የአፋር ብሔረሰብ ታሪክና ባህል አጭር ቅኝት
የአፋር ብሔራዊ ክልል ከትግራይ በሰሜን ምዕራብ፣ ከአማራ በደቡብ ምእራብ እና ከኦሮሚያ በደቡብ በኩል የሚዋሰን ሲሆን ከኤርትራ ጋር በሰሜን ምስራቅ፣ ከጅቡቲ ደግሞ በምስራቅ በኩል ይዋሰናል። የክልሉ ሕዝብ በ27,000 ስኩዬር ኪሎ ሜትር ስፍራ ላይ ይኖራል። በአምስት የዞንና በ32 የወረዳ አስተዳደሮች የተዋቀረው ክልሉ በምስራቅ አቅጣጫ ኢትዮጵያን ከሌላው አለም ጋር የሚያገናኝ የተፈጥሮ ድልድይ ሲሆን የብሔረሰቡ አባላት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራና በጅቡቲ ሰፍረው ይገኛሉ።