Tuesday, 9 February 2021

የኢኮኖሚ ዋልታችን ግብርናችን! መልስ ለሗላቀር ግብርናችን ለአማሓራ ሳይንታችን



ለአርሶ አደሩ

****

ለአማራ ሳይንት የህብረተሰቡ ዋነኛ የኢኮኖሚያችን ዋልታ ግብርና እንደሆነ ይታወቃል። ሆኖም ወረዳዋ ራሷን በምግብ እንዳትችል እና  ግዜው የሚጠይቀውን የግብርና ልማት እንዳትከተል፣  የግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂ እንዳታገኝ ሲነፈጋት የኖረች ወረዳ ናት። አምሓራ ሳይንት የግብርናና የገጠር ልማት ስራዋ ለዘመናት ተረስቶ ከመሬት የተሻለ የግብርና የልማት ግብዓትን እንዳታገኝ   የወረዳዋ አርሶ አደሮች ከተመጽዋችነት የማያላቅቅ  ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የግብርና ዘይቤ ውስጥ እንድትሆን የተፈረደባት ወረዳ ናት። 


ሆኖም ግን ወረዳዋ የሁሉም የአየር ንብረት ባለቤት ስለሆነች  በዚህም አርሶ አደሩ የላቀ ዋጋ ወዳላቸው ምርቶች በማምረት እንዲሸጋገር የቀበሌ የወረዳ አመራሮች ሌት ተቀን መስራት አለባቸው።


ትኩረት !!

📌ለእርሻ ልማታችን (ለሰብል አዝዕርት) ልማት 

📌ለአትክልትና ፍራፍሬ ምርት

📌ለእንስሳት ሃብት ልማት

📌ለግብርና ሜካናይዜሽን

📌ለባዮ ቴክኖሎጂ  

📌ለግብርና ጥራትና ስነ-ምግብ 

📌ለንብና ለሐር  ልማት 

📌ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ልማት

📌ለአረንጓዴ የግብርና ልማት (አግሮኢኮሎጅ)


ግብርና ለተማሩ ወጣቶች፡

*****************

የወረዳዋ አመራሮች ግብርናን እንደ ቢዝነስ እና ስራ ፈጠራ  እንዲሁም እንደ ስራ እድል በማየት ለተማሩ ስራ ፈላጊዎች አመራሩ ከመቸውም ለወረዳዋ መስራት አለበት። ኋላቀር ግብርናችንን የምናሳድገው  የተማሩ ወጣቶችን በማደራጀት በግብርናው ክፍለ  ኢኮኖሚ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ እንደሆነ የአማራ ሳይንይ  የወረዳዋ አመራሮች ሊገነዘቡና ሊያውቁ ይገባል። ከዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ለተመረቁ ወጣት ስራ ፈላጊዎች በተደራጀ መንገድ በግብርና ልማት ሥራ እንዲሳተፉ የወረዳዋ አመራሮች ድጋፍ መስጠት ፕሮጀክት መንደፍ  ያስፈልጋቸዋል፡፡  የከተማ ግብርና ልማት  ለምሳሌ  ደሮ እርባታ የእንስሳት ምርት  ውጤቶች፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች ነገሮች  ላይ በማሰማራት መሬት በማቅረብ፣ አንዳንድ ቴክኖሎጅ ግበአት ከክልል በመጠየቅና መመስጠት፣ በማመቻቸት፣ የማስፈፀምና የመፈፀም ስራ በመስራት አንድም ለስራ ፈጠራ ያለንን ቁርጠኝነት ሌላም የግብርናውን ዘርፍ እናሳድጋለን።


Amhara Sayint Social Media Network

No comments: