Thursday, 31 October 2024

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?

‎ኢየሱስ ክርስቶስ፦


‎ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነ፤ (ማቴ ፳፰፥፲፱)
‎ከአብ ጋር ዕሪና ያለው፤   (ዮሐ ፲፥፵)
‎ዓለም ሳይፈጠር የነበረ፤   (ዮሐ ፩፥፩)
‎ዓለምን የፈጠረ ፈጣሪ፤  (ዕብ  ፲፩፥፪)
‎በቅድምና ከአብ የተወለደ፤ (መዝ ፪፥፯)
‎ሥጋ እንደሚለብስ በራሱ የመሰከረ፤ (ዘፍ ፫፥፳፪)
‎ወደ ገነት ገብቶ አዳምን የፈለገ፤ (ዘፍ ፫፥፱)
‎በነቢያት አስቀድሞ የታወቀ፤ (ኢሳ ፵፪፥፩-፭)
‎አብ ልጄ ብሎ የጠራው፤ (ማቴ ፲፯፥፭)
‎ምሳሌ የተመሰለለት፤    (፩ኛ ቆሮ ፲፥፬)
‎ሱባዔ የተቆጠረለት፤  (ገላ ፬፥፬)
‎በብሥራተ መልአክ የተጸነሰ፤ (ሉቃ ፩፥፴፩)
‎ሥጋን የለበሰ (ማቴ ፩፥ ፳፫)
‎ቁራኝነትን ያጠፋ፤ (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳፬)