በቲና በቀለ
#ከአመታት_በፊት እንዲህ ሆነ... ከአንድ ወዳጄ ጋር ባህርዳር ጣና አካባቢ ተቀምጠን በብዙ ሀሳቦች ላይ እየተወያየን ባለንበት ሰአት እኛ ከተቀመጥንበት በስተቀኝ በኩል ጓደኛዬ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎችን ይመለከታል እንዳስታውላቸው ይነግረኛል።
ሴትና ወንድ በእድሜም ጠና ያሉ ነጮች ናቸው፤ ወደ ሰሜን ምዕራብ ጣና ሀይቅ አካባቢ ውድ፣ ዘመናዊ በግለሰብ ደረጃ ብዙም የማይገኘው መቅረጸ ትዕይንት Camera አቅርቦ የሚያሳይ telescope ከጀረባቸው እንዲሁም ትልቅዬ ቦርሳን አዝለው ወደ ሀይቁ አይናቸውን በሁለት አቅጣጫ እያመላለሱ በተደጋጋሚ ይመለከታሉ።
ለብዙ ደቂቃወች ይህንን የጠለቀ እይታ እና የሚጠቀሙትን ውድ ዘመናዊ Telescope ስመለከት እኒህ ሰው የመልካ ምድር አሳሾች ወይም የጥንት መዛግብት ተመራማሪወች ሊሆኑ እንደሚችሉ ገመትኩ።......
ነገር ግን ሰአቱ እየመሽ ስለነበር እኒህን ሰዎች ለማናገር ሆነ ምን እየፈለጉ እንደሆን ሁኔታወችን ለመከታተል አልቻልኩም ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ልክ በሳምንቱ በእለተ ሰንበት አመሻሽ እዚህው ቦታ ንጹህ አየርን ለመቀበል ጎራ ብየ የሚስጥራዊውን የጣናን ነፋሻማ አየር እየተመገብኩ፤ በቅርብ የምትገኘውን የአባይና የጣና መገናኛ ደብረ ማርያም ገዳምን በቅርብ እርቀት እያየሁ
< አባይ በጣና ላይ እንዴት ቀለደበት
ለአንድ ቀን ነው ብሎ ዘላለም ሄደበት >
የሚለው ቃላዊ ግጥም እያስታወስኩ አባይና ጣና ደብረማርያም ላይ የሚያሳዩት ትርኢት በአይነ ህሊናየ እያመላለስኩ በተፈጥሮ አቀማመጥ እደመማለሁ።
እጆቼን አጣምሬ ከአግድም ወንበር ላይ ተቀምጨ ክብራን ገብርኤል እና እንጦስ ደሴቶች 7 ገዳማትን የያዘውን ዘጌ ባህረገብ ደሴትን በወፈ በረር የህሊና ቅኝት አልፌ በዘጌ ጊዮርጊስ አልፌ ኡራ ኪዳነ ምህረትን ታክኬ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አዝዋ ማርያም፣ ደብረ ስላሴ አስሽ. . . ታሪካዊ እና ሀይማኖታዊ ዳራ፤ መንፈስን የሚያድሱ ገዳማትን በህሊናየ ፈረስ እየጋለብኩ ከክብራቸው ብዛት ስከብር፤ ከቅድስናቸው ስቀደስ፤ ከገዳማቱ ጋር ማዶ ለማዶ እየተያየን በትዝታ እወሰወሳለሁ።
#አለምን የናቁ የብዙ ሊቃውንት ዶ/ር እና ፕሮፌሰሮች ፓይለቶች መገኛ ገዳማት፤ ኦሪታዊው የጣና ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ፤የዳጋ እስጢፋኖስ ግርማ ሞገስ፤ እያሰብኩ በደስታ የሚመስል ቁጭት በትካዜ በመሰለ የወደፊት ተስፋ በተዘበራረቀ ስሜት እዋኛለሁ..!
ከሰላሙ ሰላሜን፣ ከነፋሱ ደስታየን ሳላጣጥም ከተቀመጥኩበት በስተቀኝ በኩል ከሳምንት በፊት ከዚህው ቦታ የየሁት የውጭ ሀገር ዜጋ ከስር በፎቶ እንደምትመለከቱት የተለመደውን ውድ ውድ Camera ና አቅርቦ የሚያሳይ telescope ጣና ሀይቁ ላይ ደቅኖ ለረጂም ደቂቃ በእርጋታ ይመለከት ጀመር።
ከመዝናናት እና ፎቶ ከማንሳት የዘለለ ይህ ሰውየ አንዳች ነገርን እየፈለገ ወይም እያሰሰ ሊሆን እንደሚችል እርግጠኛ ሆንኩ።
ከተወሰነ የሀይቁ ላይ አሰሳ በኋላ ወደ ግራ ወደ ቀኝ ወደኋላ በመዞር በአቅራቢያው የሚያስተውለው ሰው እንደሌለ መቃኘት ጀመር።
#ሰው እንዳላስተዋለውና ሁሉም የየራሱን ወሬ ላይ እንደተጠመደ እሱ ላይ ትኩርት እንዳልሰጡት ሲረዳ ከጀርባ ያዘለውን ቦርሳ ፈጠን ብሎ በማውረድ በጉልበቱ በርከክ ብሎ ቦርሳውን ይፈታ ጀመር።
ከአረንጓዴ ዘንባባው በስተጀርባ የሰውየው ሁኔታን በአንክሮ እከታተለው እና አስተውለው ጀመር፤ ከታጨቀው ቦርሳ ምን ሊያወጣ እንደሆን መገመት አልቻልኩም።
ከተወሰኑ ደቂቃወች በኋላ ከታጨቀው ቦርሳ የአቅጣጫ መጠቆሚያ ና ጋዜጣ የሚመስል የተጠቀለለ ወረቀትን ሲያወጣ ተመለከትኩት።
አሁንም በድጋሚ ዞር ዞር በማለት የሰውን ትኩርት አለመሳቡን አረጋግጦ ከሰው እይታ ውጭ ሊያደርገው የሚችለውን ቦታ ውስጥ ተወሸቀ ለእኔ ግን ከቀደመው ይበልጥ ይታየኝ ነበር።
ከታጨቀዉ ቦርሳ ውስጥ ያወጣው ጥቅል ጋዜጣ ነገር መሬት ላይ ወጥሮ ሲያስተካክል ከአቅጣጫው ተቋሚው ጋር ተደምሮ የባህር ላይ ካርታ ሊሆን እንደሚችል ገባኝ።
አሁን ወደ ቀደመ አሰሳው ተመለሰና ከሁለት አቅጣጭ በተደጋጋሚ ይመለከት ጀመር።
ከጣና ሀይቅ ደቡባዊ ክፍል ወይም ከሰውየው ምዕራብ እና ወደ ሰሜን ምዕራብ ጣና፤ አሰሳውን ቀጠለ አቅርቦ የሚያሳይ ውድ telescope እና ካሜራውን በተደጋጋሚ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ላይ ተክሏል።
ከመሬቱ ጋ የወጠረውን ካርታ ላይ በያዘው ብእር መልክቶችን ያደርጋል።.........
#እኔ አንድ ጥያቄ ውስጥ ገባሁ በተደጋጋሚ ወደ ምዕራብ እና ሰሜን ምእራብ የሚመለከትዉ ምን ፍለጋ ነው የሚል...❓
በዚህ አቅጣጫ ሊገኙ የሚችሉ ገዳማት ላይ ይሆን ትኩረቱ? የሚል መላመታዊ ሀሳብ በህሊናየ ተመላለሰብኝ።.....
