Thursday, 31 October 2024

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?

‎ኢየሱስ ክርስቶስ፦


‎ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነ፤ (ማቴ ፳፰፥፲፱)
‎ከአብ ጋር ዕሪና ያለው፤   (ዮሐ ፲፥፵)
‎ዓለም ሳይፈጠር የነበረ፤   (ዮሐ ፩፥፩)
‎ዓለምን የፈጠረ ፈጣሪ፤  (ዕብ  ፲፩፥፪)
‎በቅድምና ከአብ የተወለደ፤ (መዝ ፪፥፯)
‎ሥጋ እንደሚለብስ በራሱ የመሰከረ፤ (ዘፍ ፫፥፳፪)
‎ወደ ገነት ገብቶ አዳምን የፈለገ፤ (ዘፍ ፫፥፱)
‎በነቢያት አስቀድሞ የታወቀ፤ (ኢሳ ፵፪፥፩-፭)
‎አብ ልጄ ብሎ የጠራው፤ (ማቴ ፲፯፥፭)
‎ምሳሌ የተመሰለለት፤    (፩ኛ ቆሮ ፲፥፬)
‎ሱባዔ የተቆጠረለት፤  (ገላ ፬፥፬)
‎በብሥራተ መልአክ የተጸነሰ፤ (ሉቃ ፩፥፴፩)
‎ሥጋን የለበሰ (ማቴ ፩፥ ፳፫)
‎ቁራኝነትን ያጠፋ፤ (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳፬)

Thursday, 14 December 2023

የተፈጥሮ ሕግጋት ጥናት( physics)

በምንኖርባት አለም እና በዙሪያው ባለው ነገር ስለ አሠራሩ፣ ሰለሁኔታወች እና ስለእድገቱ ጥናት ማድረጉ ተፈጥሯዊ እና ትክክለኛ ነው፡፡ ቀድሞውኑ ገና በልጅነት ዕድሜው ትምህርት ቤቱ ሕፃናትን እነዚህን መርሆዎች ለማስተዋወቅ ለብዙዎች ለኢትዮጵያውያን ይህን ሳይንስ  ለማስተዋወቅ “ፊዚክስ"  በማለት 7ኛ ክፍል በሚለው የመማሪያ መጽሐፍ ይጀምራል ፡፡ 

ፊዚክስ (የተፈጥሮ ህግጋት) ከተፈጥሮ ሳይንስ መስኮች አንዱ ነው ፡፡ ስለ ተፈጥሮ ሕጎች ይናገራል ፣ ድርጊቱ በሁሉም ሰው ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፣ በብዙ ጉዳዮችም እንኳን ስለ ቁስ አካላት ፣ አወቃቀሩ እና የእንቅስቃሴ ሕጎች ይሰጣል ፡፡

“ፊዚክስ” የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበው በአሪስቶትል ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራተኛው ክፍለ ዘመን ነው ፡፡ በመጀመሪያ “ፍልስፍና” ከሚለው ፅንሰ-ሀሳብ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ ደግሞም ፣ ሁለቱም ሳይንስ አንድ የጋራ ግብ ነበራቸው - የአጽናፈ ዓለሙን አሠራር ሁሉ በትክክል ለማብራራት ፡፡ ግን ቀድሞውኑ በአሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን በሳይንሳዊ አብዮት ምክንያት ፊዚክስ ራሱን የቻለ ሆነ ፡፡

Monday, 24 April 2023

ስለእመቤታችን ስዕለ አድኖ

 አንባቢያን ልታስተውሉት የሚገባው እጅግ በምስጢር ከተሞላው የእመቤታችን ስዕለ አድኖ እኔም እናንተም በጥቂቱ እናውቅ ዘንድ በማሳጠር በአጭር አማርኛ የፃፍኩት እና ሌሎች ትርጓሜዎችም ያሉት መሆኑን ልትረዱ ይገባል!! በተጨማሪ ቀስት ከቀስት ለይታችሁ ተመልከቱ!



#ሀ > አክሊለ ብርሃን ሲሆን ይህም በሁሉም ቅዱሳን አናት ላይ ተደርጎ የሚቀመጥ ሲሆን ቅዱስነታቸውን፤ መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው መሆኑን ያመለክታል!

#ለ > የእመቤታችን ከውስጥ የምትለብሰው ቀይ ልብስ ፤ አረጋዊ ስምዖን በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል እንዳላት ጌታን ከፀነሰች ጀምሮ ከእርሱ ጋርም የደረሰባትን ሀዘን፤ ጭንቁን፤ መከራዋን ሁሉ የሚያመለክት ሲሆን አንድም እሳተ መለኮትን በውስጧ የተሸከመች መሆኗን ያመለክታል!!

#ሐ > በእመቤታችን በስተ ቀኝ ትከሻዋ ላይ ያለው ኮከብ ጊዜ ወሊድ ድንግል መሆኗን ያመለክታል!