ኑ የበረከት ስራ እንስራ
ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ፣ ወልደ ነጎድጓድ፣ ፍቁረ እግዚእ፣ ነባቤ መለኮት(ታኦሎጎስ)፣ ቁጽረ ገጽ በመባል የሚታወቀው ወንጌላዊው ቅዱስ ዩሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣት የመጨረሻው ሽማግሌ ሐዋርያ እሱ ነበር፡፡
ቅዱስ ዩሐንስ የተወለደው በገሊላ አውራጀ በቤተ ሳይዳ ነው፣ አባቱ ዘብዴዎስ ይባላል፡፡ ቅዱስ ዩሐንስ ገና በወጣትነቱ ዘመን ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮ የጌታውን እግር ተከትሎ አድጓል፡፡ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የጌታ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ከነበሩት ደቀ መዛሙርት አንዱ ነው፡፡