ከሆነስ የአቅጣጫ መጠቆሚያ አንዲሁም ካርታን ይዞ በሁለት አቅጣጫ የሚታሰሱ ገዳማቱ እነማን ይሆኑ❓
የሚያስሰው ዳጋን ይሆን ክቡራንን ደቅ ይሆን ናርጋን ጣና ቂርቆስ ወይስ ኡራ ኪዳነ ምህረትን❓
ከሰውየው ሁለንተናው እንቅስቃሴ አንጻር በሚስጥር የሚፈልገው አንድ ታላቅ ነገር እንዳለ ተረድቻለሁ።
ነገር ግን ይህ የሚፈልገውና የሚያስሰው ምን ይሆን ለሚል ጥያቄ መልስን ከሰውየው በየትም ብየ ማግኝት እንዳለብኝ ገባኝ።
ከለበሰው የደረት ኪስ አነስ ያለች የሞባይል ስልኩን አውጥቶ The far between To monastery is 13 km 67 degree North west and 23 degree of west የሚል መልክትን አስተላልፎ ስልኩን ዘጋ።
ስለዚህ ይህ ሰው በሁለቱ ገዳማት መካከል ያለውን እርቀት እንደተናገር ገባኝ ፈጠን ብዬም የተናገረውን ነገር በብጣሽ ወረቀት ላይ አስፍሬ ሰውየው የሚፈልጋቸው ገዳማት እነማናቸው ይሆኑ የሚል ጥያቄ ውስጥ ገባሁ።
#ስለዚህ የእረቀቱትና እና አንግል ልኬታውም እኛ ካለንበት መነሻ አድሮጎ ሊለካው እንደሚችል በመገመት በመካከላቸው የ13ኪሜ ርቀት እና 67 NW እና 23 W ዲግሪ ሊለኩ የሚችሉ ገዳማት ማን ሊሆኑ እንደሚችሉ በያዝኳት ብጣሽ ወረቀት መፈለግ ጀመርኩ።
በመጀመሪያ የደቅ ደሴት ገዳማትን እርቀት ከ ዘጌ እና ከዳጋ እስጢፊኖስ በማነጻጸር ማስላት ጀመርኩ ነገር ግን በመካከላቸው ያለው እርቀት ከ13 ኪሜ የበለጠ ሁኖ አገኘሁት።
ስለዚህ ሌላ ስሌት ማስላት ጀመርኩ ከሰውየው በተደጋጋሚ እይታ አንጻር በስተ ሰሜን ምዕራብና በምዕራብ አቅጣጫ ሊገኙ የሚችሉ ገዳማት እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ መርጨ አወጣሁ።
በሰማሁት አንግልና እርቀት ተጠቅሜ እኛ ካለንበት አካባቢ 5km ሰሜን ምዕራብና 12 km ምዕራብ አቅጣጫ እርቀትን አስለቼ አገኘሁት።
አሁን ዋናው ጥያቄ የሚሆነው እኛ ካለንበት 5 km ወደ ሰሜን ምዕራብና 12 km ወደ ምዕራብ ሊርቅ የሚችል ገዳም አለ❓
ካለ በዚህ ገዳማት ክልል ውስጥ ሰውየው የሚፈልገው ትልቅ ሚስጥር አለ ማለት ነው።
የእጂ ስልኬን አውጥቸ በMap Gps ያለሁበትን reference አድርጌ ካለንበት 12 km ምዕራብ እርቀት ላይ የሚገኘውን ስፍራ ስመለከት በሚገርም ሁኔታ ታላቁን ክቡራን ገብርኤል ገዳምን ጠቆመኝ።
ሁለተኛው ገዳማስ ማን ሊሆን ይችል ይሆን በሚል ጉጉት የስልኬን google Map Gps ካለሁበት 5km ሰሜን ምዕራብ እርቀት ሊገኝ የሚችል ቦታ እንዲጠቁመኝ አዘዝኩት ይህም ጥቆማ ደብር ማርያም ገዳም መሆኑን ስመለከት አፌን በእጀ አስጫነኝ።
#ስለዚህ በእነዚህ ገዳማት ላይ ሊሰራ የታሰበ የጥንት መዛግብትን ለመመርመር ወይም የቅርስ ስርቆት ታስቦ ሊሆን ይችል ይሆን የሚል ጥርጣሬ አጫረብኝ።
ስለዚህ ይህን የውጭ ሀገር ዜጋ ማናገር አንዳለብኝ ወሰኩንኩና ወደ ሰውየው ለመጠጋት ሞከርኩ አሁንም ጣና ላይ በአጉሊይ መነጸሩ እንዳፈጠጠ ነው።
ምንብየ ልጀምር በሚል ፈራ ተባ ሀሳብ ላይ እያለሁ የጎረነነ የእንግሊዝኛ ቋንቋ በቀኝ ጀሮዬ በኩል የሰላምታ ድምጽ ሰማ። ሰላምታየን መለስኩ..... ፈቃደኛ ከሆንኩ አንድ ጥያቄ ሊጠይቀኝ እንደፈለገ ነገርኝ እኔም ይሁንታየን ጭንቅላቴን በማንቀሳቀስ ገለጽኩለት።
የጠየቀኝ ከእሩቅ እንደ ዝንብ የሚታዩ ታንኳወችን ምንነትና አሰራረና ነበር እኔም ደንገል ከሚባል የባህር እጽዋት በባህላዊ መንገድ የሚሰሩ ጀልባወች እንደሆኑ አሰረድቼ ወደ ተከፈተው ቦርሳ አይኖቸን ወረወርኩ።
ገርበብ ብሎ ከተከፈተው ቦርሳ ሁለት ሽፋናቸው ትኩርትን የሚስብ መጻህፍቶችን ተመለከትኩ።
የመጀመሪያው The lost image of cross የሚለው መጻህፍ ሲሆን(ይህን መጻህፍ ከአባ ፍቅረ ቤት ካረጀችው ጎጆ በኖራ አፈር ከተለቀለቀች ቤት ውስጥ ያየሁት መጻህፍ ነበር)......
