ማውጫ
- #Editor (1)
- ፩. ታሪክና ህብረተሰብ (10)
- ፪. የህይወት ክህሎት (4)
- ፫. ነጻ ሃሳብ (6)
- ፬. ቤተ-አምልኮ (16)
- ፭. ኪነ-ጥበብ (9)
- ፮. ውብ ሀገር (7)
- ፯. አገራዊ ጉዳዮች (2)
- ፰. ሳይንስና ቴክኖሎጅ (ሳይቴክ) (8)
- ፱. ንግድና ኢኮኖሚ (9)
- ለቤተ-መፅሃፍትዎ (4)
- ስራ-Vacancy (1)
- የጉዞ ማስታወሻ (1)
Tuesday, 21 December 2021
ከላሊበላ ሰማይ ስር
Monday, 6 December 2021
ሰብአ ሰገል
የሰብአ ሰገል ምንነት፥ ታሪክ፥ ኮከቡ፥ ጉዟቸው፥ በስተመጨረሻው መሰወራቸው
አባታችን አዳም በዕለተ አርብ በነግህ ከተፈጠረ በኋላ እናታችን ሔዋን በሳምንቱ አርብ በዘመናችን አነጋገር 3 ሰዓት ላይ ከግራ ጎኑ ተፈጠረች። በገነትም 7 ዓመት ከ3 ወር ከ 17 ዕለታት ካሳለፉ በኋላ ሕግን ተላልፈው እፀ በለስን በመብላታቸው ከገነት ተባረሩ። በዚህ ግዜ አምላካችን እግዚአብሔር ለአዳም የተስፋ ቃል ሰጠው፤ እርሱም ከልጅ ልጅህ ተወልጀ ከ5 ቀን ከመንፈቅ በኋላ አድንሃለሁ የሚል ቃል ነበረ። ይህ የተስፋ ቃልና ከመላእክት ለአዳም የተሰጡትን ስጦታዎች አዳምና የልጅ ልጆቹ ሲቀባበሉት ቆይቶ ከካሕኑ መልከጼዴቅ እጅ ላይ ደረሰ። ከመልከጼዴቅ አንዳንዶቹ ለአብርሃም ተሰጠ ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ለኢት-ኤል ተሰጠ ይላሉ።
Thursday, 4 November 2021
ኤክሳይዝ ታክስ ምንድነው?
ኤክሳይዝ ታክስ የቅንጦት እቃዎች ሆነው ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሰረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ፣ እንዲሁም የሕብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱና ማህበራዊ ችግር የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል የተጣለ ታክስ ነው፡፡
Friday, 1 October 2021
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በበረራ
ስለ ለውጥ ያለኝ አተያይ
መለወጥና ስኬታማ መሆን የምትችለው በማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ የምትጓጓለት አንድ ሐሳብ ካለህ አሁኑኑ ጀምረው። ምክንያቱም የምትማርበት ብቸኛው መንገድ ይሄ ነው።
You only learn by doing, so if you have an idea you crave to explore, start now—that’s the only way to learn.
በአንድ አመት ውስጥ የምትሆነው በእያንዳንዷ ቀናት የምታደርጋቸው ልማዶችን ውጤት ነው። (አንተ የልማድህ ውጤት ነህ። እንደሚባለው።)
Who you’ll become in a year’s time is a summation of your daily habits and what you do everyday, today.
እድገት የሚመጣው በሙከራ ነው። ነገሮችን በአዲስ መንገድ ማድረግና መሞከር ስታቆም፣ ማደግህንም ታቆማለህ።
Growth is a function of experimentation; when you stop testing new ways of doing things, you stop growing.
ታላቅ የሚያስብለው ውጤቱ ሳይሆን ሂደቱ ነው። እንድሁም፣ በማንኛውም ዘርፍ ላይ ውጤታማ ለመሆን ፅናትና ወጥነት ያስፈልጋል።
Greatness is in the process, not the result—to be great at anything, you must be consistent.
ብዙ የለውጥ በሮች በዙርያህ አሉ። ደስተኛ ካልሆንክ፣ አዳዲስ በሮችን ለመክፈት ሞክር።
The doors to change are all around you; if you’re unhappy, try opening a new door in your life.
የፈጠራ ችሎታህ ውጤታማ የሚሆነው ቀላል ሲሆን ነው። ነገሮችን አታወሳስባቸው።
Creativity wins when it’s simple—don’t complicate things.
ለማመስገን ሁሌም ምክንያት አለህ!
You can always find a reason to be grateful.
Thursday, 30 September 2021
Wednesday, 1 September 2021
ሀብታም ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?
ሀብታም ለመሆን የሀብታሞችን ባህሪ መላበስና የድሆችን አመለካከት ደግሞ ማስወገድ ያስፈልጋል። በዚህ ፖስት ብዙ ሰዎችን በድህነት ቀፍደው የሚያስቀሩ ስድስት የድህነት ባህሪያትን እንመለከታለን፤ ምክንያቱም የስኬት አንዱ መሰረት የውድቀት መንስኤዎችን ለይቶ ማወቅ ነው። እነዚህ ስድስት ባህሪያት የሚተገብራቸውን ሰው ሀብታም፣ የማይተገብራቸውንም ደግሞ ድሃ የሚያደርጉ ናቸው፣ ስለሆነም እነዚህ 6 ልማዶች ሀብታም እንዲትሆን ይረዱሃል ማለት ነው። የውድቀት መንስኤዎችን ለይተን ስናውቅ እግረ መንገዳችንን የስኬት መሰረቶችንም እንማራለን።