ኢየሱስ ክርስቶስ፦
ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነ፤ (ማቴ ፳፰፥፲፱)
ከአብ ጋር ዕሪና ያለው፤ (ዮሐ ፲፥፵)
ዓለም ሳይፈጠር የነበረ፤ (ዮሐ ፩፥፩)
ዓለምን የፈጠረ ፈጣሪ፤ (ዕብ ፲፩፥፪)
በቅድምና ከአብ የተወለደ፤ (መዝ ፪፥፯)
ሥጋ እንደሚለብስ በራሱ የመሰከረ፤ (ዘፍ ፫፥፳፪)
ወደ ገነት ገብቶ አዳምን የፈለገ፤ (ዘፍ ፫፥፱)
በነቢያት አስቀድሞ የታወቀ፤ (ኢሳ ፵፪፥፩-፭)
አብ ልጄ ብሎ የጠራው፤ (ማቴ ፲፯፥፭)
ምሳሌ የተመሰለለት፤ (፩ኛ ቆሮ ፲፥፬)
ሱባዔ የተቆጠረለት፤ (ገላ ፬፥፬)
በብሥራተ መልአክ የተጸነሰ፤ (ሉቃ ፩፥፴፩)
ሥጋን የለበሰ (ማቴ ፩፥ ፳፫)
ቁራኝነትን ያጠፋ፤ (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳፬)
በማሕጸን ጽንስን ያዘለለ፤ (ሉቃ ፩፥፵፩)
መላእክት የዘመሩለት፤ (ራእ ፬፥፰)
ተጸንሶ ሳል በሰማይም ያለ፤ (ሉቃ ፪፥፲፬)
በሕቱም ድንግልና የተወለደ ፤ (ማቴ ፩፥፳፫)
ያለ አባት ከሴት ብቻ የተወለደ፤ (ገላ፥ ፬፥፬)
አለቅነት በጫንቃው ላይ ያለ፤ (ኢሳ ፱፥፮)
ከሁለት አካል አንድ አካል የሆነ፤ (ዮሐ ፩፥፲፬)
ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ፤ (ዮሐ ፪፥፲፱)
ንጉሥ ሆኖ የተወለደ፤ (ማቴ ፪፥፩-፪)
ለቤዛነት የተሰደደ፤ (ማቴ ፪፥፲፬-፲፭)
መምህር ሆኖ ሳለ ለመማር የሚሻ፤ (ሉቃ ፪፥፵፮)
በዮሐንስ እጅ የተጠመቀ፤ (ዮሐ ፫፥፲፭)
ላመኑት የዘላለም ሕይወትን የሚያድል፤ (፫፥፴፮)
የአብ ኃይሉና ቀኙ የሆነ፤ (፪ኛ ጤሞ ፫፥፭)
ጥምቀትን መዳኛ ያደረገ (ማር ፲፮፥፲፮)
ወንጌልን የሠራ፤ (ዮሐ ፩፥፲፯)
አዲስ ቃል ኪዳን የገባ፤ (ማቴ ፳፮፥፳፮)
የዓለሙን ኃጢአት የሚያስተሠርይ በግ፤ (ዮሐ ፩፥፳፱)
መጾምን ያስተማረ፤ (ማቴ ፬፥፪)
ፍቅርን የሰበከ፤ (ዮሐ ፲፭፥፲፫)
ከሙታን መካከል ተለይቶ የተነሣ፤ (ማቴ ፳፰፥፮)
ኦሪትን የፈጸመ፤ (ማቴ ፭፥፳፩-፵፰)
ከአብርሃም በፊት የነበረ፤ (ዮሐ ፰፥፶፰)
አልፋና ዖሜጋ የሆነ፤ (ራእ፩፥፲፯)
ምሕረቱ እጅግ የበዛ፤ (ዮሐ ፰፥፲፩)
ሐዋርያትን የጠራ፤ (ማቴ ፭፥፲፱-፳፩)
ሥጋውንና ደሙን የሰጠ፤ (ማቴ ፳፮፥፳፮)
ዓርአያነትን የሰጠ፤ (፲፫፥፲፭)
አዳኝ ሆኖ የተገለጠ፤ (ሉቃ ፱፥፶፮)
ለአዳም ቤዛ የሆነ፤ (ኤፌ ፩፥፯)
ይቅርታን ያስተማረ፤ (ሉቃ ፲፯፥፬)
