Saturday, 19 February 2022

ሰማያዊው ወንዝ (አባይ)

በአንዱዓለም አስናቀ

ግዮን-

ሰማያዊው

መለኮታዊው....

•••

ፍልስምና የእምነት ጓዳችን

ታሪክና ማንነታችን

ወንዛችን እና ወዛችን....

•••

ሳይጎድል እየፈሰሰ

ሳይደክም እየደረሰ

ሳይነጥፍ እያረሰረሰ....

••

ከኤዶም ፈልቆ 

ኢትዮጵያን  ከቦ

ብርሃን አፍላግ - ሊያጠጣ

ለእናቱ ዛሬ ደረሰ።





የሰማዕታት ሐውልት(የካቲት 12)

የካቲት 12, 1929 ዓ.ም በእለተ ዓርብ – በኢጣሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወኪል አገረ ገዢ የነበረው ማርሻል ሩዶልፎ ግራዚያኒ ፣ የኔፕልስ ልዕልት ልጅ መውለዷን ምክንያት በማድረግ በቀድሞው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ ለድሆች ምጽዋት ለመስጠት ስለፈለገ የከተማው ድሆች እንዲሰበሰቡ ተደረገ ሶስት ሺህ የሚሆኑ ምንዱባኖች በቅጥሩ ውሥጥ ተኮልኩለው ነበር፡፡ ለእያንዳንዱ ደሀም ሁለት የማርትሬዛ ብር እንዲሰጥ ተወስኖ ነበር፡፡

Sunday, 13 February 2022

ፆመ ነነዌ

ነነዌ Nineveh

ነነዌ የአሦራውን ጥንታዊ ዋና  ከተማ ስትሆን በላዕላይ መስጴጦምያ በአሁኑ አጠራር በሰሜናዊ ኢራቅ የምትገኝ ከተማ ስትሆን ከተማዋን ሶርያ፣ ቱርክ እና ኢራን ያዋስኗታል፡፡

ነነዌ የአሦራውያን ከተማ

ነነዌ በጤግሮስ ወንዝ ዳር በ4000 ቅ.ል.ክ. ገደማ በኩሽ ልጅ ናምሩድ የተቆረቆረች ከተማ  ከተማ ናት (ዘፍ.10፡11-12)።  ነነዌ  የአሦራውያን ዋና ከተማ እና መናገሻ የሆነችው ግን በ1400 ቅ.ል.ክ. ነው  (2ነገ.19፡36)፡፡ አሦር የተባለው የሴም ሁለተኛ ልጅ (ዘፍ.10፥22)  አሦራውያን ለተባሉት ሕዝቦች የመጀመሪያ አባት ነበር። ሀገራቸው በላይኛው መስጴጦምያ ነው። ነነዌም ዋና ከተማቸው ነበረች። 

Saturday, 12 February 2022

የ"ቶ" ፊደል ምስጢር እና ታሪክ

የ "ቶ" ፊደል የተፈጠረዉ አለም ሲፈጠር ነዉ። የሰዉ ልጅ የተፈጠረዉ በ"ቶ" ቀመር መሆኑ አጀብ ያስብላል። በግዕዝ የፊደል ስርአት መሰረት (ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ) "ቶ" ሰባተኛዋ ፊደል ነች። ሰባት ቁጥር ብዙ ትርጉምና ምስጢር አለው፡፡ ሰባት ቁጥር በቤተክርስትያን ፍፁምነትን ይወክላል።

Friday, 4 February 2022

ካልተጻፈ ታሪክ የለም! ወደ ማይጠየፈን አይጠየፍ፤ የንጉስ ሚካኤል መንደር ደሴ ላኮመልዛ ወይራ አምባ

 


ሚካኤል “አባ ሻንቆ” photo credit ሽፍታ

በዛሬዋ ዕለት ጥር 27/1842 ዓ.ም ራስ ሚካኤል “አባ ሻንቆ” ከዛሬዋ ደሴ ላኮመልዛ  በፊት ደግሞ  ወይራ አምባ ከሰሜኗ  የፍቅር ከተማ ክፍለ ሀገር ተንታ ተወለዱ። 

