Wednesday, 24 February 2021

የከተማ እድገት መሰረት፤ የኢኮኖሚ ደም-ስር፤ አንገብጋቢው ጉዳያችን የሁልግዜም ጥያቄያችን መንገድ መንገድ መንገድ

"መንገድ ካሰቡበት የሚያደርስ" የሚለው ብሂል ለአማራ ሳይንት አይሰራም።  የንግድ ልውውጦቹ የተሳለጡ እንዲሆኑለት፤ አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ በጊዜ እንዲያደርስና ተጠቃሚ እንዲሆን፤ የከተማዋ ነዋሪዎች የሚፈልጉትን ሸቀጥም ሆነ ምርት በጊዜ እንዲያገኙ፣ ወረዳዋ የቱሪዝም

ሃብቷ እንዲተዋወቅና የገቢ ምንጭ እንዲሆናት፤ የህክምና፣ የመብራት፣ የትምህርትና የመሳሰሉ አገልግሎቶች ወረዳዋ  እንዲዘምኑላት፤ በጥቅሉ የወረዳዋ ኗሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እንዲሻሻል፤  የወረዳዋ ልማትና እድገቷ እውን እንዲሆን  የዘመናዊ መንገድ  ልማት (የአስፋልት መንገድ)  ህዝቡ አብዝቶ የሚጮህለት ግን እስካሁን  ሰሚ ያጣ ጥያቄያችን ነው።


እንጮሃለን!!!  ለምን?

1. ለወረዳዋ ለአስፋልት መንገድ ልማት በክልልም ሆነ በፌደራል በጀት ስለማይመደብ

2.  እንደሌሎች ወረዳዎች  የመልማት ጥያቄ ህዝብ ስላለው

3. ነባሩ የጠጠር መንገድ ሁኔታ:  ለማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ መንግስታዊ ችግር  

4. ከፍተኛ የህዝብ እና የንግድ የትራፊክ እንቅስቃሴ

5. ፍትሃዊ እና እኩል የአስፋልት የመንገድ ስርጭት ባለመኖሩ

6.  የወረዳዋን ከተማ ገጽታ የመለወጥና የማሳደግ ሁኔታዎች

ውድ የአማራ ሳይንት ተወላጆች ወንድም እህቶቸ፣ እናት አባቶቸ፣ አርሶ አደር፣ ነጋዴ፣ መምህር፣ ተማሪ፣  መንግስት ሰራተኛ፣ ሁላችንም በአንድ ላይ ለራሳችን ለልጆቻችን ለወረዳችን  ስንል በሰለጠነ መንገድ የወረዳዋን ከፍተኛ አመራሮች የአስፋልት የመንገድ ጥያቄያችንን ደጋግመን እናቅርብ። 

በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ህግና መመሪያ መሰረት አንድ ወረዳ የአስፋልት መንገድ እንዲሰራለትና  የነባር መንገዶች ደረጃ የማሳደግ ፕሮጀክቶች የመጀመሪያ ደረጃ ምርጫ የሚከናወነው በሚከተሉት አምስት መመዘኛዎች መሠረት ነው፡፡

>>> የትራፊክ ሁኔታ 

>>> የመንገድ ሁኔታ 

>>>  ንግድ  እና ከጎረቤት ወረዳ አዋሳኝነትና አገናኝነት (ማዕከላዊነት)

>>> የኢንቨስትመንት እድል ናቸው።

 ከዚህ አንጻር የአማራ ሳይንት ወረዳ የአስፋልት መንገድ ስራ ማህበረ-ኢኮኖሚው አዋጭነቱ  (Socio-economic fesibility) ከብዙው በጥቂቱ:-

1. ቱሪዝም:- ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቦታዎች መገኛ (የተፈጥሮ እና ሠው ሠራሽ የሚዳሠሱ እና የማይዳሠሡ የቅርስ ባልተቤት)

2. ማዕከላዊነት:- ደቡብ ወሎን እና ሰሜን ወሎን ከደቡብ ጎንደር ጋር ለማስተሳሰር (የአምሓራ ሳይንት - ስማዳ ፕሮጀክት)፤ 

3. የግብርና ምርቶች:- ሁሉም የግብርና ምርቶች በአይነትና በብዛት መገኘት

4. ኢንቨስትመንት:-   ለኢንቨስትመንት ድንግል ቦታ

5. የገበያ መዳረሻ :- source of market place

6. የከተሞች መስፋፋት እና የንግድ መኖር

 

የመንገድ ፕሮጀክቶቻችን

1. የቡሶ  አጅባር የአስፋልት መንገድ

2. የአጅባር  ስማዳ መንገድ 

No comments: