Showing posts with label ፫. ነጻ ሃሳብ. Show all posts
Showing posts with label ፫. ነጻ ሃሳብ. Show all posts

Monday, 31 January 2022

ባርነትን የመረጠ የሚመክተው ጋሻ የሚጠጋበት ዋሻ የለውም

አንዱዓለም አስናቀ (የ'የሽወርቅ ልጅ)

የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ የሚለው  የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር እንዲዘመር እንጅ እንዲከበር በመንበረ ብልጽግናም ዛሬም አልተፈቀደም።  ስለዲሞክራሲ ብዙ ሲነግረን የኖረው መንበረ-ኢህአዴግ  የሚናገርለት ዲሞክራሲ በተግባር ሲታይ  አፈና ድብደባ እስርና ግድያ ሆኖ ቆይቷል። የግፍ አጥቢያው  ወንበረ-ብልጽግና ተግባራዊ ዲሞክራሲን ከኢህአዴግ አስበልጦ በወንበዴዎቹ በትምክተኝነት የህዝብን ሉአላዊነት በመንጠቅ  ጋዜጠኞችን  እንዲሁም የእውነት ታጋይዎችን ማሰሩን  ግድ ሆኖበታል ውርስ ነውና።  

በወያኔ ጎዳና ብልጽግና ዛሬም ውሸት ይናገራል (2.2 ቢልየን ብር) ለአንድ ህንጻ ማደሻ ይውላል። በወያኔ ዝማሬ ሁሉም ነገር ኢትዮጵያ እንዳደገች ህዝቡ ተለውጦ የድህነትን ሸማ አስፈንጥሮ እንደጣለ ህዝቡ ያሻውን መናገር እና ማድረግ እንደቻለ ዘወትር እንሰማለን፤ ግን በተግባር ግን በአስለቃሽ ጭስ ተቆልተን በጥይት እናራለን።  

በመንበረ ብልጽግና በጧትና በማታ  በዘወትር መልእክቱ  ሀገር በለፀገ ህዝብ ተለወጠ የሚል ድስኩሩን በሆድ አደር ሚዲያዎች እንሰማለን፤ እኛ ግን የቀን ስራ ሰርተን ዳቦ መግዛት ቸግሮናል፤ 30 ቀን ዘምተን የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶናል፤ በቀላጤው ወንድማችን ሸኔ  (በኦነግ) መከራችን በየቀኑ ይጨምራል።  

ዛሬም በህወሃት ችግራችን እንዲያገረሽ  እንጂ እንዲቀንስ አይፈለግም።  በመንበረ ብልጽግና ለጥቂቶቹ ሀገራችን ገነት ሆና ሲደላቸው ሲመቻቸው  ብዙሀኑ ግን በችግርና በረሀብ መማቀቁን ህይዎቱን ቀጥሎበታል። እናም ኤሎሄያችን ጩህታችን ዛሬም ያስተጋባል። ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ለፍትህ፣ ለእኩልነት ለነፃነት  እንደ ህዝብ ካልታገልክ ባርነትን ከመረጥክ የምትመክተው ጋሻ የሚ የምትጠጋበት  ዋሻ የለህም።

Wednesday, 24 February 2021

የከተማ እድገት መሰረት፤ የኢኮኖሚ ደም-ስር፤ አንገብጋቢው ጉዳያችን የሁልግዜም ጥያቄያችን መንገድ መንገድ መንገድ

"መንገድ ካሰቡበት የሚያደርስ" የሚለው ብሂል ለአማራ ሳይንት አይሰራም።  የንግድ ልውውጦቹ የተሳለጡ እንዲሆኑለት፤ አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ በጊዜ እንዲያደርስና ተጠቃሚ እንዲሆን፤ የከተማዋ ነዋሪዎች የሚፈልጉትን ሸቀጥም ሆነ ምርት በጊዜ እንዲያገኙ፣ ወረዳዋ የቱሪዝም

ሃብቷ እንዲተዋወቅና የገቢ ምንጭ እንዲሆናት፤ የህክምና፣ የመብራት፣ የትምህርትና የመሳሰሉ አገልግሎቶች ወረዳዋ  እንዲዘምኑላት፤ በጥቅሉ የወረዳዋ ኗሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እንዲሻሻል፤  የወረዳዋ ልማትና እድገቷ እውን እንዲሆን  የዘመናዊ መንገድ  ልማት (የአስፋልት መንገድ)  ህዝቡ አብዝቶ የሚጮህለት ግን እስካሁን  ሰሚ ያጣ ጥያቄያችን ነው።

Tuesday, 9 February 2021

የኢኮኖሚ ዋልታችን ግብርናችን! መልስ ለሗላቀር ግብርናችን ለአማሓራ ሳይንታችን



ለአርሶ አደሩ

****

ለአማራ ሳይንት የህብረተሰቡ ዋነኛ የኢኮኖሚያችን ዋልታ ግብርና እንደሆነ ይታወቃል። ሆኖም ወረዳዋ ራሷን በምግብ እንዳትችል እና  ግዜው የሚጠይቀውን የግብርና ልማት እንዳትከተል፣  የግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂ እንዳታገኝ ሲነፈጋት የኖረች ወረዳ ናት። አምሓራ ሳይንት የግብርናና የገጠር ልማት ስራዋ ለዘመናት ተረስቶ ከመሬት የተሻለ የግብርና የልማት ግብዓትን እንዳታገኝ   የወረዳዋ አርሶ አደሮች ከተመጽዋችነት የማያላቅቅ  ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የግብርና ዘይቤ ውስጥ እንድትሆን የተፈረደባት ወረዳ ናት። 

Saturday, 6 February 2021

ያላለቀው ልማታችን

 


ከአምሐራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ ወደ ርዕስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም እየተሰራ ያለው መንገድ ስራ 90 በመቶ የሚሆነው የአፈር ጠረጋና ምንጣሮ ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ ስራ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዑመር እንደገለጹት ከአጅባር ተድባበ ማርያም 30ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ ስራ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በመሰራት ላይ እንደሆነ ገልጸው አስካሁን በተሰራው ስራ 23 ነጥብ 17 ኪ.ሜትር የሚሆነው መንገድ የአፈር ጠረጋና የምንጣሮ ሥራ ተሰርቶለታል ፡፡

Wednesday, 3 February 2021

በጠያቂ እጦት ስትሰቃይ የኖረች አምሓራ ሳይንት

 

አምሓራ ሳይንት ለብዙ ዓመታት “ወንዝ የሚሻግራት” መሪ አጥታ ቆይታለች።  የአመራር ድክመቶች ሁሉ ምንጭ የመሪ ጉድለቶች ብቻ የሆነ አድርገን መውሰድ ይቀለናል። እኛ ተከታዮች ወይም ተመሪዎች (followers) ከመሪ ያላነሰ ተጠያቂነት አለብን። መሪዎቻችን ለአመራር ስኬት ብቸኛ ተወዳሽ መሆን እንደሌለባቸው ሁሉ ለአመራር ጉድለት ብቸኛ ተጠያቂ መሆን የለባቸውም። የመሪው ጉድለት መኖሩ ብናረጋግጥ እንኳን መሪው ብቸኛ ተጠያቂ ላይሆን ይችላል። ለአምሓራ ሳይንት ኋላቀር እድገት መሪና ተመሪውም ናቸው።