Wednesday, 3 September 2025

Gmail 2-step verification


Gmail 5 አይነት አማራጭ የ2-step verification መንገዶች አሉ።

በነገራችን ላይ የGmail ፓስዎርዳችሁ ባታስታውሱት ራሱ login ለማድረግ 2-step verification ብቻ መጠቀም ትችላላችሁ። 




እነዚህ የverification መንገዶች


1) Passkey and security keys

በስልካችሁ ወይም በኮምፒውተራችሁ ላይ passkey create ካደረጋችሁ ሌላ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ በቀላሉ login ማድረግ ትችላላችሁ። 

የይለፍ ቃላችሁን ብትረሱት ራሱ የእጅና የፊት አሻራችሁን በመጠቀም ወይም በብሉቱዝ በማገናኘት በቀላሉ መግባት ያስችላችኋል።

2) Google prompt

የGoogle አካውንታችሁን አንድ ወይም ከዛ በላይ በሆኑ ስልኮች ላይ login ስታደርጉ Gogle prompt እዛ ስልክ ላይ ይመዘገባል። 

በሌላ ስልክ ወይም የኮምፒውተር browser login ለማድረግ ስትሞክሩ መጀመርያ login አድርጋችሁበት ወደነበረው ስልክ የpopup notification ይልካል። በቀላሉ login ማድረግ ትችላላችሁ። ስለዚህ ከ1 በላይ በሆኑ ዲቫይሶች ላይ login ማድረግ የተሻለ advantage አለው።

3) Authenticator App

Gmail አካውንታችንን ከGoogle authenticator አፕሊኬሽን ጋር connect በማድረግ ፓስዎርዳችን ቢጠፋ በቀላሉ login ማድረግ ትችላላችሁ።

ስለAuthenticator አጠቃቀም ከዚህ በፊት የፃፍኩትን በዚህ ሊንክ ገባታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

https://t.me/bighabesha_softwares/3254


4) phone number

ስልክ ቁጥራችሁን ከ1 Gmail account ጋር connect በማድረግ የ2-step verification code እንዲላክላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።


5 Backup codes

ይህንን አማራጭ ስትጠቀሙ Google ባለ 8 digit 10 የተለያዩ backup ኮዶችን generate ያደርግላችኋል። እነዚህን ኮዶች በhardcopy በወረቀት ፅፎ ወይም print አድርጎ ማስቀመጥ። ፓስወርዳችን በሚጠፋበት ጊዜ ወይም በአዲስ ስልክ login ስናደርግ እነዚህን ኮዶች በማስገባት በቀላሉ login ማድረግ እንችላለን።

ስልካችሁ ላይ እነዚህን የverification መንገዶች ለማግኘት 

settings - Google - manage Your google account - security and sign-in - 2 step-verification ላይ ትገባላችሁ። 

ከላይ ከተዘረዘሩት backup ኮዶች ውስጥ ግዴታ አንድ ሰው ቢያንስ ሶስቱን መጠቀም ይኖርበታል።


ብዙ ሰው ስልክ ቁጥር ብቻ connect ስላደረገ login ማድረግ የሚችል ይመስለዋል። ግን በጣም አስቸጋሪ  ነው። 

ሌላኛው google አካውንታችሁን በተቻለ መጠን ከ1 በላይ በሆኑ ዲቫይሶች ላይ login አድርጉ።


No comments: