Labels
- #አዘጋጅ (1)
- ፩. ታሪክና ህብረተሰብ (12)
- ፪. የህይወት ክህሎት (7)
- ፫. ነጻ ሃሳብ (3)
- ፬. ቤተ-አምልኮ (23)
- ፭. ኪነ-ጥበብ (9)
- ፮. ውብ ሀገር (9)
- ፯. አገራዊ ጉዳዮች (2)
- ፰. ሳይንስና ቴክኖሎጅ (ሳይቴክ) (14)
- ፱. ንግድና ኢኮኖሚ (12)
- ለቤተ-መፅሃፍትዎ (5)
- ስራ-Vacancy (1)
- የጉዞ ማስታወሻ (1)
Thursday, 6 November 2025
Tuesday, 4 November 2025
ብሔረ ብፁዓን
ባሕረ ጥበባት የሆነች ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አስተምህሮዋ ሙሉ በሙሉ በመለኮታዊ መገለጥ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በሥጋዊና በደማዊ የግል አስተሳሰብና ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ አንድም አስምህሮ የላትም፡፡ ከልዑል እግዚአብሔር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው ልጆቿም ቅድስናን ገንዘብ ያደረጉ ናቸው፡፡ ቅድስናንም ገንዘብ ማድረጋቸው ሰማያዊው ምሥጢር ፍንትው ብሎ እንዲታያቸው ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡
ፈጣሬ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር አንድ ዓለም ብቻ ሳይሆን 20 የተለያዩ ዓለማትን እንደፈጠረ የምታውቅ ብቸኛዋ የእምነት ተቋም ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ብቻ ናት፡፡ ስነ ፍጥረትን እጅግ በሚገርም ሁኔታ ተንትኖ የሚያቀርበው መጽሐፈ አክሲማሮስም ሆነ ሌሎቹ ቤተክርስቲያን ድርሳናት እንደሚያስረዱት ከሆነ እግዚአብሔር 20 የተለያዩ ዓለማትን ፈጥሯል። እነዚህም፡- 5ቱ ዓለማተ መሬት፣ 4ቱ ዓለማተ ማይ፣ 2ቱ ዓለማተ ነፋስ እና 9ኙ ዓለማተ እሳት ናቸው፡፡
Saturday, 1 November 2025
ከፍታህን ምረጥ!
1. ንስሮች በከፍታ ለብቻቸው ይበራሉ፦ ንስር ፈፅሞ ከጥንብ አንሳ፣ ቁራና መሰል ትናንሽ አእዋፍት ጋር አብሮ አይበርም።📌 ንስርን በተፈጥሮ ከሚገዳደሩት የወፍ ዝርያዎች መካከል አንዱና ዋነኛ የሆነው ቁራ ነው። ቁራ በንስሩ ጀርባ ላይ በመፈናጠጥ የንስሩን አንገቱን እና ጀርባውን መንከስ ይጀምራል። በዚህን ጊዜ ንስሩ ለመከላከል ወይም ከላዩ ላይ ለማስወገድ የሚያደርገው አንዳችም ዓይነት ምላሽ አይኖርም። ጸብ ውስጥም አይገባም፣ ግጭትም አይፈጥርም።
ከቁራው ጋር እየታገለ ምንም ዓይነት ጊዜና ጉልበትንም አያባክንም። ነገር ግን አንድ ነገር ያደርጋል። ይህም ንስሩ ረዣዥም ክንፎቹን በመዘርጋት ከፍ ወዳለው ወደ ሰማየ ሰማያት መወንጨፍ ይጀምራል።
ከፍታው በጨመረ ቁጥር ቁራው አየር ንብረቱን መቋቋም ስለማይችል መተንፈስ አስቸጋሪ ይሆንበታል። በስተመጨረሻም በኦክስጂን እጥረት ምክንያት ቁራው ከጀርባው ላይ ይወድቃል። ከቁራዎች ጋር ጊዜያችሁን አታባክኑ።
ቀጥታ ወደ ከፍታ ውሰዷቸው። የዚያን ጊዜ መተንፈስ ስለማይችሉ አቅም በማጣት ተሸንፈው ይወድቃሉ። ግዜያችሁንና ጉልበታችሁን ከደካሞች ጋር በመላፋት አታባክኑ። ከፍታን ምረጡ!! እናንተ ከፍ ስትሉ ራሳቸው ይወድቃሉ እንጅ እነሱን ለመጣል ምንም ጉልበት አታባክኑ!!!