ደሴ  እንኳን ለሀገሬ ሰው ይቅርና በ7ኛው ክፍለ ዘመን ከአርመን ተሰደው ለመጡ ክርስቲያኖች መጠጊያ፤ ሰው እምነቱ  እርስ በእርስ የማይባላባት፤ ሙስሊም ክርስቲያኑ የሚለው የወግ ማዕረግ በተግባር የሚታይባት የፍቅር ተምሳሌት ከተማ፤ እስላም ክርስቲያኑ፣ በረኸኛው ከደገኛው፣ ብሔረሰብ ሕዝቡ፣ ተፈጠሮና ሰው… ሁሉም በፍቅር የሚኖሩባት ምድር ደሴ። 

Monday, 31 January 2022

ባርነትን የመረጠ የሚመክተው ጋሻ የሚጠጋበት ዋሻ የለውም

አንዱዓለም አስናቀ (የ'የሽወርቅ ልጅ)

የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ የሚለው  የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር እንዲዘመር እንጅ እንዲከበር በመንበረ ብልጽግናም ዛሬም አልተፈቀደም።  ስለዲሞክራሲ ብዙ ሲነግረን የኖረው መንበረ-ኢህአዴግ  የሚናገርለት ዲሞክራሲ በተግባር ሲታይ  አፈና ድብደባ እስርና ግድያ ሆኖ ቆይቷል። የግፍ አጥቢያው  ወንበረ-ብልጽግና ተግባራዊ ዲሞክራሲን ከኢህአዴግ አስበልጦ በወንበዴዎቹ በትምክተኝነት የህዝብን ሉአላዊነት በመንጠቅ  ጋዜጠኞችን  እንዲሁም የእውነት ታጋይዎችን ማሰሩን  ግድ ሆኖበታል ውርስ ነውና።  

በወያኔ ጎዳና ብልጽግና ዛሬም ውሸት ይናገራል (2.2 ቢልየን ብር) ለአንድ ህንጻ ማደሻ ይውላል። በወያኔ ዝማሬ ሁሉም ነገር ኢትዮጵያ እንዳደገች ህዝቡ ተለውጦ የድህነትን ሸማ አስፈንጥሮ እንደጣለ ህዝቡ ያሻውን መናገር እና ማድረግ እንደቻለ ዘወትር እንሰማለን፤ ግን በተግባር ግን በአስለቃሽ ጭስ ተቆልተን በጥይት እናራለን።  

በመንበረ ብልጽግና በጧትና በማታ  በዘወትር መልእክቱ  ሀገር በለፀገ ህዝብ ተለወጠ የሚል ድስኩሩን በሆድ አደር ሚዲያዎች እንሰማለን፤ እኛ ግን የቀን ስራ ሰርተን ዳቦ መግዛት ቸግሮናል፤ 30 ቀን ዘምተን የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶናል፤ በቀላጤው ወንድማችን ሸኔ  (በኦነግ) መከራችን በየቀኑ ይጨምራል።  

ዛሬም በህወሃት ችግራችን እንዲያገረሽ  እንጂ እንዲቀንስ አይፈለግም።  በመንበረ ብልጽግና ለጥቂቶቹ ሀገራችን ገነት ሆና ሲደላቸው ሲመቻቸው  ብዙሀኑ ግን በችግርና በረሀብ መማቀቁን ህይዎቱን ቀጥሎበታል። እናም ኤሎሄያችን ጩህታችን ዛሬም ያስተጋባል። ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ለፍትህ፣ ለእኩልነት ለነፃነት  እንደ ህዝብ ካልታገልክ ባርነትን ከመረጥክ የምትመክተው ጋሻ የሚ የምትጠጋበት  ዋሻ የለህም።