ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ኃይለ ቃልን ከትርጓሜ፣ ትርጓሜንከምሥጢር እንዲሁም ደግሞ ምሥጢርን ከዜማ ጋርአስተባብረውና አስማምተው የሚደርሱ ሊቃውንት ባለቤትናት፡፡ በ5ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድአምስቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ14ኛው መ.ክ.ዘመንየተነሣው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡ በዚሁ ዘመንአባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌድንግል “ማኅሌተ ጽጌ” የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡ ማኅሌተጽጌ ግጥማዊ አካሔድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው፡፡ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታበቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግልማርያም የስደት ዘመን ነው፡፡ በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድሌሊት በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ መሰደድናመንከራተት እያሰቡ የሚደረስ ምሥጋናና ጸሎት ነው፡፡በሀገራችን የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት /ዘመነ ጽጌ/ ናቸው፡፡ ይህም ወቅት ተራሮች በአበባየሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡በዚህም ዘመን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ስለልብስስ ስለምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴትእንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡ አይደክሙም፣አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡ እግዚአብሔርን ዛሬያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህየሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጐደላችሁ እናንተንማይልቁን እንዴት እንግዲህ ምን እንበላለን ምንስ እንጠጣለን?ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ ...» /



