(በቲና በቀለ)
ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ አፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ በቅብዓ ነገሥት ከብረው ለነገሡ ደጋግ ነገሥታት ኃይለ እግዚአብሔርን የሚያገኙባቸው በርካታ የአሸናፊነት ሚስጥር የንጉስነት ክብር የሚገለጥበት ጥንታዊያን ቅዱሳት መካናት ከሆኑት ከ፬ቱ ጥንታዊያን መናብርተ ጽዮን መካከል አንዷ ናት።
አገር እንደ አገር ለመቀጠል በእወቀት በእምነትና በአመክንዩ የተዋጀ ማህበረሰብ መፈጠር ተቀዳሚ ሚና ነው።
እውነትን ፍለጋ ከያለንበት ተሰባስብን የተዳፈነን ታሪክ ከተዳፈነበት የተሰወረን እውነት ከተሰወረበት ልንገልጥ ተነስተናል.... ኢትዩጵያ እውነተኛ ማንነቱ ወደ ተዋቀረበት ስፍራ እንጓዝ ዘንድ አብራችሁ ተከተሉኝ።
ከደብረ_ሮሀ ላሊበላ ተነስተን ግማደ መስቀሉ ካረፈባት ግሸን ማርያም ብንጓዝ ወረሂመኖን ተሳልመህ አምሐራ ሳይቷ ተድባበ ማርያምን ይዘን በቦረናና ወግዴ ርዕሰ አድባራትን ቃኝተን ከለላ ጥንታዊውን ጋስጫ ጊዮርጊስን ጎብኝተን ወረኢሉና ጃማን አብያተ ክርስቲያናትን አይተን እስከ የጁ ብንጓዝ ወሎ የተገነጣጠለ ሳይሆን እንደ ሰንሰለት የተያያዘ የተጋመደ ከኢትዮጵያ መዝገበ ሚስጥር ቦታወች ዋናው ያልተነገረ የሚስጥርና ታርክ ባለቤት ነው❗
ከደሴ 228 ኪ.ሜ ከወረዳዉ ሳይንት ከተማ አጅባር በስተሰሜን ምስራቅ 25 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በ11° 06′ 87″ ከምድር ወገብ ሰሜንና 30° 45′ 20″ ምስራቅ ጅ.ፒ. ኤስ ከባህር ጠለል ወለል በላይ 8,458 ጫማ ላይ እገኛለሁ...፡፡
አለማቀፍ የታሪክ ምሁራን የምርምር አይነ የእውነት መንገድ ጠቋሚ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ የተወሰነባት አምሳለ ገነት ድንቅ ምድር። ታሪክ ሃይማኖት ስርአት ትውፊት አምልኮ ለኢትዮጵውያን የለገሰች ኦሪትን ተቀብላ ለሐዲስ ያስተላለፈች የኢትዮጵያ ቀደምት አውደ ምህረት።
ደብሯ ዙሪያዋ ገደል ሆና በግራና ቀኝ በጉንዳና ገዳማይ ጅረቶች እንዲሁም በሽሎ ወንዝ ታጅባ የምትገኝ ዉብ የታሪክ አምባ ነች፡፡ አምባዉ ለመዉጣት 12 በሮች አሉት፡፡ ፊትበር፣ ቦካ፣ ገተም፣ ሞገራ ግራኝ፣ ታሪኳ፣ የዘንጌ፣ አሳስት፣ አጎና፣ አምጣ ፈረሴን፣ አህያ መደብለያ እና ጌለት በሮች መግባት ይቻላል❗
ተድባበ ማርያም ቤተክርስቲያን
የጥንታዊት ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአማሐራ ሳይንት ወረዳ የምትገኘው ጥንታዊት ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም የተመሰረተችው በዘመነ ብሎይ በፈቃደ እግዚአብሔር በቀዳማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግስት 982 ዓመተ ዓለም ተመስርታለች፡፡ በመፅሐፈ ሱባኤ ዘአማኑኤል ካልእ ገጽ 2)6 ላይ እንደተጻፈው ሌዋዊያን ካህናት ከእስራኤል በአዛሪያስ መሪነት የጁን አልፈው ከዛሪዋ አማሐራ ሳይንት ደረሱ፡፡ 12 በር ባለው ተራራ ላይ ለእግዚብሔር ቤተ መቅደስ ከሰሩ በኋላ ግማሾቹ ደብር ደባብ እንበላት አሉ አዛርያስ እና የዳዊት የወንድም ልጆች ሳቤቅ ይህቺማ የኢየሩሳሌም የዳዊት መታሰቢያ ከተማ ትሆን ዘንድ ተድባበ ጽዮን እንበላት ብለው እንደሰየሟት ይነገራል፡፡ በዘመነ ሐዲስ ክርስትና ሲስፋፋ አማሮች ተድባበ ጽዮን የሚለውን ስያሚ እንዲቀይሩ የአክሱም ነገስታት አሰገደዷቸው ነገስታቱም አብረሃ ወአጽበሃ ተድባብ ጽዮንን ተድባበ ማርያም ብለው ሰየሙ፡፡ ትርጓሜውም ለእግዚአብሔር የተመረጠ ከፍተኛ ቦታ ማለት ነው፡፡
ርዕስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም በብሉይ ኪዳን ስለመመስረቷ ምስክር የሚሆኑ አንዳንድ የኦሪት ሥረዓቶች ሲከናወኑ ይስተዋላሉ ታቦታቱ በበሚነግሱበት ወቅት በምስራቅ ያሉ ምዕመናን ነዋያተ ቅዱሳቱን ይዘው በምዕራብ ካህናት ተሰልፈው በሰሜን ያሉ ምዕመናን መጋረጃን ይዘው በደቡብ ያሉ ምዕመናን ጎራዴውንና ካስማውን ይዘው መንቀሳቀሳቸው በኦሪት ዚሁልቁ ፪፣፫-፬ ያለውን የኦሪት ሥርዓት ያመለክታል በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን ክርስትና በ34 ዓ.ም በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ከተሰበከ በኋላ እና ሚስጢራተ ቤተክርስቲያን የጌታችን የመዳሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ማክበር ጥምቀትንና መሰዋዕተ ወንጌል መፈፀም የጀመሩት ወንድምማማቾቹ ደጋግ ነገስታት አብረሃ ወአጽብሃ በ330 ዓ.ም አካባቢ ነው፡፡ በዚህም ተድባበ ማርያም እነዚህን የሐዲስ ኪዳን ሥርዓቶች በመፈፀም ቀዳሚዋ ናት፡፡ በብሉይ ዘመን መስዋዕተ ኦሪት ከተሰዋባቸው መካከል አክሱም ጽዮን& ተድባበ ጽዮን የዛሬዋ ተድባበ ማርያም፣ መርጡለ ማርያምና ጣና ቂርቆስ ይጠቀሳሉ፡፡ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከአባቱ ከንጉሡ ከሰሎሞን መንግስት ተቀብሎ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ 4 መናብርት ጽዮን ይዞ መጥቶ ነበር፡፡
1. የአክሱም ጽዮን ንቡረ ዕድ
2. የተድባበ ማርያም ፓትርያርክ
3. የመርጡለ ማርያም ርዕሰ ርዑሳን
4. የጣና ቂርቆስ ሊቀ ካህናት ናቸው፡፡
3ስቱ በእመቤታችን ምሳሌ በጽዮን ስም አራተኛው የሊቀ ካህናቱ ታቦት ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ታድያ ታላቁ ሚስጥር ያለው እዚህ ላይ ነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ጽዩን ከእስራኤል ስትወጣ ሌዋውያኑ ጭምር ከአስራሁለቱ ነገደ እስራኤል ከያይቆብ ዘር የወጣው በእመቤታችን በኩል የክርስቶስ የዘሩ ሃረግ ከሆነው የዳዊት ልጂ ሰሎሞን የሰሎሞን ልጂ ሚኒሊክ ጸጋ ነገስትን ወርሶ ከአምስቱ ሚስጥራዊ ውርሶች ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጣ።
ጽዩን ከመንበሯ ተነስታለችና ያኔ ጸጋ ከ እስራኤል ለቀቀ ህዝቡም በአለም ተበታተኑ በአህዛብም ግዞትም ወደቁ። ያኔ ንግስናው ወደ ኢትዮጵያ ዞር ስርአተ አምልኮም የኦሪት የክህነት አገልግሎቱም የሌዋውያን የንግስና ስርአቱም የነገደ እስራኤልን ሆነ።
ቀዳማዊ ምኒልክን ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 12.000 መሣፍንትና መኳንንት ወይዛዝርት 1.500 በተግባረ ዕድ የሰለጠኑ የወርቅና የብር፣ የብረትና የመዳብ፣ እንዲሁም የነሐስ አንጥረኞች አዋቂዎች ጠቢባን ፀበርተ ዕፀውና ወቀርተ አዕባን ናቸው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያ ገብተው በየክፍለ ሀገሩ ሥራቸውን ሲጀምሩ አክሱም ጽዮን ትግራይ ላይ ስትቀር የዳዊት የወንድም ልጅ ሳቤቅ የሰሎሞን አጎት ከመጀመሪያው ፓትርያርክ አዛሪያስ ጋር ተከዜን ተሻግሮ አምሐራ ሳይንት ደረሰ፡፡ የአሁኗ ተድባበ ማርያም ካለችበት ላይ ሲደርስ ቤተ እግዚአብሔር መሥራት ጀመረ፡፡ ቦታዋንም በሀገሩ ስም ገሊላ ብሎ ጠራት፡፡ ፓትርያርክ አዛሪያስ ደስ አለውና ስሙን በቡራኬ አፀደቀለት፡፡ ለዚህችውም ተድባበ ጽዮን ቤተ መቅደሱን ሰርቶ ሲጨርስ ከሌዋውያኑም ከካህናቱም ከፍሎ መስዋተ ኦሪት የሚሰው ካህናትና ሌዋውያንንም ሾመ፡፡ መስፍኑ ሳቤቅ ቤተልሄማዊም በገፀ ንጉስ በወርቅ ወንበር የሚቀመጥ ነበር፡፡ ከዚህ ላይ ገሊላ ብሎ ከሰየመ በኋላ አገሮቹን አሻግሮ እያየ በሀገሩ ምሳሌ ይሰማቸው ጀመር፡፡ ደብረ ዘይት፣ ኬብሮን አሁን ከቀን ብዛት የተነሳ ህዝቡ ኬብሮንን ከሚኖር ይለዋል ይኽውም ከተድባበ ማርያም አባ በር ወደ ምስራቅ ያለውን መግቢያ ነው፡፡ ወደ ቀኝ በኩል ተመልከተና እያሪኮ ትባል አለ ከቀን ብዛት ግን ሕዝቡ እያሪኮን አራሆ ይሏታል ቀጥሎ ኢየሩሳሌም ቀጥሎ ሎዛ ከዚህ ከሎዛ በላይ ታቦር አለው ይኸውም በአፄ በዕደ ማርያም ዘመን መግስት የተነሱት የቅኔ ፈጣሪዎች እነ ዮሐንስ ገብላአዊ፣ እነ ሠምራ አብ፣ እነ ወልደ ገብርኤል እነ ደቅ እስጢፋ የነበሩበት ነው፡፡
ከታቦር ቀጥሎ ሳይንትን ጨርሶ ወደ ቦረና መግቢያ ላይ ሊባኖስ፣ ደማስቆ፣ አርሞንኤም፣ ደብር ፋራን፣ በስተ ሰሜን በኩል ኮሬብ፣ ቃዴስ ደብረ ፍጌህ& ቂሣርያ& ቢታኒያ& ጋዛ & ጎልጎታ፣ ፌልስጥኤም ወዘተ ተብለው ተሰይመዋል፡፡ ይኸውም መታሰቢያነቱ ለ12 ነገደ እስራኤል እንደሆነ ይነገራል፡፡ ተድባበ ማርያም ከአክሱም ቀጥላ ሁለተኛዋ መናብርተ ጽዩን ናት፡፡ በሥርዓቱም መስረት የአክሱም ጽዮን አስተዳደሪ ንቡር ዕድ የተደባበ ማርያም አሰተዳደሪ ፓትርያርክ የመርጡለ ማርያም አስተዳደሪ ርዕስ ርዑሳን የጣና ቂርቆስ አስተዳደሪ ሊቀ ካህናት በመባል ይጠራሉ፡፡ ከቀዳሚዊ ምኒልክ ጀምሮ በየዘመኑም ለሚነግሱት ነገስታት ቅብዐ መንግስቱን በመቀባት ሁሉም የየራሳቸው ድርሻ ሲኖራቸው 1ኛ የአክሱም ንቡረ ዕድ ከቀዳሚ ምኒልክ ጀምሮ በተያያዘው መሠረት ማንኛውም ንጉስ ሲነግስ ከስራት ንግስ በኋላ ዘውዱን በክብር ከራሱ ላይ ያቀዳጃል፡፡ በዚህም ሃይልና ጸጋ ይቀዳጃል
2ኛ የተድባበ ማርያም ፓትርያርክ በትረ መንግስቱን ህለተ ወርቁን ጠላትህን በእጅህ ጭብጥ በእግርህ እርግጥ አድርገህ ግዛ ብሎ በቀኝ እጅ ያሲይዘዋል፡፡ በዚህ እውነተኛ ፍርድ ፍረደበት የእዚአብሔርን ህግ ጠብቅነት የተበላሸውን አድስበት የታደሰውን አጽናበት አመፀኞችን ቅጣበት ፍቃዶኞችን ሹምበት በዚህ ሁሉ አምላካችንን አገልግልበት ብሎ ይሾመዋል፡፡ በዚህም ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሃይል ይሆነዋል
3ኛ የመርጡለማርያም ርዕስ ርዑሳን ልብስ መንግስቱን ያለብሰዋል፡፡
4ኛ የጣና ቂርቆስ ሊቀ ካህናት ቅብዐ መንግስቱን ይቀባዋል፡፡ ይህ ሁሉ ስርዓት የሚደርሰው 40 ቀን ለስርዓተ ንግስ የተወሰነው ከብሉይና ከሐዲስ ኪዳን የተውጣጣው ፀሎትና መሥዋዕት ካረገ በኋላ ነው፡፡
ታላቁ እውነት እዚህ ላይ ነው ኢትዮጵያ ከ እስራኤል ተላልፎ የተሰጣትን ክብረ እና በረከት ከ1966 በኋላ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ በሚል የፖለቲካ ሂደት ከስርአቷ የወጣ መንገድ ጀመረች። ከዚያም ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ በታሪኳ ገጥሞት የማያወቀውን ወረደት እያስተናገደች ነው።
#ጽዮን ከእስራኤል ስትወጣ እስራኤላውያን እስራኤልን አጧት ግፍ መከራ ሞት ስቃዮ መሰደድ ሆነ እጣፈንታቸው ኢትዮጵያም የጥንት የእስራኤላወያኑ እጣ ፈንታ ደርሷታል። ታድያ ብዙሃኑ አስራኤልን ሙሴ እንደታደገው ሁሉ ኢትዮጵያን የሚታደጋት ንጉስ ይመጣል እየተባለ በእጂጉ ይነገራል የሚመጣጣበት ጊዜ ሁሉ ተወስኖ የሚነገር ትንቢት ሰምተናል።
ይህ ነገረ ትንቢት ለህዝብ ይፋ የወጣበት የራሱ የሆነ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም ላልተገባ አላማ በ ቤተክርስቲያኒቱ ስም ሲነገር እንሰማለን።
በእርግት ከሰባ ነገስት የዘር ሃረጉ የሚመዘዝ ንጉስ በኢትዮጵያ እንደሚነግስ ቢነገርም ሰወች ራሳቸው በተረዱት መልኩ ሃሳቦን ሲጠመዝዙ ይታያል። በመሰረታዊነት ስለ ንጉሱ የሚናገው ታላቅ የትንቢት መጻህፍ ጣና ቂርቆስ ያለ ቢሆንም ይህ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሰወች ከተመለሱ ንስሃ ከገቡ ታላቁ ንጉስ እንደሚነግስ ይናገራል ሌላው ጊዜው በዚህ የሚል ግን የለውም ..ካልተመለሱስ ነው ጥያቄው ?
ይህ ታላቅ መጻህፍ የኢትዮጵያ ሃይማኖት የአለም ሃይማኖት ሁሉ እንደሚሆን ይናገራል እንጂ ብዙሀኑ እንደሚሉት በጊዜና በቦታ የተገደበ እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል።
በእነዚህ አራት መናብርተ ጽዮን ያልነገሰ ንጉስ ጠላት አጥፍቶ፣ አገር አስፍቶና በሀይማኖት ፀንቶ ሊኖር አይችልም፡፡ እነዚህ በአሉበት ከነገሰ ግን ሀገር ለመጠበቅ ሁሉን ነገር ለማድረግ ይቻለዋል፡፡ ይህውም ከቀዳማዊ ምኒልክ ሲያያዝ መጥቶ እስከ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድረስ በነዚህ 4 መናብርተ ጽዮን ግርማዊነታቸው ነግሰው 43 ዘመን በክብረ እና በሞገስ ገዝተዋል፡፡ ግርማዊነታቸው ሲነግሱ የነበሩት የእርስ አድባራት ወገዳማት አሰተዳደሪ ለግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሰይፈ መንግስትና ህለተ ወርቅ ያስጨበጡና ያስታጠቁ ፓትርያርክ አፈወርቅ ይባሉ ነበር፡፡ ከላይ በርእሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ዘመን ኦሪት አለፈና በክርስቶስ ልደት ዘመን ሐዲስ እንደተተካ በ337 ዓ.ም በቅዱሳን ነገስታት አብረሃ አጽበሃ ዘመን በጥያቄ ጭምር ተድባበ ጽዮን የሚለው የምሳሌ ስም አልፎ በአማናዊነት ድንግል ስም ተድባበ ማርያም ተባለች፡፡ ነገስታቱ አብርሃ አጽብሃም የኦሪታዊት ተድባበ ማርያምን ክብር ከፍ በማድርግ ለስርዓተ ቁርባንና ለሐዲስ ኪዳን ለተዋህዶ ሐይማኖት መሰረት ትሆናቸው ዘንድ 318 መዘመራን ካህናትና ዲያቆናት ከካህናተ ኦሪቱ ጋር ያለውን ሐዲስ ኪዳን የሚያስተምሩ መምህራን ተክለው ከቀዳሚው ምኒልክ ዘመን በሚልጥ ክብር አክብራው እንበረምን ህዝበ ቀደስ አሰኝተው በፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ሥልጣን አጽንተው የተደባበ ማርያም ክብር እስከ አሁን ድረስ የቆየውን ማዕረግ የመሰረቱ እነሱ ናቸው፡፡ በአብረሃ ወአጽብሃ ዘመን መንግስት የነበረው ፓትርያርክ መርሐ ጽዮን ይባል ነበር፡፡
ታዲያ እኒህ ቀደምት የኢትዮጵያ ጥንታዊ ገዳማት ለሶስት ሺ አመታት ነገስታቱ ሲነግሱ ቅብዕ መንግስት የሚያገኙበት ታላቅ ሚስጥር የሚገለጥበት ቦታ ነው። እኒህ ገናና ቦታወች ወደ ፊት በታላቅ ክብር የሚገለጡበት የራሳቸው መንገድ ይኖራል ነገስታቱ መኳንቱ ሹማምንቱ በእኒህ የኢትዮጵያ የሚስጥር ቦታወች በመገኘት መንግስቱ እንዲጸና እግዘብሔርን የሚለምኑበት ታላቅ ገዳም ነው።
ቅርሳቅርስ በተድባበ ማርያም
የበግ ምስልና የተቁለመለመ የበግ ቀንድ ያለበት መስቀል በዚያ ይገኛል፡፡ የዚህ መስቀል ብርሀን የሚያስገርምና ዓይንን የሚያንፀባርቅ ሲሆን ከምን አይነት ማእድን እንደተሰራ አይታወቅም፡፡ ከጥንታዊያን ነገስታትም መካከል ዐፄ ካሌብ ወደ ደቡብ አረቢያ የናግራንን ክርስቲያኖች ለመርዳት ሲዘምቱ ፓትርያርክ ዘሙሴ እሱም የኦየሩሳሌምን ገዳም ያቀናና በመጨረሻም በአባ ጴንጠሌዎን ገዳም ገብቶ ያረፈ አባት ጋር ዘምተው ድል አድርገው ሲመለሱ ይዘው የሄዱትን ጋሻ በስዕለት ለተድባባ ማርያም አስገብተውት በቦታው ይገኛል፡፡ እንዲሁም የእብራይጥ ሲኖዶስና የአረማይክ ቅዳሴ እግዚእ በቦታው ላይ ይገኛል፡፡
#1ኛ ብራና መጻህፍት በዚህ ገዳም ከ1000 ያላነሱ የብራና ጥንታዊያን መጸህፍት ይገኛሉ እነዚህም መጻህፍት ክፊሎቹ በጥንታዊት የአክሱም ዘመን መንግስት የተጻፈ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግም በመካከለኛ ዘመን የተጻፉ ናቸው፡፡
#2ኛ በአረማክ ቋንቋ የተጻፉ የስሌዳ መጻህፍት በአረበኛና በግእዝ የተጻፉ መጻህፍት ወንጌል ዘወርቅ እየተባለ የሚጠራ ትልቅ የወርቅ ጉብ፦ጉብታ ያለበት የወንጌል መጽሀፍ ቅድስ &ሉቃስ እንዳሳላት የሚነገርላት የቅድስት ድንግል ማርያም ስዕለ አድህኖ ባለ 3 ተከፍች የገበታ ስእልና ጥንታዊና ስነ ጥበባዊ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ መስቀል በተድባበ ማርያም በርካታ ጥንታዊ የእጅና የመጾር መስቀል ይገኛሉ ከእነዚህም መካከል የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊ ጳጳስ የቀደሰበት የእጅ መስቀል የመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መስቀል የዕጨጊ ዮሐንስ በትረ ሆሳዕና እና የእጅ መስቀል የአቡነ አኖሪዎስ የእጅ መስቀል የአቡነ ቄርሎስ የእጅ መስቀልና ሌሎች ከወርቅ የተሰሩ ጥንታውያን መስቀሎች ናቸው፡፡ ስእርተ ሀና የድንግል ማርያም እናት የቅድስት ሀና ጸጉር በገዳሙ ይገኛል ይህ ጸጉር የተቀመጠበት የሽክላ ገንቦ እጅግ ጥንታዊና በስነ ጥበባዊ ይዘቱ የሚያስገርም ትእይነት ይፈጥራል፡፡ አጽመ ቅዱሳን ከአጽም ቅዱሳን መካከል ሄሮድስ የጨፈጨፋቸው ህጻናት ዓጽም በክፊል እንዲሁም የቅዱስ ጊዩርጊስ አወራ ጣት በአጠቃላይ የ28 ሰማእታት ዓጽም የሚገኝ ሲሆን
#እንዲሁም በልዩ ስፍራ የሚገኘው መካነ መቃብር የዐፄ ገላውዴዎስን ጨምሮ የስድስት ነገስታትና የአራት እጨጌዎች ተሰብስቦ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የጥንታዊያን ነገስታትና ጳጳሳት ከወርቅና ከብር የተሰሩ አልባሳትና የነገስታት ዘውድ እንዲሁም የቅዱስ የሬድ ድጓ እና ጊዩርጊስ ወልደ አሚድ፣ ገድለ አዳም ከታላቅነቱ የተነሳ ሁለት ሰው ከቀኝ ከግራሆኖ የሚዘው ባለ ገበታ የብራና መጽሀፍ እና ሌሎች በርካታ ጥንታዊን መጸፈህት በቅርስነት ተመዝግበው በተድባበ ማርያም የሚገኙ የመንፈሳዊ እሴት ማንጸባረቂያዎች ናቸው፡፡
ከ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እሰከ 11ኛው ድረስ የጨለማው ዘመን በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም የግእዝ ሥነ ጽሁፍ የተዳከመበት ዮዲት ከተከታዮቿ ጋር በመሆን ባደረሰችው ወረራ ሰነ ጽሁፍ የጠፉበት የትርጉም ስራዎች እንደቆሙ ተደረገበት ወቅት ነበር፡፡
