በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን እና ሀገር ጐብኚዎች ወደ ቅዱስ ላሊበላ መናገሻ ከተማ 11ዱ ፍልፍል አብያተ-ክርስቲያናት ወደሚገኙበት ሮሃ ከተማ ይጓዛሉ። ምክንያታቸው ደግሞ ታሪክና ጥበብን ለማወቅ እንዲሁም በረከትን ለማግኘት። በዚህ የጉዞ ማስታዎሻ ስለ ቅዱሱ ንጉስ( Holly king) ቅዱስ ላሊበላ እና ስራዎቹ ከላሊበላ ሰማይ ስር ስላሉት ነገሮች እናወሳለን።
ቅዱሱ ንጉስ (The Holly King)
ቅዱስ ላሊበላ በ 1101 አ.ም ትህሳስ 29 ቀን ከ እናቱ ከኬርዮርና ከአባቱ ዛንስዮም ላሰታ ቡግና ወረዳ ሮሃ ከተባለች ቦታ ከ ፍልፍል ቤተ መቅደስ ውስጥ ተወለደ በዚህ ፍልፍል ቤተ-መቅደስ ውስጥ እድገቱን አደረገ ስድስት አመት ሲሞላው ቤተ-መንግስት አባ ዳንእል የተባሉ መምህር ተቀጥረውለት ከ ፊደል እስከ ዳዊት ተማረ።
ቅዱስ ላሊበላ 12 አመት ሲሞላው አባቱ ዘንሳዮም 40 አመት ነግሶ በተወለደ በ 76 አመቱ ከዚህ አለም በ ሞት ተለየ ወድያው ብዙም ሳይቖይ እናቱ ኬርዮርና በሞት ተለየች፡፡ ቅዱስ ላሊበላ በ እናቱ ና አባቱ ህልፈተ ህይወተ በደረሰበት ሀዘን የተነሳ ሁሉን ነገር ለመርሳት ና የትምህርት ፍላጎት ለሞሞላት ጉዞውን ወደ ጎጃም በማድረገ አለም ስላሴ ከተባለው ደብር ከመምህር ኬፋ ሃዲሳቱን አጠናቖ በመመረቅ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡
በወቅቱም በኢትዮጵያ ላይ ነግሶ የነበረው ታላቅ ወንድሙ ቅዱሰ ገብረ ማሪያም ነበር። ነገር ግን ላሊበላ ሊነግስ መሆኑን ሲረዱ ወንድማቸውን ለመግደል ንጉሱ እና እህቱ ቅዱስ ላሊበላ ሁሌም እሚጠጣው ባህላዊ መድሃኒት ውስጥ መርዝ በመጨመር ለላሊበላ አስቀመጡለት። በሃገሬውን ባህል መሰረት ሰጪ ሳትቀምስ አይሰጥም ነበር ስለሆነም እንዲሰጠው የታዘዘው አብሮት የነበረው ዲያቖን የተቀመጠውን መድሃኒት ቀምሶ ወዲያውኑ ላሊበላ ፊት ወድቆ ሞተ ቅዱስ ላሊበላ ይህን ባየ ጊዚ እኔን ለማጥፋት የመጣው መድሃኒት የሌላውን ነፍስ አጠፋች በማለት የቀረውን መድሃኒት በመጠጣት ለ ሶሰት ለሊት እንደ ወደቀ ቀረ።
ከዚያም ነዋሪው ገንዦ ለ መቅበር ሲዘጋጁ የ ሰውነቱ ሙቀት አልተለየውም ነበር ይሄን ጊዜ ወድያው ቅዱስ ላሊበላ ነቃ የተመለከቱት ሰዎች ተደናገጡ ከዚያም ይህ ሁሉ ነገር በ እህቱ መደረጉ ያሳዘነው ቅዱስ ላሊበላ በመነሳት ጉዞውን ወደ ጫካ አደረገ ኑሮውንም ለ ረጅም አመት እዚያው አደረገ ይህ እንዲ እንዳለ ሚስት እምትሆነውን ሴት አገኝ ቤተሰቦን በማስጠየቅ በ ቤተ ክርስትያን ስርአት ተጋብተው ጥቂት አመት እንደቆዩ ጉዞውን እየሩሳሌም አደረገ ለ ተከታታይ 13 አመታትም ቆይታ በሓላ ወደ ባለቤቱ ተመልሶ ከ ውንድሙ ከ ቅዱስ ገብረ ማሪያም ጋር እርቅ በማውረድ ቅዱስ ገብረ ማሪያም ንግስናውን ለ ቅዱስ ላሊበላ በተወለደ በ57 አመቱ በማስረከብ ኑሮውን በ ገዳም አደረገ፡፡
ንጉስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናቱን ለማነፅ ምን አነሳሳው?
ገድለ ላሊበላ፣ ንጉስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናቱን ለማነፅ ስላነሳሳው ምክንያት ሲያትት፣ “ወደ መንግስተ ሰማያት አርጎ እጅግ የሚያማምሩ ህንጻዎችን በመመልከቱና እግዚአብሔርም እነዚህን ህንጻዎች የመሰሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲያንፅ ስላዘዘው፣ ቦታውንም ስለጠቆመው ነው…” ይላል፡፡
ሌሎች ምንጮች ደግሞ፣ “ላሊበላ ለረጅም ዓመታት እየሩሳሌም እንደነበረ፣ እየሩሳሌምንና ሌሎች ሃይማኖታዊ ፋይዳ ያላቸውን ቦታዎችን በመጎብኘቱና ባየው ነገር እጅጉን በመመሰጡ፣ ሌላኛዋን እየሩሳሌም ለመገንባት በማሰቡ ነው…” ባይ ናቸው፡፡
እኒህ ወገኖች እንደሚሉት፣ “በወቅቱ፣ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እየሩሳሌምን ለመጎብኘት በሚያደርጉት ጉዞ የሚደርስባቸውን እንግልት ለማስቀረት እየሩሳሌምን፣ አካባቢውንና መንግስተ ሰማያትን ሁሉ በተምሳሌትነት የሚያሳይ ታላቅ ግንባታ ለመስራት ስላሰበ ነው” ይላሉ፡፡
ቅዱስ ላሊበላ ስልጣን ላይ ከወጣ በሓላ ሕንዓዎችን ለመገንባት አሰበ ከዚያም በጊዜው ከነበሩት አባቶች በተለይ ቀይት ከ ምትባል ባለአባት የጠየቀውን 40 ጊደር ለ መግዛት በ ሚያስችለው ወርቅ ቦታውን ገዝቶ በከርሰ ምድር ውስጥ ያሉትን ሕንዓዎቸ ሊያወጣ ተዘጋጅ፡፡ ቅዱስ ላሊበላ የሚገነባባቸውን መሳሪያዎችለ 10 አመታት አዘጋጅቶ ማለትም በ 1157 አ.ም ነግሶ በ1166 አ.ም ሕንጻውን ገንብቶ ጨረሰ፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ከ 40 አመታት የንግስና ዘመን በሓላ በተወለደ በ 97 አመቱ ሰኔ12 ቀን ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡
የላሊበላ ህንጻዎች
የቅዱስ ላሊበላ ሕንጻዎቹ ታሪክ የሚያወጋው የመጀመሪያው ጽሑፍ መረጃ በ15ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ በተጻፈው “ገድለ ላሊበላ” ነው። ይህም ገድል ከአፄ ላሊበላ ሞት ሁለት መቶ አመታት በኋላ እንደተጻፈ ሲገመት የገድሉም ጸሐፊ የላሊበላን ቤተክርስቲያናት ሲያደንቅ እንዲህ ይላል
“ወዳጆቼ ሆይ! ተመልከቱ እንጂ። ይህ ሰው በእጆቹ የተገለጹለት እነዚህ ግንቦች በየትም በሌሎች ሀገሮች አልተሰሩም። ስለ እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት አሠራር በምን ቃል ልንነገራችሁ እንችላለን? የቅጽራቸውንም ሥራ እንኳ መናገር አንችልም። የውስጡንስ ተዉት ታይቶ አይጠገብም፣ አድንቆና አወድሶም ለመጨረስ አይቻልም። በላሊበላ እጅ የተሠራ ይህ ድንቅ ሥራ በሥጋዊ ሰው የሚቻል አይደለም። በሰማይን ከዋክብት መቁጠርን የቻለ፣ በላሊበላ እጅ የተሰራውን መናገር ይችላል። እናም ለማየት የሚፈልግ ካለ ይመልከት። በላሊበላ እጅ የተሠሩትን የአብያተ ክርስቲያኖቹን ሕንጻዎች ይምጣና በዓይኖቹ ይመልከት!”
