ሳይበር የሰው ልጅ የእርስ በርስ ግንኙነቱ ማደግ የፈጠረው ረቂቅ የቴክኖሎጂ ውጤት እና መሰረተ-ልማት፣ የመረጃ እንዲሁም የሰዎች መስተጋበር የሚገለጽበት ፈጠራ ነው፡፡
የሳይበር ምህዳሩን አንዳንዶች በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሰው ልጅ የተቆጣጠረው አምስተኛው ግዛት በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህም ከየብስ ፣ ውሃ ፣ የአየር እንዲሁም የውጫዊው የህዋ ግዛት መካከከል በመመደብ፡፡
የሳይበር ምህዳር፡ የብዙዎቻችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አካል ከሆነም ውሎ አድሯል፡፡ ይህ ሲባል ለስራ ፣ለትምህርት ፣ ለመዝናኛ ከመጥቀምም አልፎ ለተለያዩ የእርስ በርስ ግንኙነቶች ማሳለጫ አድርገን የምንጠቀምበት ዋነኛ መሳሪያ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ አልፎ የምህዳሩ እውን መሆን የኢንፎርሜሽን ዋጋ ከምንጊዜውም በላይ እንዲጨምር ምክንያት እየሆነ ይገኛል፡፡
የሳይበር ምህዳር አካላት
የሳይበር ምህዳር የምንለው ኮምፒውተሮች ብቻ የሚፈጥሩት ሳይሆን የተለያዩ አካላት ተሳስረው እውን ያደረጉት ምህዳር ነው፡፡ እነዚህ የሳይበር ምህዳር አካላት ከላይኛው የምህዳሩ ክፍል እስከ ታችኛው ድረስ በ4 ዋና ዋና ክፍለች ከፋፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
የውስጠኛው የምህዳሩ ክፍል፡ የሳይበር ምህዳር እውን እንዲሆን መሰረት የጣለው አካላዊ ወይም ፊዚካል ደረጃ የምንለው ነው፡፡ ይህም የተለያዩ ማሽኖች፣ኮምፒውተሮች፣ኬብሎችና የመሳሰሉ አካላት ጥምረት ነው፡፡
ሁለተኛው የሳይበር ምህዳር ውስጥ የሚቀመጠው፣ የሚተነተነው እና የሚሰራጨው ኢንፎርሜሽን ነው፡፡
ሶስተኛው የሳይበር ምህዳር ክፍል ለኢንፎርሜሽን መፈጠር፣ መተንተንና መሰራጨት መሰረት የሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የኢንተርኔት አገልግሎት ፕላትፎርሞች ናቸው፡፡
እንዲሁም የመጨረሻው እና ውጫዊ ክፍሉ፡ የሳይበር ምህዳሩን የሚጠቀመው፣ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂውን የሚያንቀሳቅሰው የሰው ልጅ የሳይበር ምህዳር ውጨኛው ክፍል ነው፡፡
⚜የሳይበር ምህዳሩ ልዩ ባህሪያት
🔻ያልተማከለ ወይም ልዩ የተማከለ አስተዳደር የሌለው ሲሆን ይህም ለቁጥጥር አዳጋች እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
🔻ለግለሰቦች እና ለቡድኖች ከፍተኛ ሃይል የሚሰጥ ሲሆን የግለሰቦች እና ቡድኖች አስተሳሰብ፣እምነት እና እሴቶችን ማንጸባረቅ የሚያስችላቸው ነው፡፡
🔻የጎንዮሽ እና ትስስራዊ ሃይል የሚያበረታታ ነው፡፡
🔻ዓለም አቀፋዊ እና ድንበር የለሽ ነው፡፡
🔻እውቀት መረጃና ምናባዊነት ላይ ያተኩራል
🔻ለደካሞች ልዩ ተጠቃሚነትን የሚሰጥ ነው
🔻ሁሉም ጋር የደራሽነት አቅም ያለው፡፡
🔻በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ የሆነ ፍልስፍናዊ ባህሪ ያለው ነው፡፡
