Tuesday, 4 November 2025

ብሔረ ብፁዓን


‎አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን

‎ባሕረ ጥበባት የሆነች ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አስተምህሮዋ ሙሉ በሙሉ በመለኮታዊ መገለጥ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በሥጋዊና በደማዊ የግል አስተሳሰብና ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ አንድም አስምህሮ የላትም፡፡ ከልዑል እግዚአብሔር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው ልጆቿም ቅድስናን ገንዘብ ያደረጉ ናቸው፡፡ ቅድስናንም ገንዘብ ማድረጋቸው ሰማያዊው ምሥጢር ፍንትው ብሎ እንዲታያቸው ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡

‎ፈጣሬ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር አንድ ዓለም ብቻ ሳይሆን 20 የተለያዩ ዓለማትን እንደፈጠረ የምታውቅ ብቸኛዋ የእምነት ተቋም ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ብቻ ናት፡፡ ስነ ፍጥረትን እጅግ በሚገርም ሁኔታ ተንትኖ የሚያቀርበው መጽሐፈ አክሲማሮስም ሆነ ሌሎቹ ቤተክርስቲያን ድርሳናት እንደሚያስረዱት ከሆነ እግዚአብሔር 20 የተለያዩ ዓለማትን ፈጥሯል። እነዚህም፡- 5ቱ ዓለማተ መሬት፣ 4ቱ ዓለማተ ማይ፣ 2ቱ ዓለማተ ነፋስ እና 9ኙ ዓለማተ እሳት ናቸው፡፡

Saturday, 1 November 2025

ከፍታህን ምረጥ! ‎

 ‎ 

1. ንስሮች በከፍታ ለብቻቸው ይበራሉ፦ ንስር ፈፅሞ ከጥንብ አንሳ፣ ቁራና መሰል ትናንሽ አእዋፍት ጋር  አብሮ አይበርም።

‎📌 ንስርን በተፈጥሮ ከሚገዳደሩት የወፍ ዝርያዎች መካከል አንዱና ዋነኛ የሆነው ቁራ ነው። ቁራ በንስሩ ጀርባ ላይ በመፈናጠጥ የንስሩን አንገቱን እና ጀርባውን መንከስ ይጀምራል። በዚህን ጊዜ ንስሩ ለመከላከል ወይም ከላዩ ላይ ለማስወገድ የሚያደርገው አንዳችም ዓይነት ምላሽ አይኖርም። ጸብ ውስጥም አይገባም፣ ግጭትም አይፈጥርም።

‎ከቁራው ጋር እየታገለ ምንም ዓይነት ጊዜና ጉልበትንም አያባክንም። ነገር ግን አንድ ነገር ያደርጋል። ይህም ንስሩ ረዣዥም ክንፎቹን በመዘርጋት ከፍ ወዳለው ወደ ሰማየ ሰማያት መወንጨፍ ይጀምራል።

‎ከፍታው በጨመረ ቁጥር ቁራው አየር ንብረቱን መቋቋም ስለማይችል መተንፈስ አስቸጋሪ ይሆንበታል። በስተመጨረሻም በኦክስጂን እጥረት ምክንያት ቁራው ከጀርባው ላይ ይወድቃል። ከራዎች ጋር ጊዜያችሁን አታባክኑ። 

ቀጥታ ወደ ከፍታ ውሰዷቸው። የዚያን ጊዜ መተንፈስ ስለማይችሉ አቅም በማጣት ተሸንፈው ይወድቃሉ። ግያችሁንና ጉልበታችሁን ከደካሞች ጋር በመላፋት አታባክኑ። ከፍታን ምረጡ!!  እናንተ ከፍ ስትሉ ራሳቸው ይወድቃሉ እንጅ እነሱን ለመጣል ምንም ጉልበት አታባክኑ!!!

Thursday, 30 October 2025

ነገረ ማርያም

መግቢያ፡- 

ይህ የነገረ ማርያም ትምህርት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰቷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷያ ያለውን የሕይወቷን ታሪክ ብቻ የሚያጠና ሳይሆን ፣ስለ አምላክ እናትነቷ (እግዚአብሔር ወልድ ተወለደ፣ሰው  ሆነ ስንል እንዴት ሰዉ ሆነ የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ) ፣ ስለ ዘላለማዊ ድንግልናዋ፣ በነገረ ሥጋዌ (በነገረድ ድኅነት ትምህርት ዉስጥ ) ስላላት ድርሻ ፣ ስለ ንጽሕናዋ ፣ቅድስናዋ፣ስለተሰጣት ክብር ጨምሮ የሚያጠና የሚያካትት የሃይማኖት ትምህርት ክፍል ነው፡፡ ነገረ ማርያም የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የነገረ ድኅነት  አስተምህሮ አካል ነዉ፡፡

መጽሃፉን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ 👇👇👇

https://drive.google.com/file/d/1KTISm0Nsu-1_xEm-PRKsyHHAwZhYEfI_/view?usp=drivesdk




Sunday, 26 October 2025

ልክ እንደ ቀስት ሁን፡ ወደኋላ መሳብ ረጅም ርቀት ይሄዳል 🏹🌟


በሕይወታችን ውስጥ ነገሮች የዘገዩብን፣ ጊዜያችን የባከነ ወይም ሁኔታዎች ከአቅማችን በላይ ሆነው ወደ ኋላ እየጎተቱን እንደሆነ ተሰምቶን ያውቅ ይሆናል!