Friday, 31 October 2025
Thursday, 30 October 2025
ነገረ ማርያም
ይህ የነገረ ማርያም ትምህርት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰቷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷያ ያለውን የሕይወቷን ታሪክ ብቻ የሚያጠና ሳይሆን ፣ስለ አምላክ እናትነቷ (እግዚአብሔር ወልድ ተወለደ፣ሰው ሆነ ስንል እንዴት ሰዉ ሆነ የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ) ፣ ስለ ዘላለማዊ ድንግልናዋ፣ በነገረ ሥጋዌ (በነገረድ ድኅነት ትምህርት ዉስጥ ) ስላላት ድርሻ ፣ ስለ ንጽሕናዋ ፣ቅድስናዋ፣ስለተሰጣት ክብር ጨምሮ የሚያጠና የሚያካትት የሃይማኖት ትምህርት ክፍል ነው፡፡ ነገረ ማርያም የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የነገረ ድኅነት አስተምህሮ አካል ነዉ፡፡
መጽሃፉን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ 👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1KTISm0Nsu-1_xEm-PRKsyHHAwZhYEfI_/view?usp=drivesdk
Sunday, 26 October 2025
ልክ እንደ ቀስት ሁን፡ ወደኋላ መሳብ ረጅም ርቀት ይሄዳል 🏹🌟
በሕይወታችን ውስጥ ነገሮች የዘገዩብን፣ ጊዜያችን የባከነ ወይም ሁኔታዎች ከአቅማችን በላይ ሆነው ወደ ኋላ እየጎተቱን እንደሆነ ተሰምቶን ያውቅ ይሆናል!
ይህ ስሜት ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፣ ከኋላው ግን የሕይወት ትልቁን ምስጢር ደብቋል።
"አንድ ቀስት ወደ ኋላ በተለጠጠ ቁጥር ወደ ፊት የሚወነጨፍበት ርቀት #እየጨመረ ይሄዳል!"
የእኛም ሕይወትም ልክ እንደዚህ ቀስት ነው። በአሁኑ ጊዜ ከአቅም በላይ በሆኑ ሁኔታዎች ምክንያት ወደ ኋላ የሄድን ወይም ጊዜው የባከነ ቢመስልም፣ ይህ ማለት ግን #አብቅቷል ማለት አይደለም።
Thursday, 23 October 2025
አውሬው 666 ማን ነው? ከኢሉሚናቲ ሚስጥራዊ ማህበረሰብ በስተጀርባ የተደበቀው እውነት ምንድን ነው?
ምዕራፍ1፡ የ666 እና የአውሬው ምንነት
📌 የ666 ትርጉም፡-
በመጀመሪያ ደረጃ፣ 666 ቁጥር ከክርስትና መጽሐፍ ቅዱስ የመጣ ነው። የዮሐንስ ራእይ 13:18 "ጥበብ ያለው ሰው አውሬውን ቁጥር ያስብ፤ ቁጥሩ ደግሞ የሰው ቁጥር ነውና፤ ቁጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት (666) ነው።" በራእዩ ውስጥ፣ "አውሬ" የሚለው ቃል የሐሰት ነቢይ ወይም ፀረ-ክርስቶስ (AntiChrist) ማለት ነው። ስለዚህ 666 የፀረ-ክርስቶስ ምልክት ወይም "ቁጥር" ነው። ይህ ክፉ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚቃረን ኃይልን ያመለክታል።
ከስሙ ትርጉም ስንነሳ፤ እነዚህ ሦስት ስድስቶች ምንድን ናቸው? በብዙ መልኩ ሊቃውንት አባቶቻችን ቢተረጉሙትም ለግንዛቤ ያህል ሁለቱን ጠቅሼ አልፋለሁ።
✔ 1ኛ... 666 ማለት፤ የመጀመሪያው 6 የሚወክለው የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ቀን ነው። ይህም ስድስተኛው ቀን ነው። ሁለተኛው 6 የሚወክለው የቀትር አጋንንት (ማለትም የአየር ላይ አጋንንት) ከሰማይ ወደ ምድር የተበተኑበትን ሰዓት ይወክላል። ሦስተኛውና የመጨረሻው 6 ደግሞ የሚወክለው፤ መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት፣ ጠላት ዲያቢሎስ ድል የተነሳበት፣ ነፍሳት ከሲኦል የወጡበት ሰዓት ስለሆነ በዋናነት እነዚህን ሦስት ስድስቶችን የያዙትን ጊዜአት እንደሚቃወም ለመግለፅ ራሱን በሦስት ስድስቶች (666) ወከለ በማለት ሊቃውንት አባቶች ያመሰጥሩታል።
✔ 2ኛ.... 666 ምንድን ነው ለሚለው ደግሞ፤ አባቶቻችን በጥንት መፅሐፍቶች ላይ ከትበውልን እንዳለፉት፤ ሦስት ስድስቶች የሆኑበትን ምክንያት 'ሥላሴን እቃወማለሁ' ማለት ነው ይላሉ። እንዴት ቢሉ፤ ሥላሴ ማለት 'ሠለሰ' ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን 'ሦስት አደረገ፣ ሦስት' የሚል ትርጉም አለው። የሥላሴ ሦስትነት ምን አይነት ሦስትነት ነው ቢሉ መልሱ ልዩ ሦስትነት ነው። የስድስቶች ብዛት (666) ሦስት የሆነበት ምክንያት አንድም የሥላሴን ልዩ ሦስትነት እቃወማለሁ ሲል ነው ይላሉ።




