****
(የተረሱ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ መስህብ ፍለጋ)
Photo credit: Amhara sayint press |
ምስጢር፣ እውቀት፣ እውነት፣ ውበት፣ እምነት፣ ታሪክ፣ ጀግንነት፣ ተፈጥሮ ሁሉም በአንድ ላይ ተሰድረውና ተደምረው የሚገኙባትን ቦታ ፍለጋ እንሄዳለን ፡፡ አምሓራ ሳይንት
አምሐራ ሳይንት ተወልደህ የፈራህ እንደሆን ፣
እናትህን ጠይቃት ሽል ቀይራ እንደሆን ።
አምሐራ ሳይንት ሆነህ የሸሸህ እንደሆን
እናትህን ጠይቃት ዘር ቀይራ እንደሆን ።
ሚኒሽር ጌጡ ነው ትራስ ነው ዝናሩ
ዘራፍ በል ሳይንቴ አንተ የጀግና ኩሩ!!
እየተባለች የምትሞገስ የጀግኖች አገር ጥራ ከተባልክ እሷም ጥንታዊቷ ከተማ አምሓራ ሳይንት ናት፡፡
ጀግንነት ብቻ ሳይሆን አምሓራ ሳይንት ምልክቷ ውበትም ጭምር ነው ነው፡፡
የሳይንቷ ቆንጆ ተነሽ ከመኝታሽ፣
እንዴፅጌረዳ ይጣፍጣል ሺታሽ።
በማለት ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ያለ ሜካፕ ውብ የሆኑ ቆንጆ ሴት የደመ ግቡዎች መገኛ ጭምር ናት አምሓራ ሳይንት።
ዓይኑን ለወረወረ እግሩን ላዟዟረ ሰው እንኳን ኗሪዎቿ ይቅርና መሬቷ ከቆላ እስከ ደጋ ፤ በክብር ተጎማሎ ከተቀመጠው የታቦር ተራራ፤ እንደሰማይ ተዘርግቶ ለጋማና ለቀንድ እንስሣት መፈንጫ የሆኑት አምባ ምድሮቿ፣ በገዳማት ተከበበው ልብን ስርቅ የሚያደርጉት መልከአምድራዊ አቀማመጧ፣ ሜዳዎቿ እስከ የአባይ ወንዝ ትልቁ ገባር የበሽሎ ተፋሰስ ሸለቋማ ቦታ ድረስ ያለው ዝቀተኛ ቦታዎቿ የአማራ ሳይንት የተፈጥሮ ቦታ የውበቷ መገለጫዋ ነው፡፡
አምሓራ ሳይንት የአማራ ህዝብ የታሪክ እና የቅርስ እምብርት ናት፤ (የአማራ ሕዝብ የመጀመሪያው መገኛ ሀገረ አምሓራ ሳይንት ወይም ቤተ አምሓራ) እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያረጋግጣሉ(ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፡ዝኒከማሁ)። ከአፄ ይኩኖ አምላክ ጀምሮ ያለውን ብዙ ያልተፃፈለትን የኢትዮጵያን ታሪክ ሰድራ ከትባ የያዘች የታሪክ አደራ ያዥ ቦታ ናት አምሓራ ሳይንት። በኢትዮጵያ መስዋዕተ ኦሪት ከተሰዋባቸው 4 ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የተድባበ ማርያም መገኛ ናት አምሓራ ሳይንት።
ይቀጥላል.......
No comments:
Post a Comment