ይህ ስሜት ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፣ ከኋላው ግን የሕይወት ትልቁን ምስጢር ደብቋል።

"አንድ ቀስት ወደ ኋላ በተለጠጠ ቁጥር ወደ ፊት የሚወነጨፍበት ርቀት #እየጨመረ ይሄዳል!"

የእኛም ሕይወትም ልክ እንደዚህ ቀስት ነው። በአሁኑ ጊዜ ከአቅም በላይ በሆኑ ሁኔታዎች ምክንያት ወደ ኋላ የሄድን ወይም ጊዜው የባከነ ቢመስልም፣ ይህ ማለት ግን #አብቅቷል ማለት አይደለም።

Thursday, 23 October 2025

የ666 ሚስጥር እና ከኢሉሚናቲ ሚስጥራዊ ማህበረሰብ በስተጀርባ የተደበቀው እውነት

ምዕራፍ1፡ የ666 እና  የአውሬው ምንነት

📌 የ666 ትርጉም፡-

በመጀመሪያ ደረጃ፣ 666 ቁጥር ከክርስትና መጽሐፍ ቅዱስ የመጣ ነው። የዮሐንስ ራእይ 13:18 "ጥበብ ያለው ሰው አውሬውን ቁጥር ያስብ፤ ቁጥሩ ደግሞ የሰው ቁጥር ነውና፤ ቁጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት (666) ነው።" በራእዩ ውስጥ፣ "አውሬ" የሚለው ቃል የሐሰት ነቢይ ወይም ፀረ-ክርስቶስ (AntiChrist) ማለት ነው። ስለዚህ 666 የፀረ-ክርስቶስ ምልክት ወይም "ቁጥር" ነው። ይህ ክፉ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚቃረን ኃይልን ያመለክታል።

ከስሙ ትርጉም ስንነሳ፤ እነዚህ ሦስት ስድስቶች ምንድን ናቸው? በብዙ መልኩ ሊቃውንት አባቶቻችን ቢተረጉሙትም  ለግንዛቤ ያህል ሁለቱን ጠቅሼ አልፋለሁ።

✔ 1ኛ... 666 ማለት፤ የመጀመሪያው 6 የሚወክለው የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ቀን ነው። ይህም ስድስተኛው ቀን ነው። ሁለተኛው 6 የሚወክለው የቀትር አጋንንት (ማለትም የአየር ላይ አጋንንት) ከሰማይ ወደ ምድር የተበተኑበትን ሰዓት ይወክላል።  ሦስተኛውና የመጨረሻው 6 ደግሞ የሚወክለው፤ መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት፣ ጠላት ዲያቢሎስ ድል የተነሳበት፣ ነፍሳት ከሲኦል የወጡበት ሰዓት ስለሆነ በዋናነት እነዚህን ሦስት ስድስቶችን የያዙትን ጊዜአት እንደሚቃወም ለመግለፅ ራሱን በሦስት ስድስቶች (666) ወከለ በማለት ሊቃውንት አባቶች ያመሰጥሩታል።

✔ 2ኛ.... 666 ምንድን ነው ለሚለው ደግሞ፤ አባቶቻችን በጥንት መፅሐፍቶች ላይ ከትበውልን እንዳለፉት፤ ሦስት ስድስቶች የሆኑበትን ምክንያት 'ሥላሴን እቃወማለሁ' ማለት ነው ይላሉ። እንዴት ቢሉ፤ ሥላሴ ማለት 'ሠለሰ' ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን 'ሦስት አደረገ፣ ሦስት' የሚል ትርጉም አለው። የሥላሴ ሦስትነት ምን አይነት ሦስትነት ነው ቢሉ መልሱ ልዩ ሦስትነት ነው። የስድስቶች ብዛት (666) ሦስት የሆነበት ምክንያት አንድም የሥላሴን ልዩ ሦስትነት እቃወማለሁ ሲል ነው ይላሉ።

