭ፤ የሰው እና የሰው አካል ሽያጭ፤ እንሰሳት እና የእንሰሳት አካላት፤ ወዘተ መግዛት ወይም መሸጥ ማለት ነው።

Saturday, 6 February 2021

ኢኮኖሚያችን እድሜው የእለት ነው!

 



እኛ ሀገር የለት የለቱን ሰርቶ የሚኖረው በርካታ ህዝብ ነው! ምክንያቱም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ መደበኛ ባልሆነው (Informal economic sector) ላይ ነው ኢኮኖሚካሊ ህይወቱ የተመሰረተው! ስለዚህ የትኛውም አይነት ብጥብጥ ከአንድ ቀን በላይ ከቆየ በልቶ የማደርን ህልውና ነው የሚያሳጣው።