ከአምሐራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ ወደ ርዕስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም እየተሰራ ያለው መንገድ ስራ 90 በመቶ የሚሆነው የአፈር ጠረጋና ምንጣሮ ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ ስራ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዑመር እንደገለጹት ከአጅባር ተድባበ ማርያም 30ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ ስራ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በመሰራት ላይ እንደሆነ ገልጸው አስካሁን በተሰራው ስራ 23 ነጥብ 17 ኪ.ሜትር የሚሆነው መንገድ የአፈር ጠረጋና የምንጣሮ ሥራ ተሰርቶለታል ፡፡
አንደ ሰራ አስኪያጁ ገለጻ እየተሰራ ያለው መንገድ አሰቸጋሪ በሆነ መልክዓ ምድር ላይ የሚሰራ ስለሆነ
በታሰበው ፍጥነት ለመሄድ ያልተቻለ ቢሆንም እንኳን ስራው የነፍስም የስጋም ጥሪ ስለሆነ የምንችለውን ሁሉ በማድርግ እየሰራን ነው ብለዋል ፡፡
የመንገድ ጠረጋና የምንጣሮ ሥራው 90 በመቶ ይሠራ እንጅ በዚህ አመት መሰራት የነበረበት የድልድይ ግንባታ ስራዎች ወቅታዊ ችግር በሆነው የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር ምክንያት ማጠናቀቅ ያስቸግራል ብለዋል ፡፡ ስለሆነም ቀሪ ስራዎችን በ2014 ለማጠናቀቅ ታስቦ አየተሰራ እንደሆነ ነው ስራ አስኪያጁ የያስረዱት ፡፡
አቶ አሸናፊ አያይዘውም መንገዱ በሚያልፍባቸው አካባቢወዎች የአርሶ አደሮችን መሬት የሚነካ ስለሆነ በወረዳው በኩል የካሳ ክፍያ በፍጥነት እንድከፍል በማድረግ ወረዳው እገዛ እንድያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአጅባር ተድበባ ማርያም መንገድ ስራ ፕሮጀክት የአፈር ጠረጋ ስራ አሁን ላይ ከተራራው ጫፍ በተለምዶ የፊት በር ከሚባለው ቦታ ላይ ደርሷል ፡፡
ይህ ቦታ ደግሞ ከባድ ፍንዳታዎችን የሚጠይቅ እና ወደ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም አምባ ላይ ለመውጣት ወሣኝ ቦታ እንደሆነ ስራ አሰኪያጁ ያስረዳሉ ፡፡
የአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ መሰራት ቀደምት የስልጣኔ ምንጭ የሆነችውን ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያምን በማስተዋወቅ በኩል ከፍተኛ ሚና የሚኖረው ሲሆን በኣካባቢው የሚመረቱ ምርቶችን እና ወደ አካባቢው ሊገቡ የሚችሉ ምርቶችን በማምጣት በኩል አይነተኛ ሚና የሚጫወት ነው ያሉት ደግሞ የትድደበ ማርያም ቀጠና ትምህርት ሱፕርቫይዘር አቶ ፈጠነ ሲሳይ ናቸው ፡፡
እንደ አቶ ፈጠነ ገለጻ መንገዱ በታሰበው ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት እንድሰጥ የአካባቢው ህብረተሰብ የሚችለውን ሁሉ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ነው እንደሆነ ገልጸዋል ፡፡
በቦታው ተገኝተን እንደተመለከትነው የተድባበ ማርያም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ለፕሮጀክቱ ሰራተኞች የምሳ ግብዣ ፕሮግራም በማዘጋጀት በስራው ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን እና መንገዱ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ውይይት በማድርግ ለሰራተኞቹ አብሮነታቸውን አሳይተዋል ፡፡
የመንገዱ መሰራት ከዚህ ቀደም በእናቶች እና በህብረተሰቡ ላይ ሲደርስ የነበረውን እንግልት በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ለዚህም አስፈላጊውን አገዛ በማድረግ እየሰሩ እንደሆነ የተናገሩት ደግሞ የ016 ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ሞገስ አድማሱ ሲሆኑ በቀጣይም የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በፕሮክቱ በኩል የቀረቡትን የወሰን ማስከበር ችግሮች ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው ስንል የአምሐራ ሳይንት ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሰይፉ ቦጋለንና የአምሐራ ሳይንት ወረዳ መንገድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሰብስቤ ጌታነህን የጠየቅን ሲሆን ፕሮጀክቱ በወሰን ማስከበር ምክንያት ችግር አይገጥመውም፤ ለዚህም ከአርሶ አደሮች ጋር በመነጋጋር ችግሮችን እየፈታን ነው ብለዋል ፡፡ በመንገድ ጽ/ቤት በኩልም አስፈላጊው የቴክኒክ ድጋፍና እገዛ እየተደረገ መሆኑን አቶ ሰብስቤ ተናግረዋል ፡፡በአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ ስራ ፕሮጀክት ምክንያት መሬታቸወ ለተጎዳባቸው አርሶ አደሮችም ከ3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ እንድተከፈለ አቶ ሰይፉ ተናግረዋል ፡፡
በአጠቃለይ በወረዳው በሚሰሩ ሁሉም ፕሮጀክቶች ላይ በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት የሚቆም ፕሮጀክት እንዳይኖር በወረዳው በኩል አስፈላጊውን በጀት በመያዝና ግንዛቤ በመፍጠር እየሰሩ እንደሆነ አቶ ሰይፉ አስረድተዋል ፡፡
ጥር 27/2013 ዓ.ም የአምሐራ ሳይንት ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
No comments:
Post a Comment