ሁለተኛው እና እጂግ ያስገረመኝ መጻህፍ ከሽፋን ገጹ ላይ በ ሶስት ማእዘን ውስጥ UTHIOPIA የሚል ጽሁፍ መጻህፍ ሽፋን ላይ በማየቴ ነው።
አሁን ጥያቄየ የሚሆነው በዚህ 12 ኪሜ ምዕራብ አቅጣጫ 5 ኪሜ ሰሜን ምዕራብ በመሀከላቸው 13 ኪሜ ርቀት ያለው የሶስት ማእዘን ክልል ውስጥ አንዳች UTHIOPUA በሚል ትርጉም ጋር የሚገናኝ ሚስጥራዊ ነገር ሊኖር እንደሚችል ገመትኩ..
ከታጨቀዉ ቦርሳ ውስጥ ያየሁአቸው እኒህ መጻህፍት ከዚህ ቀደም በተለያየ አጋጣሚ በገዳምያኑ ዘንድ ሲነገር ሰምቻለሁ።
በተለይ የተለየ መልእክት ያለው ሽፋን መጻህፍ በሶስት መአዘን ውስጥ ከተጻፈው Uthiopia ከሚል ቅኔያዊ ትርጉም ጋ ተጣምሮ አንዳች ያልተገለጸልኝ እንቆቅልሽ እንዳለ ተረዳሁ።
ይህ ሰው የምን ሀገር ዜጋ ሊሆን እንደሚችል መገመት አልከበደኝም፤ ምክኒያቱም ከለበሰው ውሀ መሳይ ቲሸርታ ከግራ ደረቱ ላይ በእኩል መደቡ ከታች ወደ ላይ ጥቁር ቀይ ቢጫ ያለው ሰንደቅ አላማ በሰማያዊ ቀለም Grate Germany የሚል ጽሁፍን ተመልክቻለሁና።
ይህ ሰው ጀርመናዊ ዜግነት ያለው ሰው እንደሆን ሳውቅ ይባስ እልህ እና ቁጭቴን ጨመረበኝ።
ካለኝ ትኩርት የተነሳ ''ካጠገቤ እራቅ'' አይነት እይታ አይቶ ትኩረቱን ወደ ስራው መለሰ።
እኔም ቁሜ ከነበረበት ቦታ እራቅ ብየ የሰውየውን ሁናቴ እከታተል ጀመር።
ብዙ ግዜ የውጭ ሀገር ዜጎች እሁድ ከ ቀኑ 9 ስአት በኋላ ከሌሎች ቀናት በተለየ በጣና ላይ የሚያደርጉትን አሰሳና ፍለጋ በዚህ ቀንና ስአት በልዩ ትኩርት ምርምራቸውን እንደሚያደርጉ ሰምቻለሁ።
በእርግጥ ይህ ስአት ለምን እንደሚመርጡት በነጮች ብዙ መላምታዊ ንግርቶች ቢወሩም እውነታው ግን መለኮታዊ ሚስጥር የሚገለጥበት ሚስጥር ስላለው ነው።
#ብዙም ተፈጥሮን የማስተዋል ጥበቡ ስለሌለን አናስተውለውም እንጂ በእለተ ሰንበት ከ9 ስአት በኋላ የጣና ሀይቅ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴው ይቀየራል።
የነፋሱ አነፋፈስ፣ የሞገዱ አጣጣል፣ የማዕበሉ ኡደት፣ ሳይቀር ምህዋሩን ይቀይራል፤ ልዩ የሆነ የእጣን ሽታም ከምስራቅ ና ከምእራብ በኩል ይነፍሳል።
#አባቶች እንደሚያስረዱት ይህ የሚሆንበት ምክኒያት ታላቁ ሔኖክ እንዳለው አለምን የሚመግቡ 4ቱ የሰላምና 8ቱ የመአት ነፋሳት የ 12 ነፋሳት መስኮቶች በእለተ ሰንበት እራሳቸውን እያደሱ ወደ አለም የሚነፍሱት እና አለማቱን የሚመግቡት የመነሻ ምንጫቸው እዚህው ቦታ አካባቢ በዚህው ቀን ና ስአት እንደሆን አበዉ ይናገራሉ።
ከዚህም የተነሳ ብዙ ተመራማሪወችን የሚመርጡት ጊዜ ይህንን ስአት እንደሆን ስለማውቅ ቶሎ ልሄድ አልፈቀድኩም።
ብዙ ጊዜ ጀርመኖች አለም ላይ እራሳቸውን እንደ መላክ የሚያዩ የአሊያንስ ዘር ወይም የወደቁት መላእክት ዘሮች ነን ብለው ስለሚያስብ ከሰው ልጆች እራሳቸውን አግነው ይመለከታሉ።
