ኑ የበረከት ስራ እንስራ
ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ፣ ወልደ ነጎድጓድ፣ ፍቁረ እግዚእ፣ ነባቤ መለኮት(ታኦሎጎስ)፣ ቁጽረ ገጽ በመባል የሚታወቀው ወንጌላዊው ቅዱስ ዩሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣት የመጨረሻው ሽማግሌ ሐዋርያ እሱ ነበር፡፡
ቅዱስ ዩሐንስ የተወለደው በገሊላ አውራጀ በቤተ ሳይዳ ነው፣ አባቱ ዘብዴዎስ ይባላል፡፡ ቅዱስ ዩሐንስ ገና በወጣትነቱ ዘመን ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮ የጌታውን እግር ተከትሎ አድጓል፡፡ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የጌታ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ከነበሩት ደቀ መዛሙርት አንዱ ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ለጌታውና ለፈጣሪው ለመድኃኔዓለም ክርስቶስ ባሳየው ልዩ ቀረቤታና ፍቅር ምክንያት “ፍቁረ እግዚእ” የሚል ስያሜ አግኝቷል፡፡ ፍቅሩንና ታማኝነቱንም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ “እሱን ያገኘ ያገኘኛል፡፡” ብሎ ሳይፈራ ከእግረ መስቀሉ በመዋል በጽኑ እምነት አስመስክሮአል፡፡ በመሆኑም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ በመጨረሻዋ ሰዓት ቅዱስ ዮሐንስን ከእመቤታችን ጋር ከእግረ መስቀሉ ባየው ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን “እነሆ ልጅሽ ይርዳሽ፣ ያጽናናሽ”፤ ብሏታል፡፡ ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስም “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ብሎታል፡፡ ዩሐ. 19፥26፡፡
ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እነሆ ልጅሽ ይርዳሽ ያጽናናሽ” ማለቱ እኛን ለቀረነው ክርስቲያኖች በቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት ለእመቤታችን መስጠቱን፣ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ዮሐንስ “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ማለቱ እኛን እመቤታችሁ እናታችሁ ቅድስት ድንግል ማርያም ናትና ታጽናናችሁ፣ ተስፋ አለኝታ ትሁናችሁ ማለቱ እንደሆነ በግልጽ እንረዳለን፡፡
እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ በእንድ ቤት ልጅ ሆኗት 15 ዓመት የኖረ ይህ ሐዋርያ ነው፤ መልኩ ጌታችንን ይመስል ነበር፤ ለዚህም ነው ይሁዳ ጌታን በመሳም ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠው መልካቸው ስለሚመሳሰል ተሳስተው ዮሐንስን እንዳይዙት፤ ስለዚህ ሐዋርያት ስንቱን እንናገር ብዙ መከራ ተቀብሏል ነገር ግን እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ደሙ ፈሶ በሰማዕትነት አይደለም የሞተው፤ በ 90 ዓመቱ በዛሬዋ ቀን ከነስጋው ተሰወረ እንጂ በረከቱ ይደርብን። “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። …ቃልም ስጋ ሆነ” ይህን ቃል ያነበበ ሰው ግን እንዴት ይስታል፤ “አቤቱ ምሳሌ ስጠኝ እንጂ ምሳሌ አታድርገኝ” የምትለዋ ጸሎት እንዴት መልካም ነች፤ ወደ ነገራችን እንመለስ፤ በነገራችን ላይ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው በኤፌሶን ነው ዘመኑ መቼ ነው ቢሉ ጌታ ባረገ በ 30 ዓመቱ፤ የጻፈበት ቋንቋ ጽርዕ ይባላል፤ እናም ወንጌሉን ሲጀምር በመጀመሪያ ቃል ነበር ብሎ መጻፍ ሲጀምር ራዕይ ያያል ከዋንኞቹ መልአክት አንዱ ከትልቅ ሐይቅ ዳር ቁጭ ብሎ የሐይቁን ውኃ በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ መሬት ያፈሳል ቅዱስ ዮሐንስ ጠጋ ብሎ ምን እየሰራህ ነው ይለዋል የሐይቁን ውኃ ወደ መሬት እፍስሼ ለመጨረስ ነው ይለዋል ይህ እንዴት ይሆናል ደግሞም በእንቁላል ቅርፊት ይለዋል፤ ይህ ሐይቅ ፍጡር ነው ከረጅም ዘመን በኃላ ሊሳካሊኝ ይችላል አንተስ አለክ አይደል ቢቀዱት የማያልቀውን ቢጀምሩት የማይጨርሱትን የመለኮት ነገር የምትመራመር አለው በዚህ ጊዜ ነው የሐንስ የጀመረውን አቁሞ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ብሎ ወደ ሚስጢረ ስጋዌ የገባው ዮሐ 1፤14
ዮሐንስ ወንጌላዊ
