የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?
ካላወቃችሁ አትጨነቁ፡፡ ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው:: ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::
ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል .... ሼር በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎችም ይትረፉ፡፡
🏷 በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function Key እንላቸዋለን፡፡
በዋናነትም ከሌሎች #ቁልፎች ጋር በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡
◽️F1
ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን #የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የMicrosoft Online Help ይከፍታል፡፡
◽️F2
#የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt + Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡
◽️F3
ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift + F3 መጫን #የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡
◽️F4
አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 #መጫን ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ
#የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4 ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt + F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማለት ነው፡፡
◽️F5
አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5 መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የFind መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት
ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡
◽️F6
በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን #ወደቀጣዩ የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡
◽️F7
ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ
#Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡
◽️F8
ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ #Startup menu ለመግባት የጠቅማል፡፡
◽️F9
በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግንበ ማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን
#Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { } ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ ለማጥፋት
◽️F10
አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን #ራይት ክሊክ እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
◽️F11
በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫንየ ምንመለከተው ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡
◽️F12
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ #የ Save as ማስኮትንይ ከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡

No comments:
Post a Comment