ስለዚህ ይህንን ጀርመናዊ የሚያስበዉን እና የሚፈልገውን ቀድሜ ማሰብ እና ማወቅ ስችል ብቻ ነው ትኩረት ስጥቶ ስለሚፈልገው ነገር ሊነግረኝ እና ሊያወራኝ የሚችለው ..... የሚል ሃሳብ መጣልኝ።
ከታጨቀዉ ቦርሳ ውስጥ ያየኋቸው መጻህፍቶች እርፍት አሳጠው ያቅበዘብዙኝ ደመር።
ይህ Uthiopia የሚል ጽሑፍ በሶስት መአዘን ውስጥ ተጽፎ የተቀመጠቀት ሚስጥራዊ ኮድ ምን ይሆን የሚል ጥያቄ አይምሮየን ወዲ ወዲያ ይንጠኝ ጀመር።
ከ7 ወር በፊት አንድ መጻህፍን አይቸ ነበር ይህ መጻህፍ ስለ Uthiopia ትርጉም ይገልጻል።
Utopia [juːˈtəʊpɪə] . An imagined place or state of things in which everything is perfect. The
word was first used in the book Utopia (1516) by Sir Thomas More. Synonyms: paradise, heaven (on earth), Eden, Garden of Eden, Shangri-La, Elysium, Zion....ይላል
በአጭሩ ዩትዮጵያ ''UThiopia'' የሚለው ስያሜ 1516 ቶማስ ሙር በተባለ አለማቀፍ ታዋቂ የታሪክ ተመራማሪ የተናገረላት ምናባዊ የምትመስል ሉአላዊት ሀገርን ነው።
ይህ Uthiopia የሚል ስያሜው ትርጉም ሲገልጻት ፍጹም ሰላማዊ ገነት ቦታ፤ የገነት ጠባቂ ህዝብ፤ በማለት ይግልጻታል።
ይህ Uthiopia የሚለው የስም ትርጓሜ ከሶስት መአዘን ክልል ውስጥ እንዲጻፍ ያስፈለገው ነገር ምንድን ነው ሚስጥሩ❓
የሚል ከባድ ጥያቄ ውስጥ ገብቸ በቁመት ዘልግ ያለውን የውጭ ሀገረ ዜጋ በአይነ ቁራኛ እከታተለዋለሁ።
አሁን ዋናው ጥያቄ የሚሆነው ይህ ነው......ይህ ያየሁት እና በሽፋን ገጹ በሶስት መአዘን ውስጥ ያለውችው Uthiopia አንዳች ቁርኝት እንደለው ተረዳሁት።
ስለዚህ በዚህ 12 ኪሜ ምዕራብ አቅጣጫ 5 ኪሜ ሰሜን ምዕራብ በመሀከላቸው 13 ኪሜ ርቀት ያለው የሶስት ማእዘን ክልል ውስጥ አንዳች UTHIOPUA በሚል ትርጉም ጋ ባስገባው የማገኘው ሚስጥራዊ ነገር ሊኖር እንደሚችል ገመትኩ።
ይህም ማለት በ12 km ምዕራብ አቅጣጫ ካለው ክቡራን ገብርኤል እንዲሁም 5 km እርቃ ከምትገኘው ደብር ማርያም በማህከላቸው 13ኪሜ እርቀት ውስጥ ባለው የሶስት ማዕዘን ክልል ውስጥ Uthiopia የሚለው ትርጉም ሳስገባው.........።
በሚገርምና በሚደንቅ ሁኔታ ይህንን ትርጉም ሰጠኝ። UTHIOPIA የሚለው ፍጹም ሰላማዊ የሆነ ገነት ቦታ እና በሶስት መአዘን ክልል ውስጥ ደግሞ የተቀመጠው፤ የዚህ ገነት ቦታ መገኛ ውክል ክልል መሆኑን ተረዳሁ።
በመገረምና በመደነቅ ካለሁበት ፈዝዠ ቀረሁ......❗
