1- Scitable
https://www.nature.com/scitable
ዝንባሌዎ ስለ ጅኔቲክስ እና ስለሮቦት ሳይንስ ማወቅ ከሆነ እንግዲያውስ ሳይቴብል ለርሶ የተከፈተ ድህረገፅ ነው፡፡ ይህ ድህረገፅ በማበብ ብቻ በግልዎ መማር የሚችሉበት ሲሆን ልክ እንደ ት/ቤት በጋራም ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በኦንላይን ክፍል ውስጥ መማር ይችላሉ፡፡ ይህ ድህረገፅ በዓለም ላይ የሳይንስ ነክ ፅሁፎችን በማሳተም በሚታወቀው በ Nature Publishing Group ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በሌሎች ትልልቅ የሳንስ ኩባኒያዎች ስለሚደገፍ ት/ቱን በነፃ ነው የሚያስተምረው፡፡
በዚህ የኦንላይን ት/ቤት ውስጥ በ 4 ብቁ ፕሮፌሰሮች የተዋቀረ ሲሆን ተማሪዎች ለሚጠይቁት ማንኛውም ጥያቄ ከ 48 ሰዓት ባነሰ የጊዜ ገደብ ውስጥ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
2- iTunes U
https://www.open.edu/itunes/
ይህ ድህረገፅ ከ 600 በላይ በሆኑ ዩኒቨርስቲዎች የሚደገፍ ሲሆን ዓለም ላይ አሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎችን ማለትም የስታንፎርድ፣ የያሌ እና የኤም አይቲን ዩኒቨርሲቲዎችን የማስተማሪያ መፅኃፎችና ሌክቸር ኖቶች ሰብስቦ ይዟል፡፡ ይህ ድህረገፅ በተለይ ለመምህራን ትልቅ እፎይታን ያመጠጣ ሲሆን የማስተማሪያ መፅሀፎች፣ ቪዲዮዎችን እና ፈተናዎችን አካቶ ይዟል፡፡
ድህረገፁ ሰፋ ያለ ይዘት ያለው ሲሆን በውስጡ የግብርና፣ አስትሮኖሚ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ጂኦሎጂ ፣ ኬሚስትሪ እና የመሳሰሉ ሳይንሶችን በጥልቀት ይተነትናል፡፡
3- . Space.com
https://www.space.com/
ዝንባሌዎ በምድር ወጣ ስላሉ ጉዳዮች ከሆነ እንግዲያውስ ይህ ድህረገፅ የእርስዎ ነው፡፡ በዚህ ድህረገፅ ውስጥ ስለ ሌሎች ዓለማት ስለፕላኔቶች እና ከነርሱ ስለተያያዙ ሌሎች ነገሮች በሰፊው ይተነተናል፡፡ ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን፣ ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን "This Week in Space"(ሳምንቱ በስፔስ ውስጥ) በሚለው ፕሮግራማቸው ውስጥ ያስቃኛሉ፡፡
4- Scientific American
https://www.scientificamerican.com/
ስለጤና፣ ስለዝግመተለውጥ፣ እና ስለ ተለያዩ የሳይንስ ክፍሎች በሰፊው የሚተነተንበት እና ይበልጡን ለመማር ማስተማር ሂደት እንዲመች ተደርጎ የተሰራው ይህ ድህረገፅ በአሜሪካን ውስጥ በሳይንስ ምንጭነቱ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ከሆነው ከአሜሪካን ሜጋዚን ጋር በጥምረት የሚሰራ ሲሆን ወቅታዊ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩም ያቀርባል፡፡
5- Physics Central
https://www.physicscentral.com/
የፊዚክስ ሱሰኛ ኖት? እንግዲያውስ ይህ ቦታ የእርስዎ ነው፡፡ የፊዚክስ አምሮትዎን የሚቆርጥና በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ፈጣን አዕምሮ ባለቤቶች የሚመች ድህረገፅ ን፡፡ በ American Physical Society ተዘጋጅቶ የሚቀርበው ይህ ድህረገፅ ተመራማሪዎችን እና ተማሪዎችን የሚያገናኝ መድረክ ነው፡፡
የተለያዩ መረጃዎችን በemail ለማግኘት ብሎጋችንን Follow up አድርጉ ቤተሰብ ይሁኑ።
https://amharasayint.blogspot.com/
No comments:
Post a Comment