Saturday, 5 March 2022

ካራ ማራ


የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት 
ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ

ሚያዚያ ወር 1970፡፡ በአብዛኛው በሚሊሺያ ሀይል የተገነባው የኢትዮጵያ ሰራዊት እብሪተኛውን የሶማሊያ ወራሪ ያባረረበት የካራ ማራ የድል በዓል እንዲከበር ተወሰነ፡፡ መሆኑም በምስራቅ ኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች በአማርኛ እንዲህ እየተባለ ተዘፈነ፡፡
“አባርሮ ገዳይ በረሃ ያለው
ጠላቴን ዛሬ አወድመዋለሁ”

ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድል ነው፡፡ ክርስቲያንም ሆነ ሙስሊም፣ ኦሮሞም ሆነ አማራ ሀገርን ከወራሪ ለማዳን በተደረገው ጦርነት ደሙን አፍስሷል፤ አጥንቱን ከስክሷል፡፡ በመሆኑም በውጊያው ከፍተኛ ተሳትፎ የነበረው የምስራቁ የኦሮሞ ህዝብ እንዲህ ሲል ዘፍኗል፡፡

Jijjigaa gadi Ogaadeenis tiyya
Irrattin du’a biyya haadha tiyyaa
በቀላል አማርኛ ስንፈስረው እንደዚህ ሊሆን ይችላል፡  
“ከጅጅጋ በታች ኦጋዴንም የኔ ናት
እሞትላታለሁ ሀገሬ እናቴ ናት”

Thursday, 3 March 2022

ሳይበር

ሳይበር የሰው ልጅ የእርስ በርስ ግንኙነቱ ማደግ የፈጠረው ረቂቅ የቴክኖሎጂ ውጤት እና መሰረተ-ልማት፣ የመረጃ እንዲሁም የሰዎች መስተጋበር የሚገለጽበት ፈጠራ ነው፡፡
የሳይበር ምህዳር የምንለው የተለያዩ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ልማቶች ማለትም ኮምፒውተሮች ፣ራውተሮች፣የኮምፒውተር ኔትዎርኮች፣ወ.ዘ.ተ. ተሳስረው የፈጠሩት ምናባዊ ዓለም ሲሆን በዚህ ምህዳር ውስጥ ኢንፎርሜሽን ይቀመጣል፣ ይሰራጫል፣ እንዲሁም ይተነተናል፡፡

የራስህ ተጠቂ አትሁን!

አንድ ሰው አመለካከቱ የተዛባ ከሆነ የራሱ ጠላት ነው። የአካል ጉዳይ ሳይሆን፣ የአመለካከት ጉዳይ መሆኑን ልብ ይበሉ። ዋነኛው ጠላት ያለው ከውስጣችን መሆኑን መዘንጋት የለብንም!

የራስህ ተጠቂ አትሁን! Don’t become a victim of yourself. የውሸት ወሬ እየፈጠረ ሽባ የሚያደርግህ የውስጥ ጠላትህ ነው። 

Tuesday, 1 March 2022

ቅዱስ ጊዎርጊስ

 


አንስጣስዮስ ከሮም ወደ ፍልስጤም በፈቃደ እግዚአብሔር ሄደ።በዚያም ከክቡራን መኳንንት፣ ከታላላቆች መሳፍንት መካከል አንዱ ነበር። ከፍልስጤም ዕጻ ከምትሆን ድያስ ከተባለች አገር ቴዎብስታ (አቅሌስያ) የምትባል ደግ ሚስት አገባ። የቴዎብስታ የስሟ ትርጓሜ ቤተ ክርስቲያን ማለት ነው። አቅሌስያም እንደ ስሟ የተቀደሰች፣ የተመሰገነች፣ የተባረከች፣ የተመረጠች በብርሃኑ ዓለምን ሁሉ ያበራውን የሰማዕታትን ኮከብ ይሸከም ዘንድ እግዚአብሔር ማህጸኗን የባረከላት ሴት ነበረች።እነዚህ ሁለት ደጋግ የእግዚአብሔር ሰዎችም ዘሮንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ቴዎብስታ (አቅሌሲያ) በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ተጋብተው በህይወታቸው እግዚአብሔርን የሚያስደስት ተግባር ይፈጽሙ ነበር። ጥር 20 ቀን 277 ዓ.ም በሀገረ ፍልስጤም ልዩ ስሟ ልዳ በተባለ ስፍራ ደም ግባቱ ያማረ፣ መልከ መልካም ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ወለዱ። በተጨማሪም ማርታና እስያ የሚባሉ ሁለት ሴቶች ልጆችን አፈሩ።

Wednesday, 23 February 2022

"ይህችን ዓመት ተወኝ!"


ከዓመት እስከ ዓመት - ፍሬን ሳላፈራ - ደረቅ እንደሆንኩኝ

በራድ ወይም ትኩስ - ሁለቱንም ሳልሆን - እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ

አለሁኝ በቤትህ - ለሙን መሬትህን - እያጎሳቆልኩኝ

አውቃለሁ አምላኬ - ፍሬዬን ለመልቀም - እንዳመላለስኩህ

ዛሬም ሳላፈራ - እሾህን አብቅዬ - ደርቄ ጠበቅሁህ

ያልተደረገልኝ - ያላፈሰሰክብኝ - ያልሰጠኸኝ የለም

ነገር ግን ይህ ሁሉ - አላርምህ አለኝ - አልለየኝም ከዓለም

የማትሰለቸኝ ሆይ - ተነሥቼ እስክቆም - እባክህ ታገሠኝ

የእኔን ክፋት ተወው - መልአክህን ሰምተህ - ይህችን ዓመት ተወኝ!

Saturday, 19 February 2022

ሰማያዊው ወንዝ (አባይ)

በአንዱዓለም አስናቀ

ግዮን-

ሰማያዊው

መለኮታዊው....

•••

ፍልስምና የእምነት ጓዳችን

ታሪክና ማንነታችን

ወንዛችን እና ወዛችን....

•••

ሳይጎድል እየፈሰሰ

ሳይደክም እየደረሰ

ሳይነጥፍ እያረሰረሰ....

••

ከኤዶም ፈልቆ 

ኢትዮጵያን  ከቦ

ብርሃን አፍላግ - ሊያጠጣ

ለእናቱ ዛሬ ደረሰ።





የሰማዕታት ሐውልት(የካቲት 12)

የካቲት 12, 1929 ዓ.ም በእለተ ዓርብ – በኢጣሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወኪል አገረ ገዢ የነበረው ማርሻል ሩዶልፎ ግራዚያኒ ፣ የኔፕልስ ልዕልት ልጅ መውለዷን ምክንያት በማድረግ በቀድሞው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ ለድሆች ምጽዋት ለመስጠት ስለፈለገ የከተማው ድሆች እንዲሰበሰቡ ተደረገ ሶስት ሺህ የሚሆኑ ምንዱባኖች በቅጥሩ ውሥጥ ተኮልኩለው ነበር፡፡ ለእያንዳንዱ ደሀም ሁለት የማርትሬዛ ብር እንዲሰጥ ተወስኖ ነበር፡፡

Sunday, 13 February 2022

ፆመ ነነዌ

ነነዌ Nineveh

ነነዌ የአሦራውን ጥንታዊ ዋና  ከተማ ስትሆን በላዕላይ መስጴጦምያ በአሁኑ አጠራር በሰሜናዊ ኢራቅ የምትገኝ ከተማ ስትሆን ከተማዋን ሶርያ፣ ቱርክ እና ኢራን ያዋስኗታል፡፡

ነነዌ የአሦራውያን ከተማ

ነነዌ በጤግሮስ ወንዝ ዳር በ4000 ቅ.ል.ክ. ገደማ በኩሽ ልጅ ናምሩድ የተቆረቆረች ከተማ  ከተማ ናት (ዘፍ.10፡11-12)።  ነነዌ  የአሦራውያን ዋና ከተማ እና መናገሻ የሆነችው ግን በ1400 ቅ.ል.ክ. ነው  (2ነገ.19፡36)፡፡ አሦር የተባለው የሴም ሁለተኛ ልጅ (ዘፍ.10፥22)  አሦራውያን ለተባሉት ሕዝቦች የመጀመሪያ አባት ነበር። ሀገራቸው በላይኛው መስጴጦምያ ነው። ነነዌም ዋና ከተማቸው ነበረች። 

Saturday, 12 February 2022

የ"ቶ" ፊደል ምስጢር እና ታሪክ

የ "ቶ" ፊደል የተፈጠረዉ አለም ሲፈጠር ነዉ። የሰዉ ልጅ የተፈጠረዉ በ"ቶ" ቀመር መሆኑ አጀብ ያስብላል። በግዕዝ የፊደል ስርአት መሰረት (ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ) "ቶ" ሰባተኛዋ ፊደል ነች። ሰባት ቁጥር ብዙ ትርጉምና ምስጢር አለው፡፡ ሰባት ቁጥር በቤተክርስትያን ፍፁምነትን ይወክላል።

Friday, 4 February 2022

ካልተጻፈ ታሪክ የለም! ወደ ማይጠየፈን አይጠየፍ፤ የንጉስ ሚካኤል መንደር ደሴ ላኮመልዛ ወይራ አምባ

 


ሚካኤል “አባ ሻንቆ” photo credit ሽፍታ

በዛሬዋ ዕለት ጥር 27/1842 ዓ.ም ራስ ሚካኤል “አባ ሻንቆ” ከዛሬዋ ደሴ ላኮመልዛ  በፊት ደግሞ  ወይራ አምባ ከሰሜኗ  የፍቅር ከተማ ክፍለ ሀገር ተንታ ተወለዱ። 

ደሴ  እንኳን ለሀገሬ ሰው ይቅርና በ7ኛው ክፍለ ዘመን ከአርመን ተሰደው ለመጡ ክርስቲያኖች መጠጊያ፤ ሰው እምነቱ  እርስ በእርስ የማይባላባት፤ ሙስሊም ክርስቲያኑ የሚለው የወግ ማዕረግ በተግባር የሚታይባት የፍቅር ተምሳሌት ከተማ፤ እስላም ክርስቲያኑ፣ በረኸኛው ከደገኛው፣ ብሔረሰብ ሕዝቡ፣ ተፈጠሮና ሰው… ሁሉም በፍቅር የሚኖሩባት ምድር ደሴ። 

Monday, 31 January 2022

ባርነትን የመረጠ የሚመክተው ጋሻ የሚጠጋበት ዋሻ የለውም

አንዱዓለም አስናቀ (የ'የሽወርቅ ልጅ)

የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ የሚለው  የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር እንዲዘመር እንጅ እንዲከበር በመንበረ ብልጽግናም ዛሬም አልተፈቀደም።  ስለዲሞክራሲ ብዙ ሲነግረን የኖረው መንበረ-ኢህአዴግ  የሚናገርለት ዲሞክራሲ በተግባር ሲታይ  አፈና ድብደባ እስርና ግድያ ሆኖ ቆይቷል። የግፍ አጥቢያው  ወንበረ-ብልጽግና ተግባራዊ ዲሞክራሲን ከኢህአዴግ አስበልጦ በወንበዴዎቹ በትምክተኝነት የህዝብን ሉአላዊነት በመንጠቅ  ጋዜጠኞችን  እንዲሁም የእውነት ታጋይዎችን ማሰሩን  ግድ ሆኖበታል ውርስ ነውና።  

በወያኔ ጎዳና ብልጽግና ዛሬም ውሸት ይናገራል (2.2 ቢልየን ብር) ለአንድ ህንጻ ማደሻ ይውላል። በወያኔ ዝማሬ ሁሉም ነገር ኢትዮጵያ እንዳደገች ህዝቡ ተለውጦ የድህነትን ሸማ አስፈንጥሮ እንደጣለ ህዝቡ ያሻውን መናገር እና ማድረግ እንደቻለ ዘወትር እንሰማለን፤ ግን በተግባር ግን በአስለቃሽ ጭስ ተቆልተን በጥይት እናራለን።  

በመንበረ ብልጽግና በጧትና በማታ  በዘወትር መልእክቱ  ሀገር በለፀገ ህዝብ ተለወጠ የሚል ድስኩሩን በሆድ አደር ሚዲያዎች እንሰማለን፤ እኛ ግን የቀን ስራ ሰርተን ዳቦ መግዛት ቸግሮናል፤ 30 ቀን ዘምተን የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶናል፤ በቀላጤው ወንድማችን ሸኔ  (በኦነግ) መከራችን በየቀኑ ይጨምራል።  

ዛሬም በህወሃት ችግራችን እንዲያገረሽ  እንጂ እንዲቀንስ አይፈለግም።  በመንበረ ብልጽግና ለጥቂቶቹ ሀገራችን ገነት ሆና ሲደላቸው ሲመቻቸው  ብዙሀኑ ግን በችግርና በረሀብ መማቀቁን ህይዎቱን ቀጥሎበታል። እናም ኤሎሄያችን ጩህታችን ዛሬም ያስተጋባል። ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ለፍትህ፣ ለእኩልነት ለነፃነት  እንደ ህዝብ ካልታገልክ ባርነትን ከመረጥክ የምትመክተው ጋሻ የሚ የምትጠጋበት  ዋሻ የለህም።

Friday, 28 January 2022

ጥር 21 የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት

ጥር 21 በዓለ አስተርእዮ (የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት)

እንኳን ለዚህች ታላቅ በዓሏ አደረሰን፡፡ 

ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡
ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡ በማለት አደነቀ፡፡ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡

Wednesday, 19 January 2022

ቃና ዘገሊላ



 ‹‹ቃና ዘገሊላ›› ምንድነው?

ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት(ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡ የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡ ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡

Tuesday, 18 January 2022

ገሀድ፣ ከተራ እና የጥምቀት በኢትዮጵያ


═════ ❁ ═════

ገሀድ :

➢. ገሃድ የቃሉ ትርጉም መገለጥ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና እንዲሁም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡(ማቴ 3፡13-17)

ጥምቀት

ጥምቀት የሚለው ቃል “አጥመቀ” (አጠመቀ) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በተከማቸ ውሃ ውስጥ መነከር፡ መዘፈቅ፡ ገብቶ መውጣት ማለት ነው። ምስጢረ ጥምቀት በምስጢራዊ (በሃይማኖታዊ) ፍቺው በተጸለየበት ውሃ (ማየ ኅይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብሎ የመውጣት ሂደት ነው (ማቴ 28፡19)። ጥምቀት “የክርስትና መግቢያ በር” ናት፡፡ ምክንያቱም ከሌሎች ምስጢራት ስለሚቀድምና ለእነርሱም መፈጸም ቅድመ ሁኔታ ስለሆነ ነው፡፡ ጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት (ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና) ምሥጢር ነው። ሰው ከሌሎች ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ለመካፈል አስቀድሞ መጠመቅና ከማኅበረ ክርስቲያን መደመር አለበት፡፡ ስለዚህም ምስጢረ ጥምቀት ከአምስቱ አዕማደ ምስጢራት እንዲሁም ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ የእምነታችን መሠረትም፣ የጸጋ ልጅነት የሚገኝበትም ምስጢር ነውና ከሁለቱም ይመደባል፡፡

Thursday, 6 January 2022

ልደተ ክርስቶስ


 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት አሉት

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት እንዳሉት ታምናለች ታሳምናለች፤ እነዚሁ ቀዳማዊ ልደትና ደኃራዊ ልደት ሲባሉ፤ ይኸውም ወልድ (ቃል) ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ያለ አ