ዮሐንስ ማለት ‹‹ የእግዚአንሔር ጸጋ ነዉ››፤ደስታ ማለት ነዉ፡፡አባቱ ዘብዴዮስ ፤ እናቱ ማርያም ባዉፍልያ ትባላለች፡፡ቁጥሩ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የሆነ ያዕቆብ የተባለ ወንድም ነበረዉ፡፡ ማቴ 4፡21 ፤ ማር 1፡20 ፤ማቴ 20፡20 ቅዱስ ዮሐንስ አስቀድሞ የዮሐንስ መጥምቅም ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ዮሐ 1፡ 35 ቅዱስ ዮሐንስ ከአባቱና ከወንድሙ ጋር ዓሣ በሚያጠምድበት በገሊላ ባህር ላይ መረቡን ሲያበጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያነት ጠራዉ፡፡ እሱም አባቱን ሌሎቹንና ታንኳን ትቶ ከወንድሙ ያዕቆብ ጋር ጌታን ተከተለዉ፡፡
የዮሐንስ ስሞች
1. ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
2. ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
3. ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ
4. ዮሐንስ ታኦሎጎስ
5. ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
6. ዮሐንስ ወንጌላዊ
7. ዮሐንስ ዘንስር
✟ ጌታ ስለሚመስል (ፍቁረ እግዚእ) ይባለል።
✟ ነገረ መለኮትን በበለጠ ከሌሎች አምልቶ አስቶ በጥልቀት በማስተማሩ ነባቤ መለኮት(ታዖሎጎስ)ተሰኝቷል። ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር) ማለት ነዉ፡፡ከአባቶቹ ነብያት ከወንድሞቹ ሐዋርያት መካከል እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ሚስጥረ ስላሴን አምልቶ አስፍቶ የተናገረ የለም።
✟ ስለጌታም ባለው ቅናት ባሳየው የሀይል ሥራ በኦኔርጌስ (ወልደ ነጎድጓድም) ተብሏል።
✟ ፍጥሞ በምትባል ደሴት በራዕይ መጻእያትን በመግለጡ ባለራዕይ (በግሪክ አቡቀለምሲስ) ይባላል ባለ ራዕይ የራዕይ አባት ማለት ነው፤
✟ ቁጽረ ገጽም ይባላ የጌታችንን ስቃዩን ካየ በኃላ ፊቱ ሳይፈታ 70 ዓመት ሙሉ አልቅሷል፤ ከመስቀል ስር ያልተለየው ብቸኛው ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ ነው።
1. ቅዱስ ዮሐንስ ወንድሙ ያዕቆብ የሰማርያ ሰዎች በእሳት እንዲጠፋ ተመኝተዉ ነበር ፡፡በዚህ ዓይነት የችኩልነት ስሜታቸዉ የተነሳ ጌታ ‹‹‹ቦአኔርጌስ››‹‹‹‹የነጎድጓድ ልጆች›››››ብሏቸዋል፡፡ማር 3፡17 ሉቃ 9፡54 በምሥጢር ደቂቀ ምሥጢር ደቂቀ መለኮት ሲል ነዉ፡፡ማር 3፡17
2. ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፤ያዕቆብ ዮሐንስ) ቀዳሚዉ ነዉ፡፡ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡
3. ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡፡
4. ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አምልቶና አስፍቶ በመጻፉ (ታኦጎሎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡
5. ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራእይ አባት ማለት ነዉ፡፡
6. ቅዱስ ዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌልን በመጻፉ ወንጌላዊ ተብሏል፡፡
7. በሥላሴ ስዕል ላይ ካሉት አራቱ እንስሳ አንዱ ንስር ነዉ፡፡ንስር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል፡፡ንስር በእግሩ እንደመሽከርከሩ ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡ንስር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላዉያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏል፡፡ንስር አይኑ ንጹህ ነዉ ሽቅብ ወጥቶ ቁልቁል ሲመለከት ቅንጣት የምታክል ሥጋ የታመልጠዉም፡፡ቅዱስ ዮሐንስም ወንጌል ሲጀምር እጅግ ርቆና መጥቆ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት የአካላዊ ቃልን (የእግዚአብሔር ወልድን)በቅድምና መኖር ተናግሯል፡፡በዚህም ዮሐንስ ዘንስር ተብሏል፡፡
ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነዉ፡፡ ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ??›› ዮሐ 21:20 ። ይህም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡ በማቴ 16፡18 ላይ ‹‹እዉነት….……ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ›› ያለዉ ቃል ለቅዱስ ዮሐንስና መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነዉ፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።
ምንጭ
✞ ማህበረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገፅ
✟ አምደ ተዋህዶ ገፅ
No comments:
Post a Comment