በአፄ ምኒልክና በተቀሩት ጀግና የጦር መሪዎቻቸው የሚመራው የኢትዮጵያ ወታደር በወራሪው ጣሊያን ላይ ድል ከተቀዳጀ ይኸው 125 ዓመት ሆነው። ከረጅም ዓመታት ጀምሮ የአድዋ በዓል በየአመቱ ይከበራል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንን ታላቅ የድል በዓል ያከብራል። አገሩን ከሚወደውና አዲስ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት ከሚፈልገው ጀምሮና፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከውጭ ኃይሎች ጋር በማበር ዛሬ አገራችን የምናየው ውድቀት ውስጥ እንድትወድቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለማበርከት ከበቃው ድረስ፣ ሁሉም በየፊናው ይህንን በዓል ያከብራል።