Tuesday, 18 May 2021

ታሪክን መማርና ማወቅ መጀመሪያ የድንቁርና ዕውር ዓይን ይከፈታል

 ታሪክን መማርና ማወቅ መጀመሪያ የድንቁርና ዕውር ዓይን ይከፈታል ሰነፎችንም በምክሩና በትምህርቱ ከድንቁርና ወደ ጥበብ ይመልሳል።

 ታሪክ ሦስቱን ዘመናት/ትውልድ (ኃላፊውን፣ ነባራዊውንና መጻዒውን) የሚያስተሳስር ድንቅ ድልድይ ነው፡፡ 

ታሪክ አንድን ጉዳይ ከሥር መሠረቱ ጀምረን እንድናውቀው ስለሚያግዘን የአንድን ክሰተት እውነታነት በስሜት ያይደለ አሳማኝ በሆነና ቅቡልነት ባለው መልኩ (logically) እንድንሞግተው፣ አልያም እንድንቀበለውም ያግዘናል፡፡ እናም ታሪክን በአግባቡ የሚያጠና ትውልድ በቂ መረጃ ያለው (well informed)፣ በራሱ የሚተማመን (self-confident) እና ትክክለኛውን ውሳኔ መስጠት የሚችል (decision maker) ይሆናል፡፡