Wednesday, 30 April 2025

Computer keyboard Function keys


የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?

ካላወቃችሁ አትጨነቁ፡፡ ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው:: ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::

Thursday, 31 October 2024

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?

‎ኢየሱስ ክርስቶስ፦


‎ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነ፤ (ማቴ ፳፰፥፲፱)
‎ከአብ ጋር ዕሪና ያለው፤   (ዮሐ ፲፥፵)
‎ዓለም ሳይፈጠር የነበረ፤   (ዮሐ ፩፥፩)
‎ዓለምን የፈጠረ ፈጣሪ፤  (ዕብ  ፲፩፥፪)
‎በቅድምና ከአብ የተወለደ፤ (መዝ ፪፥፯)
‎ሥጋ እንደሚለብስ በራሱ የመሰከረ፤ (ዘፍ ፫፥፳፪)
‎ወደ ገነት ገብቶ አዳምን የፈለገ፤ (ዘፍ ፫፥፱)
‎በነቢያት አስቀድሞ የታወቀ፤ (ኢሳ ፵፪፥፩-፭)
‎አብ ልጄ ብሎ የጠራው፤ (ማቴ ፲፯፥፭)
‎ምሳሌ የተመሰለለት፤    (፩ኛ ቆሮ ፲፥፬)
‎ሱባዔ የተቆጠረለት፤  (ገላ ፬፥፬)
‎በብሥራተ መልአክ የተጸነሰ፤ (ሉቃ ፩፥፴፩)
‎ሥጋን የለበሰ (ማቴ ፩፥ ፳፫)
‎ቁራኝነትን ያጠፋ፤ (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳፬)

Monday, 24 April 2023

ስለእመቤታችን ስዕለ አድኖ

 አንባቢያን ልታስተውሉት የሚገባው እጅግ በምስጢር ከተሞላው የእመቤታችን ስዕለ አድኖ እኔም እናንተም በጥቂቱ እናውቅ ዘንድ በማሳጠር በአጭር አማርኛ የፃፍኩት እና ሌሎች ትርጓሜዎችም ያሉት መሆኑን ልትረዱ ይገባል!! በተጨማሪ ቀስት ከቀስት ለይታችሁ ተመልከቱ!



#ሀ > አክሊለ ብርሃን ሲሆን ይህም በሁሉም ቅዱሳን አናት ላይ ተደርጎ የሚቀመጥ ሲሆን ቅዱስነታቸውን፤ መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው መሆኑን ያመለክታል!

#ለ > የእመቤታችን ከውስጥ የምትለብሰው ቀይ ልብስ ፤ አረጋዊ ስምዖን በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል እንዳላት ጌታን ከፀነሰች ጀምሮ ከእርሱ ጋርም የደረሰባትን ሀዘን፤ ጭንቁን፤ መከራዋን ሁሉ የሚያመለክት ሲሆን አንድም እሳተ መለኮትን በውስጧ የተሸከመች መሆኗን ያመለክታል!!

#ሐ > በእመቤታችን በስተ ቀኝ ትከሻዋ ላይ ያለው ኮከብ ጊዜ ወሊድ ድንግል መሆኗን ያመለክታል!