ፀሐይ ወደ ማደሪያዋ እየገሰገሰች ጀንበር እየደበዘዘች ነው....።
ሰዉ እራቅ ራቅ ብሎ ከጠቀመጠበት ቦታው እየተነሳ ወደ ማደሪያ ገሰገሰ።
የሀይቁ ማእበል በነፋሱ እየተገፋ በማን አለብኝነት ሿሿሿሿ እያለ ማእበሉን እያስፈነጠር በፍንጣቂ አካሉ ባዶ መሬት ላይ ይዘረራል.... ከሰሜን ከገዳማቱ ደጂ በኩል ጣና የሚያመጣው ነፋሻማ ነፋስ ለነፍስ ሀሴትን ይሰጣል። ፍጹም ሰላም ፍጹም የመንፈስ እርጋታን ያድላል.....።
ወደ ነጩ ተጠጋሁና sir Can I help You? አልኩ በፍጥነት ዞር ብሎ አየኝ እና ምስጋናውን ሰጦኝ እርዳታን እንደማይፈልግ ገለጸልኝ።
በነጩ ከልክ ያለፈ ንቀትና እብሪት ተበሳጨሁ..... በመቀጠል በተሰባበር እንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲህ አልኩት አነተ የምታስሰው እና የምትፈለገው ነገር ቀድሜህ ተረድቸዋለሁ..። በማፌዝ እይታ ተመለከተኝ ስራውን ቀጠል።
I know... where is found The far between To monastery is 13 km 67 degree North west and 23 degree of west........በማለት ደፈር ብየ ነገርኩት።
እኔ ወዳለሁበት እየተመለከተ...What do you say? በማለት ትኩረትን ሲሰጠኝ ተመለከትኩት.. yes sir I know all about your Browsing behind Tana and Uthiopia..... what do you fined in the region of 12 km west 5 km North west and 13 km distant between them? and inside the triangular region what does that mean ''UTHIOPUA ''? ይህ ነጭ ከመቅስፈት የተለየ የመደነቅ ባህሪን አመጣና ስራውን ትቶ ወደኔ ዞር ብሎ '' How can you know about these''? በማለት ተጠጋኝ......
አሁን ትኩረት ሰጥቶ ሊያወራኝ የሚችለውን ሚስጥር ስላለኝ፤ የኤልያንስ ዘሮች ነን ብለው የሚያስቡትን ጀርመናዊ እብሪት ልባቸውን ፤በአቅሜ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ታላቅ እንደሆን የምመሰክረበት የጀብድ መድርክ ላይ የቆምኩ ያክል ተሰማኝ።
ከመነጸሩ ባሻገር የሚታዩ አይኖቹን አጥብቦ እንዴት እኒህን ልታውቅ ቻልክ አለኝ። እኔ ፈጠን ብየ የጠቢባን የአባቶቸ ልጂ ነኝ አልኩት.....ከታጨቀው ቦርሳው ገጿ የበዛ ድሽክነሪ አወጣ፤ መጻህፏ የግእዝ ቋንቋን በእንግሊዘኛ እና በጀርመነኛ ቋንቋ ተርጉማ የያዘች መዝገበ ቃላት ነበር።
ጥራዟ ካማረ መዝገበ ቃላት ውስጥ አንዳች ብጣች ወረቀትን አውጣና በተረጋጋ ና በለሰለሱ ቃላት ጥያቄወችን እንዲጠይቀኝ እና ለጥያቄወች ሁሉ መልስ እንደምሰጠው በሞጸት እና በሽንገላ ጠየቀኝ..
Sorry What does that mean Debre DEDEK?
ደብር ደደክ ምንድን ነው ብሎ ነበር የጠየቀኝ......ነጩ ከጠየቀኝ ጥያቄው አንጻር መደንገጤ ስለቦታው እና ትርጉሙ አንዳች እውነት ላውቅ እንደምችል ተረድቶኛል።
መልስ ከመመለሴ በፊት መጀመሪያ ልጠይቅህ የምፈልገው ጥያቄ አለኝ አልኩት።
ለምን አዚህ ቦታ እንደመጣህ ልትነግረኝ ትችላለህ? አላማህስ ምንድን ነው❓ የምተሰራው ለማን ነው❓
አልኩት ነገሮችን አለባብሶ ለማለፍ ሞከር ቆጣ ብየ ጥያቄየን እንዲመልስልኝ ጠየኩት።
ለመሆኑ ህጋዊ ነህ የኢትዮጵያ መንግስት ያውቅሀል❓
ሰውየው እንደ ንቀትም እየተመለከተ እቃወችን ወደ ቦርሳው መሸከፍ ጀመረ ስልክ ደውሎ መልክት አስተላልፎ ዘጋ። በድጋሚ ጠየኩት Have you License paper? ካልያ ወደ ሚመለከተው የህግ አካል እንሄዳለን በሚል አጥብቄ መያዜን ሲመለከት።
በኢትዮጵያ ኢንባሲ በኩል ተፈቅዶለት በቅርስና ጥበቃ ተቋም ይሁታ ሰውየው እንዲገባ የሚያሳይ የፈቃድ ደብዳቤ አሳየኝ።
ወረቀቱን እንዳየሁ እንዴት እንዲህ አይነት ፈቃድ በኤምባሲ በኩል ይሰጣል ብየ በመገረም ፈዥዠ ቀረሁ።
#ሰውየው ቀጠለ now have you seen my license paper andlegit So tell me Where is Debre dedek❓
አለኝ ይህ ሰው ከዚህ ከሚያስሰው ሚስጥራዊ ቦታ ጋር ደብረ ደደክ የሚል በግእዝ የተጻፈ ስም እንደሚፈልግ ገብቶኛል።
ደብር ደደክን አላውቀዉም ባውቀዉም አልነግርህም❗
ብየ በቁጭትና በብስጭት አንገቴን አቀርቅሬ በዘንባባ በተዋቡ መንገዶች ቁልቁል ወደ ማደሪያየ ወረድኩ።
እንዴት ደብረ ደደክን ሊያውቅ ቻለ❓ ከሚሰራው ስራ ጋ የሚያገናኘው ምን ይሆን....በእርግጥ ስለ ደብረ ደደክ ምንም አይነት መረጃ እና ማስረጃ ሊያገኝ እንደማይችል አውቃለሁ።
ምክኒያቱም ይህ ስያሜ ምንን እንደሚያመለክት በብዙወች ዘንድ እንደማይታወቅ ቦታው በሚስጥር እንደሚጠበቅ አውቃለሁ። ቦታው የተለየ መንፈሳዊ ሂወት ያለበት የኢትዮጵያ ሚስጥራዊ ዶሴዋ ጥንስስ መነሻም መድረሻውም እዚህ ቦታ ነው ልዪ መለኮታዊ ጠብቆት ያለበት ወደ ፊት በታላቅ ክብር ና ሞገስ የሚገለጥ ልዩ የሰማያውያን እና የምድራውያን የመገናኛ የኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ቅዱስ ቦታ ነው።
በብዙሃኑ ዘንድ ከጥቂቶች በስተቀር የሰው ይሁን የቦታ፤ የተራራ ይሁን የኮረብታ ፤የገዳማቱ ይሁን የምደረ በዳ፤.....አይታወቅም ያለ ግን የተሰወር ድንቅ ቦታ ነው።
ይህ ነጭ ሊያገኘው እንደማይችል እርግጠኛ ሁኛለሁ። ምናልባት በሰረቁት የብራና መዛግብቶቻችን ጠቋሚነት የደብረ ደደክን መገኛ ቢጠቁሙት እንኳ ልዩ መለኮታዊ ጥበቃ ያለበት የማይደፈር ቅዱስ ስፍራ መሆኑን ሰምቻለሁ....።
#ደብረ_ደደክ ማለት ደጋማው ተራራ የሚል ስያሜን ይሰጣል።
ስለዚህ አካባቢ ከዚህ ቀደም እንደገለጽኩት ከሚመጣው ከንጉስ ቴውድሮስ የዘር ሀረግ መነሻ ጋር አያይዠ እንዲሁም በተለያየ ምክኒያት ጠቁሜያችሁ አለሁ ምድረ ጻድቃን እንደሚባልም ገልጨዋለሁ።
እንግዲህ ለጠቢብ ሰው አንድ ቃል ትበቃዋለች ነውና መርምሩ.....