ከአንድ መቶ አመታት ያህል በኋላም በ1520ዎቹ ፍራሲስኮ አልቫሬዝ የተሰኘ ካህን ከፖርቱጋል መልእክት ለማድረስ መጥቶ ለስድስት አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጦ ነበር። በዚህም ወቅት የላሊበላን ውቅር ቤተክርስቲያናት ለመጎብኘት እድል አግኝቶ እያንዳንዱን ሕንጻ ከገለጸ በኋላ በመደነቅ እንዲህ ብሏል፣
“ስለነዚህ ሕንጻዎች ከዚህ በላይ መጻፍ አልችልም። ምክንያቱም ከዚህ በላይ ብጽፍ የሚያምኑኝ አይመስለኝም። እስካሁን የጻፍኩትንም እውነት አይደለም ይሉኛል ብዬ እፈራለሁ። እኔ ግን በኀያሉ እግዚአብሔር እምላለሁ የጻፍኩት ሁሉ እውነት ነው! እውነታው እንዲያውም ከዚህም ከጻፍኩት እጅግ የበለጠ ነው። ውሸታም እንዳይሉኝ ግን ትቼዋለሁ።”
ይህንንም አድናቆቱን በ1532 ዓ.ም በመጽሐፍ መልክ አሳትሞት የውጪው ዓለም ላሊበላን እንዲያውቅ አድርጓል። ስለ ላሊበላ ሕንጻዎች በጽሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመግለጽ የሞከረው የውጭ ሐገር ተጓዥ አልቫሬዝ ነበር። የአልቫሬዝ ገለጻ ምናልባትም ላሊበላ ከኢማም አሕመድ ኢብን ኢብራሂም "ግራኝ አሕመድ" ዘመን በፊት ምን ይመስል እንደነበር በመጠኑ ይገልጽልናል። አልቫሬዝ ላሊበላን ከጎበኘ ከ10 አመታት በኋላ ኢማም አሕመድ በላሊበላ አካባቢ ሰፍሮ እንደነበረ ይነገራል።
ኢማም አሕመድ ንዋየ ቅድሳቱንና ንብረቶቹን ከመውሰድ ውጭ እንደሌሎቹ ቤተክርስቲያናት ላሊበላን ለማቃጠል እና ለማውደም እንዳልሞከረ አንዳንድ ምንጮች ይጠቁማሉ። በቤተ ክርስቲያናቱ አሰራር ኢማም አሕመድም ተደምሞ የነበረ ይመስላል። በድጋሚ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ከመጡ ጎብኚዎች ጀምሮም ብዙዎች ለላሊበላ አድናቆታቸውን በተለያየ ጊዜ ጽፈዋል። ነገር ግን በአፄ ላሊበላ ዘመን የነበሩ ምስክሮች የጻፉት ታሪክም ሆነ ስለ አሰራሩ የሚነግሩን መረጃዎች እጅግ ጥቂት ናቸው። በመሆኑም የተለያዩ አጥኚዎች ምሁራዊ መላምታቸውን በየጊዜው ሲሰጡን ከርመዋል።
No comments:
Post a Comment