ለህብረተሰቡ እለታዊ የገበያ ዋጋ መረጃ የሚሰጥ አዲስ ድህረ-ገፅ ይፋ ሆነ
www.aaminfo.gov.et
---------------------------------------
የካቲት 05/2013 - የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት በከተማዋ ያሉ የገበያ ማዕከላትን በማስተሳሰር በተለይ ሸማቹ ማህበረሰብ ቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልክና የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም መረጃዎችን በማግኘት ግብይት ማግኘት ያስችላል ብለዋል።
በተጨማሪም የምርት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማወቅ፣ በምርቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪን ለመለየት እና ሸማቹ ህብረተሰብ በየትኛው የገበያ ስፍራ በምን አይነት ምርት በምን ዋጋ እንደሚሸጥ ካለበት ሆኖ ለማወቅ እንደማያስችል ኃላፊው ገልጸዋል።