#በ9-15ኛው ክፍለ ዘመን
በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን 40 ዓመታት መሉ ቤተ ክርስቲያንን ስታቃጥል መጸህፍትንና ሌሎችንም የቤተ ክርስትያን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ ተደምሰሱ፡፡ አያሌ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት (ካህናት) አብረው ተቃጠሉ፡፡ በዚህም ጊዜ በኢትዮጵያ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕጅጉ ተዳክሞ ነበር ነገር ግን በዚች ጥንታዊት ገዳም ምንም አይነት ወረራ አልደረሰባትም በ15ኛው ክፍለ ዘመንም ግራኛ የተነሳበትን በመሆኑ ቱርክ እየተላላከ ባስመጣው መሣሪያና በድብቅ ያስለጠነውን ወታደር አሳልፎ ኢትዮጵያን መውረር ሲጀምር 15 አመት ያህል ያለማቋረጥ በኢትዮጵያ ላይ የቱርክ ጥይት እንደ እሳት ሲነድ ከዮዲት ጉዲት ወራራ ተርፈው የቀሩና ከርእርሷም በኋላ የተተኩት የቤተክርስቲያን ቅርሶች በግራኝ ወራራ ጨርሰው ሲወድሙ የግራኝ ወራራ በቤተክርስቲያንና በምዕመናና ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትል አያሌ ገዳማትና አድባራት ሲቃጠሉና ሲመዘበሩ ይህቺ ታላቅ የታሪክና የቅርስ ባለቤት የሆነችው ርእስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ምንም አይነት ቃጠሎና የቅርስ ዝርፊያ አልደረሰባትም፡፡ ከዚህም አልፎ በአጼ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት ካቶሊካዊያን በየገዳማቱና በእየአድባራቱ እንዲሁም በእየቤቱና በእየለቅሶው ቤት በእየገበያው እየዘሩ የካቶሊክን ሀይማኖት ለማስፋፋት ሲጥሩ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ዓጽም ካረፈበት እየወጣ መቃጠል ሲጀምር ብዙ ካህናትና መነኮሳት ሊቃውንትና ምእመናን ልጅ አዋቂ ሳይባል የተዋህዶ ሀይማኖት ልጆች የሆኑ ሁሉ ባሉበት እየታደኑ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸምባቸው የርእስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ሊቃውንትና ካህናት መነኮሳት ግን እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በፆምና በፀሎት ፀንተው መከራውንና ችግሩን በመቋቋም ተዋህዶ ሀይማኖታቸውን አቅንተው እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ታሪካቸውንና ቅርሳቸውን በመጠበቅ ይገኛሉ፡፡







No comments:
Post a Comment