Sunday, 7 February 2021

ክብረ አምሓራ የማንነታችን ዐምድ


 

ጀግና

 አትንኩኝ የሚለው የሰራ አካላቱ

ክንዱ እሳት ነበልባል ቁርጥ ያለ አሞቱ

አየናና ሜታ ወግሎ ነው እድገቱ

ደግነት ጀግንነት ደሞ ምን ቸግሮት

አምሓራ ሳይንቴው ስበር አስተምሮት

ካልነኩት አይነካም ጅንን ያለ ነው

ከነኩት አይለቅም ልክ ነብር ነው።



ፎጣ ለባሾቹ



ያገር ባለ አደራ ፎጣ ለባሾቹ

ከነኳቸው ነብር እንደ አንበሳ ቁጡ

ለአገራቸው ታማኝ ኩሩና ቅንጡ

የነጻነት አባት ነፍጠኛ ነው ፈርጡ !!


 በነገራችን ላይ በእያንዳንዱ  ፎጣ ስር እሳት የሚተፋ ነፍጥ እና ንፍጣሙን የሚያናፍጥ ወኔ አለ !!

ትዝታ ወ-ልጅነት

ኤቢ የማርያም ልጅ







ውሀ ቅጂ ብላ ብሰደኝ እናቴ

ወለሹን ቀዳሁት አወይ ልጅነቴ

አወይ ልጅነቴ ነፍስ አለማወቄ

ሲመጣ መሽኮርመም ሲሄድ መናፈቄ።


እያልን እያንጎራጎርን ነበር ድሮ ከወንዝ ውሀ የምንቀዳው

ወሎ ቤተ አምሐራ

ባህሌን እወደዋለሁ እኮራበታለሁ

ኑ አምሓራ ሳይንት እንሂድ

      

                       ****

(የተረሱ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ መስህብ ፍለጋ)

Photo credit: Amhara sayint press


ምስጢር፣ እውቀት፣ እውነት፣ ውበት፣ እምነት፣ ታሪክ፣ ጀግንነት፣ ተፈጥሮ ሁሉም በአንድ ላይ ተሰድረውና ተደምረው የሚገኙባትን ቦታ ፍለጋ እንሄዳለን ፡፡ አምሓራ ሳይንት

Saturday, 6 February 2021

ያላለቀው ልማታችን

 


ከአምሐራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ ወደ ርዕስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም እየተሰራ ያለው መንገድ ስራ 90 በመቶ የሚሆነው የአፈር ጠረጋና ምንጣሮ ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ ስራ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዑመር እንደገለጹት ከአጅባር ተድባበ ማርያም 30ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የአጅባር ተድባበ ማርያም መንገድ ስራ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በመሰራት ላይ እንደሆነ ገልጸው አስካሁን በተሰራው ስራ 23 ነጥብ 17 ኪ.ሜትር የሚሆነው መንገድ የአፈር ጠረጋና የምንጣሮ ሥራ ተሰርቶለታል ፡፡

ኢኮኖሚያችን እድሜው የእለት ነው!

 



እኛ ሀገር የለት የለቱን ሰርቶ የሚኖረው በርካታ ህዝብ ነው! ምክንያቱም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ መደበኛ ባልሆነው (Informal economic sector) ላይ ነው ኢኮኖሚካሊ ህይወቱ የተመሰረተው! ስለዚህ የትኛውም አይነት ብጥብጥ ከአንድ ቀን በላይ ከቆየ በልቶ የማደርን ህልውና ነው የሚያሳጣው።