#ጣና ላይ ያየሁት በሶስት መአዘን ክልል ውስጥ Uthiopia የሚል ታምራዊ ትርጉም፤ መለኮታዊው የደብር ደደክ ሚስጥር በህሊናዬ እያርመሰመስኩ አንገቴን ወደ ምድር አቀርቅሬ በተዋቡ ጎዳናወች፤ ስላየሁት ነገር በሀሳብና በቁጭት በመገረምና በመደነቅ ለምን እና እንዴት ጥያቄወች ታጂቤ መነገዴን ቀጠልኩ።
የታዋቂው ተመራማሪ የቶማስ ሞሪ የዩትዮጵያ ትርጉም ከሶስት ማእዘን ክልል ውስጥ ጋ በማቀናጀት የሰጠኝን ፍንጭ ሳስብ፤
ይህ ህልም የሚመስል እውነት አንድ የመጻህፍ ቅዱስ ቃል አስታወሰኝ።
ኦሪት ዘፍጥርት ምእራፍ 2 ቁጥር 10 ጀምሮ እንዲህ ይላል ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር።
''አንደኛው ወንዝ ስም ኤፊሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፤
የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል''። ይላል
ስለዚህ ገነትን የሚያጠጡ 4ተ ማይ አፍላጋት አሉ፤ ይህ ግዮን የተባለው ወንዝ ከጣና ተንተረሶ የሚገኘው ገነትን የሚያጠጣው አባይ ነው።
ውሀ በተፈጥሮ ህግ ከታች ወደ ላይ ይፈስ ዘንድ ተፈጥሯዊ ህግ አይፈቅድም ስለዚህ ይህ ግዮን የተባለው አባይ ገነትን የሚያጠጣው እንዴት ነው?
ስለዚህ ገነት ምድር ላይ ረባ ወይም በትንሹ ከፍ ብላ ትገኛለች ማለት ይቻላል፤ ምክኒያቱም ከምድር የሆነው አባይ ወይም ግዩን ወደ ገነት እንደሚፈስ ቅዱስ መጻህፍ ይናገራልና።
ገነት ምድር ላይ ካለች የት ቦታ❓ የት ሀገረ❓ የት ስፍራ❓ ለሚለው ጥያቄ የነጩ ሳይንሳዊ መርምር መንገድ በትንሹ መለኮታዊ ሚስጥርን ሳይገልጥልን አልቀረም።
#አባቶች ሲናገሩ ገነት ምድር ላይ ጣና አካባቢ አንድ ክንድ ከስንዘር ረባ በህቡ ትገኛለች ይላሉ።
ጥያቄው በዚህ ሶስት መአዘን ክልል ውስጥ ያለችው ቦታ አባቶቻችን የነገሩን የገነት መገኛ ናት ወይስ ሌላ ሚስጥራዊ ዳራ አለው የሚለው ነው❓
ይህንን ለመመለስ ሳይንሳዊ ትንታኔ ሳይሆን መለኮታዊ እረዳትነት ያስፈልጋል።
ይህንን የማወቅ ጸጋና እውቀትም ስለሌለን ከአባቶቻችን እግር ስር እንፈልገው እናገኘውማለን።
#በእውነት የአበዉ የአባቶቻችን የእውቀትና የጥበብ መንገዷ የት ናት❓ የአባት ፍኖት የጠፋው ትውልድ መቃዋ እንደተሰበር ባህር ላይ ነፋስ እንደሚያወዛውዛት መርከብ ማለት ነው። ነፋስም ይነፍሳል መቃዋው ተሰብሯል መንገዷም በነፋሱ አነፋፈስ ይወሰናል!......
በቲና በቀለ
ባህርዳር







No comments:
Post a Comment