ገነትን በደሙ የከፈተ፤ (ማቴ ፳፭፥፴፭)
፮ቱ ትዕዛዛተ ወንጌልን የነገረ፤ (ማቴ ፳፭፥
ሞትን ያሸነፈ፤ (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፶፬)
በመላእክት የተመሰገነ፤ (ማቴ ፬፥፲፩)
በሐዋርያት የተሰበከ፤ (ሐዋ ፪፥ ፳፪)
ፍርድ ሁሉ ለእርሱ የሆነ፤ (ዮሐ ፭፥፳፯)
ሊቀ ካህን ሆኖ የተገለጠ፤ ( ዕብ፯፥፳፮)
አምላክነት ገንዘቡ የሆነ፤ (ሮሜ ፱፥፭)
በሰውነቱ የሚራብ፤ (ማር ፲፩፥፲፪)
በአምላክነቱ የሚያጠግብ፤ (ሉቃ ፱፥፲፯)
ሊያገለግል የመጣ፤ (ማቴ ፳፥፳፰)
ሕይወትና ትንሣኤ ተብሎ የሚጠራ፤ (ዮሐ ፲፩፥፳፭)
እውነተኛ የበጎች ጠባቂ፤ ( ዮሐ ፲፥፲፩)
የቤተ ክርሰቲያናችን ራስ፤ (ኤፌ ፬፥፲፭)
ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ፤ (፪ኛ ጴጥ ፩፥፲፮-፲፱)
ሙሴና ኤልያስን ያነጋገረ፤ (ማር ፱፥፬)
ለሙሽራይቱ ሙሽራ የሆነ፤ (ዮሐ ፫፥፳፱)
ዳግም ለመምጣት ቀጠሮ የያዘ፤ (ራእ ፳፪፥፲፪)
ትንቢተ ነቢያትን የፈጸመ፤ (ማቴ ፩፥፳፫)
የነቢያት አለቃቸው፤ (ሉቃ ፯፥፲፮)
የታመነ ምስክር፤ (ማቴ ፲፤፴፪)
ከአባቱ የሰማውን የሚናገር፤ (ዮሐ ፲፭፥፲፭)
አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የገባ፤ (ዕብ ፱፥፲፪)
ገዳማዊ ሕይወትን የጀመረ፤ (ማቴ ፬፥፩)
ተባሕትዎን የወጠነ፤ (ማቴ ፰፥፳)
ጋብቻን ተገኝቶ የባረከ (ዮሐ ፪፥፪)
እናቱን እነኋት ብሎ የሰጠ፤ (ዮሐ ፲፱፥፳፯)
የመስቀል ሞትን የሞተ፤ (ፊል ፪፥፰)
በብዙ ወገን የተገፋ፤ (ዮሐ ፭፥፲፮)
ደዌአችንን የተሸከመ፤ (ኢሳ ፶፫፥፬)
ነፍሱን ስለ እኛ የተወ፤ (ዮሐ፲፱፥፴)
ቅዱሳንን አብዝቶ የሚወድ፤ (ማቴ ፲፥፵)
በክብር ወደ ሰማይ ያረገ፤ (ሐዋ ፩፥፱)
ለነፍሳት ግዕዛንን የሰበከ፤ (፩ኛ ጴጥ ፫፤፲፱)
ለደካሞች ማረፊያ የሆነ፤ (ማቴ ፲፩፥፳፰)
በግርማ መለኮት የሚመጣ፤ (መዝ ፶፥፫)
ሙታንን የሚያስነሣ፤ (ዮሐ ፮፥፵፬)
የጌቶች ጌታ የሆነ፤ (ሮሜ ፲፥፲፪)
ከእውነቸኛ ብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ (ዮሐ ፰፥፲፪)
ፈራጅነት ገንዘቡ የሆነ አምላክ ነው! (ራእ፳፪፥፲፪)
እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን!

No comments:
Post a Comment