በእነዚህ ልዩ ባህሪያት ምክንያት ምህዳሩ ለተጠቃሚዎች መልካም እድሎችን ይዞ መጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ዓለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለየ መልክ እየያዘች ከመምጣቷ ባሻገር የእውቀት እና የኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ መልካም እድሎች ካመጧቸው ቱሩፋቶች ጎን ለጎን ምህዳሩ የተለያዩ የደህንነት ስጋቶችን ይዞ መጥቷል፡፡ እነዚህን ስጋቶች ለመቋቋምና ምህዳሩ ያለውን መልካም ጎኖች አሟጦ ለመጠቀም ሃገራት የደህንነት ስትራቴጂዎች ከቴክኖሎጂ፣ ከሰው ልጆች እንዲሁም ከኢንፈርሜሽን ደህንነት አስተዳደር እና አሰራር ስርዓቶች አንጻር ቀርጸው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከስትራቴጂዎች መካከልም የኢንፎርሜሽን ደህንነት ገዥ ሰነዶች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡
የሳይበር ወንጀል
መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም ኢንተርኔት ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊዘልቁት ይችላሉ። በግለሰብ ደረጃ ሲከወን ጉዳቱ አስደንጋጭ ላይሆን ይችላል። ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳት ሲያስከትል ነው። አንድ አገር የፋይናንስ መረጃዎቹ ከተጠለፉበት በእንብርኩኩ ሊሄድ ይችላል።
መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም ኢንተርኔት ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊዘልቁት ይችላሉ። በግለሰብ ደረጃ ሲከወን ጉዳቱ አስደንጋጭ ላይሆን ይችላል። ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳት ሲያስከትል ነው። አንድ አገር የፋይናንስ መረጃዎቹ ከተጠለፉበት በእንብርኩኩ ሊሄድ ይችላል።
እራስን መጠበቅ የምችለው እንዴት ነው?
ከሳይበር ወንጀል እራስዎን ለመጠበቅ ሲባል ድር ላይ እያሉ ኮምፒተርዎትን መጠበቅ እና የጋራ ስሜትን መጠቀም አስፈላጊ ነው. የሚከተሉት ሀብቶች ሊረዱዎት ይችላሉ:
- የተለመደው ደህንነት የድር ሰራተኞች: በመስመር ላይ በተያዙ ሰዎች ውስጥ የሚገኙት አብዛኛዎቹ ወጥቶች ከተለመደው የዌብ ደህንነት መራቅ ይችላሉ.
- እራስዎን ከስፓይዌር መጠበቅ : በመስመር ላይ ለማግኘት ክትትል ከሚደረግባቸው በጣም ቀላል መንገዶች አንዱ ኮምፒውተርዎ ምን እያደረገ እንደሆነ ለሚመለከታቸው ተንኮል አዘል ሶፍትዌር (ተንኮል አዘል ዌር) ነው.
- የአንተን ፍለጋ ባህሪዎች አንተ የምትፈልገውን እንዲያይ አይፈልግም? የፍለጋ ፕሮግራሞች (እና ኮምፒተርዎን የሚጠቀሙ ሌሎች ሰዎች) የፍለጋ ውጤቶችን መዝገቦችን መጠበቅ ይችላሉ - የፍለጋ ታሪክዎን የግል ማድረግ ይችላሉ.
- የማይታወቅ ዝርግ -ስለ ማንነት ስለማይታወቁ የማንሸራተት, ማንነት በማይታወቅ የጎልፍ ስፖርት, ለምን ስምዎን በውርጃ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ሊያድርብዎት እንደሚችል, በድረ ገጽ surfing ልማዶችዎ, ስማቸውን የማይገልጹ ፕሮክሲዎች እና አገልግሎቶች እና ሌሎችም ስለእርስዎ ምን ያህል ሊረዱት ይችላሉ.
- የፌስቡክ የግላዊነት ቅንጅቶችዎን ያሻሽሉ : በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ የሆነው ማህበራዊ አውታረ መረብ ጣቢያ, በፌስቡክ የግላዊነት መመሪያ ላይ ብዙ ለውጦች አድርገዋል, እና አብዛኛዎቹ ለአማካይ ተጠቃሚ አይደሉም. ለመረዳት አስቸጋሪ እና እንዲያውም ለመለወጥ አስቸጋሪ እና አደጋ ሊያስከትል ይችላል, እና መስመር ላይ ደህንነትዎን ሊያሰቃዩ ይችላሉ. የፌስቡክ ግላዊነት ቅንጅቶችዎን በፍጥነት, በቀላሉ እና በደህንነት እንዴት እንደሚለውጡ ይወቁ.
No comments:
Post a Comment