በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን እና ሀገር ጐብኚዎች ወደ ቅዱስ ላሊበላ መናገሻ ከተማ 11ዱ ፍልፍል አብያተ-ክርስቲያናት ወደሚገኙበት ሮሃ ከተማ ይጓዛሉ። ምክንያታቸው ደግሞ ታሪክና ጥበብን ለማወቅ እንዲሁም በረከትን ለማግኘት። በዚህ የጉዞ ማስታዎሻ ስለ ቅዱሱ ንጉስ( Holly king) ቅዱስ ላሊበላ እና ስራዎቹ ከላሊበላ ሰማይ ስር ስላሉት ነገሮች እናወሳለን።
ማውጫ
- #Editor (1)
- ፩. ታሪክና ህብረተሰብ (10)
- ፪. የህይወት ክህሎት (4)
- ፫. ነጻ ሃሳብ (6)
- ፬. ቤተ-አምልኮ (16)
- ፭. ኪነ-ጥበብ (9)
- ፮. ውብ ሀገር (7)
- ፯. አገራዊ ጉዳዮች (2)
- ፰. ሳይንስና ቴክኖሎጅ (ሳይቴክ) (8)
- ፱. ንግድና ኢኮኖሚ (9)
- ለቤተ-መፅሃፍትዎ (4)
- ስራ-Vacancy (1)
- የጉዞ ማስታወሻ (1)
Tuesday, 21 December 2021
Monday, 6 December 2021
ሰብአ ሰገል
የሰብአ ሰገል ምንነት፥ ታሪክ፥ ኮከቡ፥ ጉዟቸው፥ በስተመጨረሻው መሰወራቸው
አባታችን አዳም በዕለተ አርብ በነግህ ከተፈጠረ በኋላ እናታችን ሔዋን በሳምንቱ አርብ በዘመናችን አነጋገር 3 ሰዓት ላይ ከግራ ጎኑ ተፈጠረች። በገነትም 7 ዓመት ከ3 ወር ከ 17 ዕለታት ካሳለፉ በኋላ ሕግን ተላልፈው እፀ በለስን በመብላታቸው ከገነት ተባረሩ። በዚህ ግዜ አምላካችን እግዚአብሔር ለአዳም የተስፋ ቃል ሰጠው፤ እርሱም ከልጅ ልጅህ ተወልጀ ከ5 ቀን ከመንፈቅ በኋላ አድንሃለሁ የሚል ቃል ነበረ። ይህ የተስፋ ቃልና ከመላእክት ለአዳም የተሰጡትን ስጦታዎች አዳምና የልጅ ልጆቹ ሲቀባበሉት ቆይቶ ከካሕኑ መልከጼዴቅ እጅ ላይ ደረሰ። ከመልከጼዴቅ አንዳንዶቹ ለአብርሃም ተሰጠ ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ለኢት-ኤል ተሰጠ ይላሉ።
Subscribe to:
Posts (Atom)