ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ሚያዚያ ወር 1970፡፡ በአብዛኛው በሚሊሺያ ሀይል የተገነባው የኢትዮጵያ ሰራዊት እብሪተኛውን የሶማሊያ ወራሪ ያባረረበት የካራ ማራ የድል በዓል እንዲከበር ተወሰነ፡፡ መሆኑም በምስራቅ ኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች በአማርኛ እንዲህ እየተባለ ተዘፈነ፡፡
“አባርሮ ገዳይ በረሃ ያለው
ጠላቴን ዛሬ አወድመዋለሁ”
ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድል ነው፡፡ ክርስቲያንም ሆነ ሙስሊም፣ ኦሮሞም ሆነ አማራ ሀገርን ከወራሪ ለማዳን በተደረገው ጦርነት ደሙን አፍስሷል፤ አጥንቱን ከስክሷል፡፡ በመሆኑም በውጊያው ከፍተኛ ተሳትፎ የነበረው የምስራቁ የኦሮሞ ህዝብ እንዲህ ሲል ዘፍኗል፡፡
Jijjigaa gadi Ogaadeenis tiyya
Irrattin du’a biyya haadha tiyyaa
በቀላል አማርኛ ስንፈስረው እንደዚህ ሊሆን ይችላል፡
“ከጅጅጋ በታች ኦጋዴንም የኔ ናት
እሞትላታለሁ ሀገሬ እናቴ ናት”