1- Scitable
https://www.nature.com/scitable
ዝንባሌዎ ስለ ጅኔቲክስ እና ስለሮቦት ሳይንስ ማወቅ ከሆነ እንግዲያውስ ሳይቴብል ለርሶ የተከፈተ ድህረገፅ ነው፡፡ ይህ ድህረገፅ በማበብ ብቻ በግልዎ መማር የሚችሉበት ሲሆን ልክ እንደ ት/ቤት በጋራም ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በኦንላይን ክፍል ውስጥ መማር ይችላሉ፡፡ ይህ ድህረገፅ በዓለም ላይ የሳይንስ ነክ ፅሁፎችን በማሳተም በሚታወቀው በ Nature Publishing Group ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በሌሎች ትልልቅ የሳንስ ኩባኒያዎች ስለሚደገፍ ት/ቱን በነፃ ነው የሚያስተምረው፡፡
በዚህ የኦንላይን ት/ቤት ውስጥ በ 4 ብቁ ፕሮፌሰሮች የተዋቀረ ሲሆን ተማሪዎች ለሚጠይቁት ማንኛውም ጥያቄ ከ 48 ሰዓት ባነሰ የጊዜ ገደብ ውስጥ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
2- iTunes U
https://www.open.edu/itunes/
ይህ ድህረገፅ ከ 600 በላይ በሆኑ ዩኒቨርስቲዎች የሚደገፍ ሲሆን ዓለም ላይ አሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎችን ማለትም የስታንፎርድ፣ የያሌ እና የኤም አይቲን ዩኒቨርሲቲዎችን የማስተማሪያ መፅኃፎችና ሌክቸር ኖቶች ሰብስቦ ይዟል፡፡ ይህ ድህረገፅ በተለይ ለመምህራን ትልቅ እፎይታን ያመጠጣ ሲሆን የማስተማሪያ መፅሀፎች፣ ቪዲዮዎችን እና ፈተናዎችን አካቶ ይዟል፡፡
ድህረገፁ ሰፋ ያለ ይዘት ያለው ሲሆን በውስጡ የግብርና፣ አስትሮኖሚ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ጂኦሎጂ ፣ ኬሚስትሪ እና የመሳሰሉ ሳይንሶችን በጥልቀት ይተነትናል፡፡