Saturday, 18 October 2025

ማኅሌተ ጽጌ፤ ምንጩ ትርጉሙና መልእክቱ


ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ኃይለ ቃልን ከትርጓሜ፣ ትርጓሜንከምሥጢር እንዲሁም ደግሞ ምሥጢርን ከዜማ ጋርአስተባብረውና አስማምተው የሚደርሱ ሊቃውንት ባለቤትናት፡፡ በ5ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድአምስቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ14ኛው መ.ክ.ዘመንየተነሣው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡ በዚሁ ዘመንአባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌድንግል “ማኅሌተ ጽጌ” የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡ ማኅሌተጽጌ ግጥማዊ አካሔድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው፡፡ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታበቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግልማርያም የስደት ዘመን ነው፡፡ በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድሌሊት በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ መሰደድናመንከራተት እያሰቡ የሚደረስ ምሥጋናና ጸሎት ነው፡፡

በሀገራችን የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት /ዘመነ ጽጌ/ ናቸው፡፡ ይህም ወቅት ተራሮች በአበባየሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡በዚህም ዘመን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ስለልብስስ ስለምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴትእንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡ አይደክሙም፣አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡ እግዚአብሔርን ዛሬያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህየሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጐደላችሁ እናንተንማይልቁን እንዴት እንግዲህ ምን እንበላለን ምንስ እንጠጣለን?ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ ...» /

Saturday, 4 October 2025

ደብረ ደደክን ፍለጋ‼️ ገነት ያለችብት ስፍራ 👉 ከኢትዮጵያ ጀርባ ምን መለኮታዊ ሚስጥር አለ?

 በቲና በቀለ


#ከአመታት_በፊት እንዲህ ሆነ... ከአንድ ወዳጄ ጋር ባህርዳር ጣና አካባቢ ተቀምጠን በብዙ ሀሳቦች ላይ እየተወያየን ባለንበት ሰአት እኛ ከተቀመጥንበት በስተቀኝ በኩል ጓደኛዬ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎችን ይመለከታል እንዳስታውላቸው ይነግረኛል።

ሴትና ወንድ በእድሜም ጠና ያሉ ነጮች ናቸው፤ ወደ ሰሜን ምዕራብ ጣና ሀይቅ አካባቢ ውድ፣ ዘመናዊ በግለሰብ ደረጃ ብዙም የማይገኘው መቅረጸ ትዕይንት Camera አቅርቦ የሚያሳይ telescope ከጀረባቸው እንዲሁም ትልቅዬ ቦርሳን አዝለው ወደ ሀይቁ አይናቸውን በሁለት አቅጣጫ እያመላለሱ በተደጋጋሚ ይመለከታሉ።


ለብዙ ደቂቃወች ይህንን የጠለቀ እይታ እና የሚጠቀሙትን ውድ ዘመናዊ Telescope ስመለከት እኒህ ሰው የመልካ ምድር አሳሾች ወይም የጥንት መዛግብት ተመራማሪወች ሊሆኑ እንደሚችሉ ገመትኩ።......

Saturday, 27 September 2025

Very Useful Resources for Video Editors!

1. Images:

Remove image background - https://removal.ai/

Stock Images - https://unsplash.com/

PNGs -https://pngtree.com/

Upscale images - https://www.photopea.com/?utm_source=homescreen

Wednesday, 3 September 2025

Gmail 2-step verification


Gmail 5 አይነት አማራጭ የ2-step verification መንገዶች አሉ።

በነገራችን ላይ የGmail ፓስዎርዳችሁ ባታስታውሱት ራሱ login ለማድረግ 2-step verification ብቻ መጠቀም ትችላላችሁ። 




እነዚህ የverification መንገዶች

Friday, 22 August 2025

ለሞባይል ጥገና የሚያስፈልጉን መሳሪያወች


1. መፍቻ ፦ ስልካችን ለመፍታት እና ለመግጠም ይጠቅማል ።

2. መልቲ ሜትር:- ሬዚስታንስ ፣ ቮልቴጅ እንዲሁም ከረንት ለመለካት እና የሰርኪዩት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ይጠቅመናል ።

3. ቲነር ፦ ዝገት ለመከላከል እና ቆሻሻ ለማስወገድ ይጠቅማል ።

4. ፔስት ፦ አይሲዎችን በመንቀያና በማስቀመጫ ሰአት ቦርዳችንና የሚነቀለዉ አይሲ በሙቀት እንዳይጓዳ ይጠቅማል ።

5. ብሎወር ፦ ሙቀትን በመስጠት አይሲዎችን ለመንቀልና ለማስቀመጥ ይጠቅማል ።

Monday, 30 June 2025

Websites for Online Courses

1- www.edx.org 
2- www.coursera.org 
3- www.udacity.com 
4- www.stjegypt.com 
5- www.edraak.org 
6- www.venture-lab.org 
7- www.education.10gen.com 
8- www.openhpi.de 
9- www.ocw.mit.edu 

Wednesday, 30 April 2025

Computer keyboard Function keys


የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?

ካላወቃችሁ አትጨነቁ፡፡ ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው:: ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::